Your cart is currently empty!
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የገላን ጉራ ቁ.2 ቅድመ አንደኛ፤ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት የተለያዩ ዕቃዎችን ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 26, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 01/2018
በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የገላን ጉራ ቁ.2 ቅድመ አንደኛ፤ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ህጋዊ ተጫራቾችን አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት የምትችሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
- ሎት 1 የመምህራንና የአስተዳደር ሠራተኞች የደንብ ልብስ እና የስፖርት መምህራን ትጥቆች ብር 30,865.00
- ሎት 2 የትምህርት አላቂ እቃዎች ብር 21,170.00
- ሎት 3 የፅዳት እቃዎች እና ሌሎች አላቂ እቃዎች ብር 22,350.00
- ሎት 4 አላቂ የቢሮ እቃዎች ብር 11,738.00
- ሎት 5 ኮንፒውተሮች እና ፈርኒቸሮች ብር 73,031.00
- ሎት 6 ልዩ ልዩ አላቂ የፅህፈትና የትምህርት መሳሪያዎች ብር 7,200.00
- የላብራቶሪ እቃዎች ብር 4,000.00
ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ዘርፍ በየሎቱ የተጠየቀውን የብር መጠን በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው። ተጫራቾች በተሰማሩበት የሥራ መስክ የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው የታደሰ የንግድ ፍቃድ ማቅረብ የሚችሉ የመንግሥት የግዥ ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የተሟላ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ
ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በሰነዱ ላይ ባለው የዋጋ መሙያ በመሙላት በታሸገ ፖስታ ኦሪጅናል እና ኮፒ ማስገባት ይኖርባቸዋል አሸናፊ ተጫራቾች ማሸነፋቸው በተገለፀበት በ 5 /አምስት/ ተከታታይ የሥራ ቀን ውስጥ ውል መፈፀምና ባለፉበት ሎት 10% ውል ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
ተጫራቾች ከላይ የተዘረዘሩትን እቃዎች የያዘ ሰነድ የማይመለስ ብር 250 /ሁለት መቶ ሀምሳ ብር ብቻ/ በመክፈል ጨረታውን ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ መግዛት ይችላሉ።
ከገዙት የጨረታ ሰነድ ውጪ ተሞልቶ የሚመጣ ሰነድ ተቀባይነት የለውም ጨረታው በ11ኛው ቀን 3፡30 ይታሸግና 4፡00 ሰአት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተቋሙ ፋይናንስ ቢሮ ይከፈታል። 11ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ የሥራ ቀኑን ጠብቆ ይከፈታል።
ውድድሩ ይፋ ከሆነበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5/ አምስት/የሥራ ቀናት ውስጥ በጨረታ ያለው ቅሬታ ማቅረብ ይችላሉ።
ተጫራቾች በሚወዳደሩበት እቃ ናሙና ማቅረብ ግዴታ አለባቸው። አሸናፊዎች ያለፉበትን እቃዎች በ7 /ሰባት/ ቀናት ለንብረት ክፍል ማስገባት ይሮርባቸዋል።
ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ጥቀቃቅን እና አነስተኛ ደብዳቤ ይዘው የሚቀርቡ ተጫራቾች በሀገር ውስጥ ምርት ላይ ማስረጃ የሚያቀርቡ ከሆነ ብቻ ልዩ አስተያየት ይደረግበታል። እራሱ በአምራችነት የተሳተፈበት ከሆነ ብቻ ልዩ አስተያየት ይደረግበታል።
ለተጨማሪ መረጃ አድራሻ ገላን ጉራ ከኮዬ ፈቼ መንገድ በተለምዶ አስራ ስድስት ዝቅ ብሎ
- ማሳሰቢያ፡– ለሁሉም እቃዎች ናሙና መቅረብ ግዴታ ነው
- ስልክ ቁጥር፡– 0950269206/0950268656
የገላን ጉራ ቅድመ አንደኛ፤ አንደኛና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት