Your cart is currently empty!
መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 18, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 118
መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ተሽከርካሪዎቹን ለመግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች አዲስ አበባ ከተማ ለሚ ኩራ ክ/ከተማ ወረዳ 03 (በተለምዶ አያት ኮንዶሚኒየም ከፀበል መድኃኔ ዓለም ቤተክርስቲያን) ፊት ለፊት በሚገኘው በማዕከሉ ዋና መሥሪያ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ከጥቅምት 15 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥቅምት 29 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በመምጣት ለጨረታው የተዘጋጁትን ተሸከርካሪዎች በአካል መመልከት ይችላል፡፡
ተጫራቾች፡–
- የጨረታ ሰነድ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
- የጨረታ ሰነዱ በማዕከሉ ቅጥር ግቢ ውስጥ ለሽያጭ የተዘጋጁትን ተሸከርካሪዎች ዝርዝር የያዘ ሲሆን፣ እየተዘዋወሩ ከተመለከቱ በኋላ ለመግዛት የሚወስኑትን ተሽከርካሪ ይለያሉ፣ ስሙንና የመለያ ቁጥሩን ይይዛሉ፡፡
- ለእያንዳንዱ ተሽከርካሪ የጨረታ ማስከበሪያ (ማስያዣ) የመነሻውን ዋጋ 10% ነው።
- ተጫራቾት የሚገዙበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ፎርም ላይ በመሙላት እና የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ ከተረጋገጠ ሲፒኦ ጋር አያይዘውና በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ እስከ ጥቅምት 29 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 (አራት ሰዓት ተኩል) ድረስ ማስገባት ይችላሉ።
- ጨረታው ጥቅምት 29 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት በማዕከሉ የስብሰባ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
ማዕከሉ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ ማብራሪ በስልክ ቁጥር፡-09 36 91 91 91 ወይም 09 75 26 41 59 መጠየቅ ይቻላል።
መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር