መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


2merkato.com(Oct 25, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 118

መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል!

ተሸከርካሪዎቹን ለመግዛት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች አዲስ አበባ ከተማ፣ ለሚ ኩራ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 03 (በተለምዶ አያት ኮንዶሚኒየም፣ ከጠበል መድኃኔ ዓለም ቤተክርስቲያን) ፊት ለፊት በሚገኘው በማዕከሉ ዋና መሥሪያ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ከጥቅምት 15 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥቅምት 29 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ በመምጣት ለጨረታው የተዘጋጁትን ተሸከርካሪዎች በአካል መመልከት ይችላል፡፡

ተጫራቾች፡

  • የጨረታ ሰነድ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፣
  • የጨረታ ሰነዱ በማዕከሉ ቅጥር ግቢ ውስጥ ለሽያጭ የተዘጋጁትን ተሸከርካሪዎች ዝርዝር የያዘ ሲሆን እየተዘዋወሩ ከተመለከቱ በኋላ ለመግዛት የሚወስኑትን ተሸከርካሪ ይለያሉ፣ ስሙንና የመለያ ቁጥሩን ይይዛሉ፡፡ 
  • ለእያንዳንዱ ተሸከርካሪ የጨረታ ማስከበሪያ (ማስያዣ) የመነሻውን ዋጋ 10% ነው፡፡
  • ተጫራቾት የሚገዙበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ፎርም ላይ በመሙላት እና የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ ከተረጋገጠ ሲፒኦ ጋር አያይዘውና በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ እስከ ጥቅምት 29 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 (አራት ሰዓት ተኩል) ድረስ ማስገባት ይችላሉ፡፡
  • ጨረታው ጥቅምት 29 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 5፡00 ሰዓት በማዕከሉ የስብሰባ አዳራሽ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

ማዕከሉ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ ማብራሪ በስልክ ቁጥር 0936919191 ወይም 0975264159 መጠየቅ ይቻላል፡፡

መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *