ኦሮሚያ ባንክ ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘዉን ንብረቶች ባሉበት በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Reporter(Jan 25, 2026)

የሐራጅ ማስታወቂያ

ኦሮሚያ ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90 216/92 እና 1147/2011 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ለሰጠው ብድር በዋስትና የያዘዉን በሰንጠረዡ ላይ የተዘረዘሩትን ንብረቶች ባሉበት በግልጽ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል::

.

የተበዳሪው ስም

የንብረት አስያዥ ስም

ለጨረታ የቀረበው ንብረት ዓይነት

አበዳሪው ቅርንጫፍ

ንብረቱ የሚገኝበት አድራሻና የቦታ ስፋት

የጨረታ መነሻ ዋጋ

የጨረታዉ ቀን፣ ሰዓት እና ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ

ጨረታው የወጣው

ከተማ፣ //ወረዳ/ ቀበሌ

የባለቤትነት መረጋገጫ ቁጥር

የቦታ ስፋት በካ./ሄክ

1

አቶ ካህሳይ ካሳሁን /እየሱስ

.ኤፍ ላይፍ ትሬዲንግ /የተ/የግ/ ማህበር

የአግሮኢንዱስትሪ ህንጻ እና የወተትና የወተት ተዋዕፆ ማቀነባበሪያ ማሽን

አፍሪካ ጎዳና

ኦሮሚያ ክልል፣ ሱሉልታ ከተማ፣ቀበሌ 01

SUL/731/10

2000

14,146,024.74

የካቲት 17 ቀን 2018 . 400-500 ዋና መስሪያ ቤት

ለመጀመሪያ ጊዜ

1. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጨረታውን መነሻ ዋጋ 25% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ/.. በኦሮሚያ ባንክ ስም አሰርተው ጨረታው በሚካሄድበት ዕለት ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል:: በጨረታው ከፍተኛ ዋጋ ላልሰጡ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ወዲያዉኑ ይመለስላቸዋል::

2. ተራ ቁጥር 1 ንብረቶች ጨረታው በሰንጠረዡ ላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት ቦሌ መንገድ ኦሎምፒያ አካባቢ አምራን ሆቴል ጎን የኦሮሚያ ባንክ ምክትል ቺፍ ኦፊሰር ህግ አገልግሎት ቢሮ የሚገኝበት ናትሩት ሀውስ (ህንፃ) 9 ፎቅ ላይ የሚገኝ የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ባለዕዳዎቹ ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው እና ታዛቢዎች በተገኙበት ይካሄዳል:: ባለ ዕዳዎቹ ባይገኙም ጨረታው ይካሄዳል::

3. የተጨራቾች ምዝገባ ከሐራጅ መዝግያ ስዓት 5 ደቅቃ በፊት ይጠናቀቃል:: የጨረታ መጠናቀቂያ ስዓት ድረስ ከፍተኛ ዋጋ የሰጠ ተጫራች ካልተለየ አስኪለይ ደረስ ጨረታው የሚቀጥል ይሆናል:: በጨረታው ከፍተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ማሸነፉን የሚገልጽ ደብዳቤ ከባንኩ ህግ አገልግሎት ሲደርሰው ብቻ አሸናፊ ይባላል::

4. ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች አሸናፊ መሆኑ በጽሁፍ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ዋጋ 15 ቀን ውስጥ ለባንኩ አጠቃሎ ገቢ ማድረግ ይኖርበታል:: በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ገቢ የማያደርግ የጨረታ አሸናፊ ያስያዘው ሲፒኦ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል:: በተጨማሪም ንብረቱ በድጋሚ ለሐራጅ ሲቀርብ ለሚፈጠረው ልዩነት ይጠየቃል::

5. በባንኩ ብድር ፖሊሲ መሰረት የሚፈለገውን ማስረጃ አሟልቶ ለቀረበ የጨረታ አሸናፊ ባንኩ ብድር ሊያመቻች ይችላል::

6. ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ንብረቱን በማስተላለፍ ሂደት ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች ግብር፣ የሊዝ ክፍያ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የስም ማዘወሪያ እና ማናቸዉም ከጨረታው ጋር በተገናኘ መንግስት የሚጠይቀው ክፍያ ይከፍላል:: ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይጽፋል::

7. ውዝፍ የሊዝ ክፍያን በተመለከተ ከእዳ ተመላሽ ብር ካለ ከተመላሽ ብር ላይ የሚከፈል ሲሆን ተመላሽ ብር ከሌለ ግን የንብረቱ ጨረታ አሸናፊ ውዝፍ የሊዝ ክፍያን ሙሉ በሙሉ የሚከፍል ይሆናል::

8. ተጨራቾች ለጨረታ የቀረቡትን ንብረቶች በስራ ሰዓት ፕሮግራም አስይዞ ለመጎብኘት ይችላሉ::

9. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 557 1372 እና ወይም 251 91 97 49 020 ዋና /ቤት ሕግ አገልግሎት፣ ለተራ .1 0115-58-52-78 / 58-63-87 ኦሮሚያ ባንክ አፍሪካ ጎዳና ቅርንጫፍ ደውለው መጠየቅ ይቻላል::

10. ባንኩ ጨረታውን በማንኛውም ጊዜ በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

ኦሮሚያ ባንክ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *