Your cart is currently empty!
በኢትዮ-ኢንጅነሪንግ ግሩፕ የኮንስትራክሽን ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ Belt & pully, Electrical item & others, Vehicle spare parts, Oil, Grease & Chemical መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 18, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
የጨረታ ማስታወቂያ
ብሔራዊ ግልፅ ጨረታ ቁጥር ኮማማኢ/ሰቼ ማ/02/2018
በኢፌዲሪ ኢትዮ-ኢንጅነሪንግ ግሩፕ የኮንስትራክሽን ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ
- የግዥ አይነት፦ Belt& pully, Electrical item & others, Vehicle spare parts, Oil, Greas & Chemical
የተጫራቾች መመሪያና ግዴታ
1. በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
2. የግብር ከፋይነት የተመዘገቡና የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር/TN NO/ያላቸው፡፡
3. ተጨማሪ እሴት ታክስ VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ::
4. ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ ዋስትና ለሚወዳደሩበት ከጠቅላላ ዋጋ VAT ጨምሮ ብር 2% በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም የባንክ ጋራንቲ ማስያዝ አለባቸው።
5. ተጫሪቾች ዋጋ ሞልተው የሚያቀርቡት ከዚህ ሰነድ ጋር ተያይዞ በቀረበው የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ ብቻ ይሆናል፤በዋጋ መሙያ ቅፅ ላይ ስርዝ ድልዝ ማድረግ እጅግ የተከለከለ ነው።
6. ማንኛውም ተጫራች በሌላ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ መስጠት አይቻልም።
7. የመወዳደሪያ ሰነዱን የማይመለስ 400 (አራት መቶ ብር ከ0/100) በመከፈል በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ከላንድ ማርክ ሆስፒታል ትይዩ በሚገኘው ጠማማ ፎቅ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 15 አንደኛ ፎቅ ላይ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ።
8. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በቀረበው ዝርዝር በመሙላት የድርጅቱ ማህተምና ፊርማ በማድረግ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) የስራ ቀናት ውስጥ ኢንዱስትሪው ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት የጨረታ ሰነድ ማስገባት ይችላሉ።
9. የጨረታ ማስገቢያ ቀንና ሰዓት ካለፈ በኋላ የሚቀርብ ጨረታ ሰነድ ተቀባይነት የለውም፡፡
10. የጨረታ መክፈቻ ቀን በሕዝብ በዓላት ቀን ከዋለ የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ በዓሉ በዋለ በማግስቱ ይሆናል።
11. ጨረታው ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈትበት ቀን እና ሰዓት በጨረታ ሰነድ ላይ የሚጠቀስ ይሆናል።
12. የጨረታ አሸናፊ የሆነው ድርጅት አሸናፊ መሆኑን በደብዳቤ ከተገለፀበት በኋላ በሦስት ቀን ውስጥ ቀርቦ ውል በመዋዋል ንብረቱን በኢንዱስትሪው ቅጥር ግቢ ማቅረብ አለበት።
13. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን ኦርጅናሉንና ኮፒውን ለየብቻ በፖስታ አሽገው ማቅረብ አለባቸው፡፡
14. ኢንዱስትሪው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት የተጠበቀ ነው።
15. አድራሻ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ከላንድ ማርክ ሆስፒታል ትይዩ በሚገኘው ጠማማ ፎቅ ግዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 15 አንደኛ ፎቅ ለተጨማሪ ማብራሪያ
በስልክ ቁጥር 09 40 81 62 06/ 09 11 76 98 12 ደውለው መረጃ መጠየቅ ይችላሉ።
በኢትዮ-ኢንጅነሪንግ ግሩፕ
የኮንስትራክሽን ማሽነሪ ማምረቻ ኢንዱስትሪ