በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 08 ፋይናንስ ፅ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 08 ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት በተለያዩ ጊዚያት በደንብ ማስከበር የተወረሱ ንብረቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 25, 2025)

ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below. 

የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ 001/2018

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 08 ፋይናንስ ፅ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 08 ደንብ ማስከበር ጽ/ቤት በተለያዩ ጊዚያት በደንብ ማስከበር የተወረሱ ንብረቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥን ይፈልጋል።

ስለሆነም –

1. በዘርፉ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የዘመኑን ግብር የከፈሉ የታክስ መለያ ቁጥር ቲን ሰርተፍኬት ያላቸው መሆናቸውን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።

2. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና CPO – 50,000.00/ሃምሳ ሺህ ብር ብቻ/ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 08 ፋይናንስ ፅ/ቤት ስም ማሠራት አለባቸው።

3. ተጫራቾች ሰነዱን የማይመለስ ብር 300.00 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።

4. በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ከሆነ ከአደራጃቸው አካል ማስረጃ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።

5. ተጫራቾች ንብረቱ ባለበት ቦታ የሚታይ ሲሆን ማየት የምትፈልጉ ተወዳዳሪዎች በደንብ ማስከበር ንብረት ክፍል ማየት ይቻላል።

6. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።

7.የጨረታ ሳጥኑ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሽጎ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።

8. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨ ረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የንብረቱ ጠቅላላ ዋጋ ከዚህ በታች ባለው ሰንጠረዥ ይሞላ።
አድራሻ፡- መርካቶ ምዕራብ ሆቴል ፊትለፊት ሀገር ውስጥ ገቢዎች ህንፃ 1ኛ ፎቅ

ስልክ ቁጥር፡-011 275 9950

በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የወረዳ 08 ፋይናንስ ፅ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *