ፒናክል ትሬዲንግ ኃላ.የተ.የግል ማኅበር የሆኑትን 6 (ስድስት) ያገለገሉ የጭነት መኪናዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Reporter(Oct 19, 2025)

ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below. 

የጨረታ ማስታወቂያ

ፒናክል ትሬዲንግ ኃላ.የተ.የግል ማኅበር የሆኑትን 6 (ስድስት) ያገለገሉ የጭነት መኪናዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በዚሁ መሠረት ማንኛውም ተጫራች ጨረታው በሚካሄድበት ቀን መኪናዎቹ በሚገኙበት ቦታ በመገኘት በጨረታው ተወዳድሮ መኪናዎቹን መግዛት ይችላል።

የመኪናዎቹ አጠቃላይ መረጃ፤

.

 

ሰሌዳ ቁጥር

 

የተሽከርካሪው ዓይነት

 

የምርትዘመን

የመጫን አቅም

1

3-B14210

 

EICHER PRO-3008G

 

2019

 

48 ኩንታል

 

2

3-B14214

 

EICHER PRO-3008G

 

2019

 

48 ኩንታል

 

3

3-B14206

 

EICHER PRO-3008G

 

2019

 

48 ኩንታል

 

4

3-B14205

 

EICHER PRO-3008G

 

2019

 

48 ኩንታል

 

5

3-B14240

 

EICHER PRO-3008G

 

2019

 

48 ኩንታል

 

6

3-B14179

EICHER PRO-3008G

 

2019

 

48 ኩንታል

 

1. የመኪናዎቹን ሁኔታ ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች መኪናዎቹ ባሉበት የድርጅቱ መጋዘን በሚገኝበት ሱሉልታ ከተማ ከጎልደን ማደያ ፊትለፊት በመገኘት ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከጥቅምት 10 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከሰኞ እስከ ቅዳሜ በሥራ ሰዓት ከ3፡ 00-5፡00 ከሰዓት ከ8፡00-10፡00 ሰዓት ማየት ይችላሉ።

2. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቶች ከጥቅምት 10 ቀን 2018 ዓ.ም እስከ ጥቅምት 20 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ) በመክፈል ከድርጅቱ ዋና መ/ቤት ቦሌ ላኪ ህንጻ 7ተኛ ፎቅ ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ።

3. ተጫራቾች ለሚጫረቱበት መኪና የመነሻ ዋጋ 2% (ሁለት በመቶ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲ.ፒ.ኦ) ተሠርቶ በጨረታው ቀን ይዞ መቅረብ መመዝገብ ይችላሉ።

4. ጨረታው ጥቅምት 20 ቀን 2018 ዓ.ም ከሰዓት 10፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ጥቅምት 24 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ በ5፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት መኪኖቹ በሚገኙበት ቦታ የሚከፈት ይሆናል።

5. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በጨረታ ዋጋ ሰነዱ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቦታ በመሙላት ዋናውንና ኮፒውን በተለያዩ ፖስታ በማድረግና ሁለቱን ፖስታዎች በአንድ ላይ በሌላ ፖስታ ውስጥ አድርገው በማሸግ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 (አሥር) ተከታታይ የሥራ ቀናት ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።

6. ድርጅቱ የጨረታውን አሸናፊ በደብዳቤ የሚያሳውቅ ሲሆን ውጤቱን ለተሳታፊዎች በግልጽ በማስታወቂያ ቦርድ በመለጠፍ የሚያሳውቅ ይሆናል።

7. የጨረታው አሸናፊ ያሸነፉትን ተሽከርካሪ ሙሉ ክፍያ ጨረታውን ማሸነፉንና መኪናውን እንዲረከብ በደብዳቤ ድርጅቱ ካሳወቀበት ማግስት በሚቆጠር በ15 ቀናት ውስጥ ለድርጅቱ ገቢ በማድረግ መኪናውን መረከብ ይኖርበታል። በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልፈለገ ግን ለጨረታው ያስያዘው ገንዘብ ለድርጅቱ ገቢ ሆኖ ጨረታው ተሰርዞ ለሀራጅ የሚቀርብ ይሆናል። በጨረታው ተሳትፈው ላላሻነፉት ተጫራቾች ያስያዙት ሲፒኦ ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

8. የጨረታው አሸናፊ ለስም ማዛወሪያና ሌሎች ተጓዳኝ ወጪዎችን በሙሉ የሚሸፍን ይሆናል።

9. ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ: በ 09 44 30 91 99/ 09 03 33 02 33/ 09 67 40 50 20 በመደወል መጠየቅ ይቻላል


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *