Your cart is currently empty!
የዳቦ መጋገሪያና ማኮፈሻ ማሽኖች፣ የዳቦ መቁረጫ፣ የአሳና የስጋ ፍሪጅ እና የችዝ መቁረጫ የመሳሰሉት ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
Addis Zemen(Jan 23, 2026)
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት ሰብለወርቅ ጡሜቦ እና የፍ/ባለዕዳ ፐርፕዝ ብላክ ኢት ኤች ትሬዲግ አ/ማ መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌደራል መጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በመ/ቁጥር/318188 በ05/02/2017 ዓ/ም በሰጠው ፍርድ እና በኮ/መ/ቁ/321320 በ6/10/2017 ዓ/ም በ26/03/2018 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 06 ክልል ውስጥ የሚገኝ የተለያዩ ፍርድ ያረፈባቸው የዳቦ መጋገሪያና ማኮፈሻ ማሽኖች፤ የዳቦ መቁረጫ ፤የአሳና የስጋ ፍሪጅ፤ የችዝ መቁረጫ የመሳሰሉት የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር ንብረቶች 625,000 (ስድስት መቶ ሀያ አምስት ሺህ ብር) ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ የካቲት 9 ቀን 2018 ዓ/ም በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 8፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል።
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌደራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ጽ/ቤት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፓርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ው አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚመጣ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ አሸናፊ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ጽ ቤት ስም CPO አሰርቶ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት በጨረታ አሸናፊ የሆነ በጨረታ ያሸነፈበትን ገንዘብ ገቢ ሳይደረግ ቀርቶ በቀጣይ ጨረታ ተደርጎ ጨረታው ከበፊቱ ጨረታው ቀንሶ ከተሸጠ ገዥው በልዩነት ተጠያቂ እንደሚሆን የፍ/አፈ/ጽ/ቤት ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን።
የፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈፃፀም ጽ/ቤት