Your cart is currently empty!
ኬ.ኤ.ኤም ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Reporter(Oct 22, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ቁጥር 007ተሽ/2018
ድርጅታችን ኬ.ኤ.ኤም ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ በጨረታ ቁጥር007ተሽ/2018 በድርጅቱ ቅርንጫፍ መ/ቤት መከኒሳ ሮያል ሴራሚክ አፓርትመንት ቅጥር ግቢ የሚገኙ በማገልገል ላይ የተለያዩ ተሽከርካሪዎችን ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም ተጫራቾች ስለአጠቃላይ የጨረታ ሁኔታ ይረዱ ዘንድ ተፈጻሚ የሚሆኑ ደንቦችን፣ የመኪኖቹን ዝርዝር ከጠቅላላ ማብራሪያና አፈጻጸም ሂደቶች ከዚህ በታች የተዘረዘሩ ሲሆን ተወዳዳሪዎች የጨረታ መስፈርቱ የሚጠይቀውን መወዳደሪያ ነጥቦች በማሟላት ፋይናንሻል ፕሮፖዛል (ዋጋ ማቅረቢያችሁን) እንድታቀርቡ እያሳወቅን፤ በዚህ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡–
1. የጨረታ ማስከሪያ /Bid Bond/ ብር 100,000/ አንድ መቶ ሺህ /ብር በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ / CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
2. የጨረታ ሰነዱ አዲስ አበባ ን/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 02 በጀርመን አደባባይ ምስራቀ ፀሐይ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አጠገብ በሚገኘው ሮያል ሴራሚክ ህንፃ ሁለተኛ ፎቅ የማይመለስ 300/ አምስት መቶ /ብር መክፈል ማስታወቂያው በሪፖረተር ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 8 የስራ ቀናት ውስጥ መውሰድ ይችላሉ።
3. በጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ፋይናንሻል(የዋጋ ማቅረቢያ) ሰነድ እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያ/ cpo/ በአንድ ላይ በማድረግ እና በጥንቃቄ በማሸግ እስከ ጥቅምት 20,2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ድረስ አዲስ አበባ ን/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 02 ጀርመን አደባባይ ምስራቀ ፀሐይ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አጠገብ በሚገኘው ሮያል ሴራሚክ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል:: በዕለቱ ጨረታው ከቀኑ በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ ከቀኑ በ8፡30 ሰዓት ይከፈታል።
4. ጨረታው የሚከፈተው አዲስ አበባ ን/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 02 በጀርመን አደባባይ ምስራቀ ፀሐይ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አጠገብ በሚገኘው ሮያል ሴራሚክ ውስጥ ነው።
5. ዝርዝር የጨረታ መመሪያው ከጨረታ ሰነዱ ውስጥ የተገለፀ ስለሆነ ማንኛውም ተጫራች በጥንቃቄ በማንበብ ዋጋቸውን በጨረታ መመሪያው መሰረት መሙላት አለባቸው።
6. ተሽከርካሪዎቹን መጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች የጨረታ ሰነዱን እና መታወቂያቸውን /ውክልና/ በመያዝ ን/ላ/ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ጀርመን አደባባይ ምስራቀ ፀሀይ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን አጠገብ በሚገኘው ሮያል ሴራሚክ ግቢ ውስጥ መጎብኘት ይችላሉ።
7. ድርጅቱ የተሸለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተከበረ ነው።
ለማንኛውም ተጨማሪ ማብራሪያ
በስልክ ቁጥር 0911 523 393 / 0940 347 034ይደውሉ
ኬ ኤ ኤም ኃ/ የተ /የግል ማህበር
አዲስ አበባ
ለሽያጭ የቀረቡ ተሽከርካሪዎች ዝርዝር መግለጫ
| ተ/ቁ | ሰሌዳ ቁጥር | የተሸከርካሪ ዓይነት | የተሰራበት ሀገር | የተሸ/ሞዴል | ተሰራበት ዘመን | የሻንሲ ቁጥር | የሞተር ቁጥር | የመጫን አቅም | 
| 1 | አ.አ-3-A68477 | አውቶሞቢል | JAPAN | GH-SCP10-AHPMNK | 1999 | SCP10-3131200 | 1SZ-0221288 | 4 ሰው | 
| 2 | አ.አ-3-A51232 | አውቶሞቢል | JAPAN | CBA-SCP10-AHPNK-D | 2004 | SCP10-0458615 | 1SZ-1207989 | 4 ሰው | 
| 3 | አ.አ-3-A47701 | አውቶሞቢል | JAPAN | GH-SCP10-AHPNK-D | 2001 | SCP-3129187 | 1SZ-0218384 | 4 ሰው | 
| 4 | አ.አ-3-37967 | ሱዙኪ | JAPAN | JID54V | 2006 | JSAJTD54 V00216874 | J2DA-391678 | 4 ሰው | 
| 5 | አ.አ-3-A24831 | ሊፋንፒክአፕ | CHINA | LF1022 | 2014 | LCN1A1E-44E0101097 | LF479Q51* 140700210* | 1 ሰውእና 9 ኩንታል | 
| 6 | አ.አ-3-A28794 | አውቶቡስ / ኮስተር/ | JAPAN | HZB50L-BGMSSV | 2007 | JTGFB 518571021004 | 1HZ-0557214 | 22 ሰው | 
| 7 | አ.አ-3-A37242 | አውቶቡስ / ኮስተር/ | JAPAN | HZB50L-BGMSSV | 2001 | JTGFB 518611000993 | 1HZ-03245125 | 22 ሰው | 
| 8 | አ.አ-3-A19652 | አይሱዙ | JAPAN | NPR71 | 2015 | JAMKP 34H3F7P08176 | 4HG1-313195 | 2 ሰውእና 35 ኩንታል | 
| 9 | አ.አ-3-A02202 | አይሱዙ | JAPAN | NPR71 | 2013 | JAMKP 34H7D7P09697 | 4HG1-089487 | 2ሰው እና 23.6 ኩንታል |