በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በተለያዩ ጊዜያት የጉምሩክ ሥነሥርዓት ባለመፈጸሙ ምክንያት እና በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ሞባይሎች፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫዎችና፣ ጌጣጌጥ እና አካላት፣ አልባሳት፣ ጫማዎች፣ የብር ጌጣጌጥ ፕላትኒየሚ፣ ጊርቦክስ የመኪና ሞተር እና ሌሎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ እና በሃራጅ ጨረታ መሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen(Feb 04, 2026)

በጉምሩክ ኮሚሽን የአ/አ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ልዩ ልዩ ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ እና በሃራጅ ጨረታ ቁጥር 56/2018፣ 57/2018፣ 58/2018፣ 59/2018፣ 60/2018፣ 61/2018፣ 62/2018፣ 63/2018 እና 64/2018 የጨረታ ማስታወቂያ

በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በተለያዩ ጊዜያት የጉምሩክ ሥነሥርዓት ባለመፈጸሙ ምክንያት እና በህገ ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክስና የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣ ሞባይሎች፣ የተሸከርካሪ መለዋወጫዎችና፣ ጌጣጌጥ እና አካላት፣ አልባሳት፣ ጫማዎች፣ የብርጌጣጌጥ ፕላትኒየሚ፣ ጊርቦክስ የመኪና ሞተር እና ሌሎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ እና በሃራጅ ጨረታ ቁጥር 56/2018 በቀን 02/6/2018 ዓ.ም ጨረታ ቁጥር 57/2018 በቀን 05/6/2018 ዓ.ም ጨረታ ቁጥር 58/2018 በቀን 09/6/2018 ዓ.ም ጨረታ ቁጥር 59/2018 በቀን 12/6/2008 ዓ.ም ጨረታ ቁጥር 60/2018 በቀን 16/6/2018 ዓ.ም፣ ጨረታ ቁጥር 61/2018 በቀን 19/6/2018 ዓ.ም ጨረታ ቁጥር 62/2018 በቀን 23/6/2018 ዓ ም፣ ጨረታ ቁጥር 63/2018 በቀን 26/6/2018 ዓ.ም እና ጨረታ ቁጥር 64/2018 በቀን 30/6/2018 ዓም በመሆኑ የቀጣይ 2018 በጀት ዓመት ዕቅድ በተፈለገው መጠን ለማሳካት ለሁሉም ተደራሽነት ባለው መልኩ በጋዜጣ ማስታወቂያ እንዲወጣልን እየጠየቅን ዝርዝር መረጃ ከዚህ በታች በተራ ቁጥር 1-14 እንገልፃለን።

በመሆኑም

1. በቅጽ/ቤቱ ለሚካሄደው ጨረታ ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት እና የዘመኑን ግብር የተከፈለ ለመሆኑ ከግብር ሰብሳቢ መስሪያ ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።

2. ማንኛውም የግልጽ ጨረታ ተጫራች ጨረታው አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ የጨረታውን ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡00-6:00 ከሰዓት በኋላ ከ7፡00 -11፡00 እንዲሁም ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00-6፡00 ሰዓት የማይመለስ ብር 100.00 /አንድ መቶ/ በመክፈል ከአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩከ ቅጽ ቤት ገርጂ ጉምሩከ መጋዘን ቅጥር ግቢ የውርስ ዕቃዎች አወጋገድ ቡድን በመምጣት የጨረታ ሰነድ መግዛት ይችላል።

3. በግልጽ ጨረታ ለመሳተፍ ተጫራቾች ለሚወዳደሩባቸው ዕቃዎች የሰጡትን ዋጋ አምስት በመቶ (5%) This (CPO) CUSTOMS COMMISSION ADDIS ABABA AIRPORT GUSTOM BRANCH OFFICE ስም ማሰራት ይኖርባቸዋል።

4. ተጫራቾች የዕቃዎቹን ናሙና በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ካርጎ መዘን እና ገርጂ መጋዘን እስከ የካቲት 02/2018 ዓ/ም የካቲት 05 /2018 ዓ.ም፣ የካቲት 09/2018 ዓ ም የካቲት 12/2018 ዓ.ም፤ የካቲት 16/2018 ዓ ም የካቲት 19/2018ዓ/ም የካቲት 23/2018ዓ.ም የካቲት 26/2018 ዓ.ም እና የካቲት 30/2018 ዓ.ም ከቀኑ በ8፡00 ተዘግቶ በዛው ቀን በ8፡15 የሚከፈት ይሆናል።

5. በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ለጨረታው የሚሰጡትን ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዘው በቀረቡት ቅጾች መሠረት ለመረጡት የዕቃዎች ኮድ የተሰጠ ዋጋ፣ የተጫራቾች ስም አድራሻ ፣ ፊርማና የጨረታ ማስከበሪያ ሲቲ ኦ(CPO) እና ከላይ በተቁ 1 የተገለጹትን ሰነዶች ኮፒ በታሸገ ኢንቨሎፕ ላይ በመፈረም አዲስ አበባ ኤርፖርት ጉቅ ጽ/ቤት ገርጂ የውርስ ዕቃዎች አወጋገድ ቡድን ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

6. ማንኛውም ተጫራች ጨረታ ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነዱ የሰጠውን መግዣ ዋጋና መግለጫ መለወጥና ማሻሻል አይችልም።

7. ማንኛውም ተጫራች የሰጠውን የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ግምገማ ተጠናቆ የጨረታው ውጤትአስከሚታወቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል።

8. የጨረታው አሸናፊዎች ጨረታውን ስለማሸነፋቸው ከተገለፀበት ጊዜ ጀምሮ በ05(አምስት) ቀናት ውስጥ ያሸነፉትን ዕቃ ዋጋ ቢ በማድረግ ዕውን መረከብ አለባቸው።

9. ከላይ በተቁ 8 በተገለጹት ቀናት ውስጥ ከፍያውን ገቢ ያላደረገ እና ንብረቱን ተረክቦ ያልወሰደ ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ (CPO) ገቢ ሆኖ ዕው በድጋሚ ለሽያጭ ይቀርባል።

10. በተራ ቁጥር 01–09 የተገለጸው እንደተጠበቀ ሆኖ በተጨማሪም በሃራጅ ጨረታ ቁጥር 56/2018 በቀን 02/06/2018 ዓ.ም የጨረታ ቁጥር 57/2018 በቀን 05/6/2018 ዓ.ም ጨረታ ቁጥር 58/2018 በቀን 09/6/2018 ዓም ጨረታ ቁጥር 59/2018 በቀን 12/6/2018 ዓም ጨረታ ቁጥር 60/2018 በቀን 16/6/2018 ዓ.ም ጨረታ ቁጥር 61/2018 በቀን 19/6/2018 ዓ.ም ጨረታ ቁጥር 62/2018 በቀን 23/6/2018 ዓ.ም. ጨረታ ቁጥር 63/2018 በቀን 26/6/2018 ዓ.ም እና ጨረታ ቁጥር 64/2018 በቀን 30/6/2018 ዓም ከጠዋቱ በ4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙት የምናካሄድ መሆኑን በዚህ አጋጣሚ እያሳወቅን፣ የዕቃዎችን ናሙና በአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ገርጂ እና ካርጎ ውርስ መዘን በመገኘት መመልከት ይቻላል።

11. በሃራጅ ጨረታ የሚወዳደሩ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00 መቶ ሺህ ለየዘርፉ CUSTOMS COMMISSION ADDIS ABABA AIRPORT CUSTOM BRANCH OFFICE ስም ማስያዘ ይኖርባቸዋል።

12. ለጨረታ የቀረቡት የዕቃዎች ዋጋ ከቫት በፊት የተሰጠ መሆኑን እናሳውቃለን።

13. ለጨረታ የቀረቡት ዕቃዎች በተናጠል ሳይሆን ለጨረታ ሰነዱ በተሰጠ ኮድ ቁጥር ብቻ የሚሸጥ መሆኑን እናሳውቃለን።

14. ቅ/ጽ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ ቦሌ ኤርፖርት በስልክ ቁጥር 0116684537 እና 0116684193 ደውሎ ይጠይቁ።

ጉምሩክ ኮሚሽን የአዲስ አበባ ኤርፖርት ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት