በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የፌዴራል መንግስት ህንጻዎች ግንባታ ፕሮጀክት ጽህፈት ቤት በ2018 በጀት አመት አገልግሎት ላይ የሚውሉ የተለያዩ የግንባታ እቃዎችን በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen(Feb 06, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ጨፌ.መ.ህ.ግ.ፕ.ጽ/ቤት 01/2018

በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የፌዴራል መንግስት ህንጻዎች ግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት በ2018 በጀት አመት አገልግሎት ላይ የሚውሉ የተለያዩ የግንባታ እቃዎችን በብሄራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም በጨረታ መወዳደር የሚፈልግ ማንኛው ህጋዊ ተጫራች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርበታል፡፡

  • ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ዋጋ ሞልተው ሲመልሱ የጨረታውን መነሻ ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ (cpo) በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  • ተጫራቾች ከጨረታው ቀን በፊት ንብረቶቹ አራት ኪሎ በሚገኘው የግንባታ ሳይት ላይ በሚገኙበት ቦታ ቀርበው ማየት ይችላሉ፡፡
  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያውን ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው በአንድ ላይ በማጠቃለል አስተማማኝ በሆነ ማጣበቂያ በታሸገ ፖስታ በማድረግ የተወዳዳሪ ስምና አድራሻ በመጻፍ ማህተም ወይም ፊርማ በማድረግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  • ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በስራ ሰዓት ሶስት መቶ (300) ብር በመክፈል ከፌዴራል መንግስት ህንጻዎች ግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት ግዥና ስራ አመራር ዳይሬክቶሬት በመቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
  • ተጫራቾች ጨረታው ከወጣበት ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት በስራ ሰዓት ፕሮጀክት ጽ/ ቤቱ ግዥና ንብረት ስራ አመራር ዳይሬክቶሬት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት አየር ላይ ቆይቶ በ16ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዕለቱ 8፡30 ሰዓት ላይ በግዥና ንብረት ሥራ አመራር ዳይሬክቶሬት ቢሮ ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ይሆናል፤ -የመከፈቻው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የህዝብ በዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት የሚታሸግና የሚከፈት ይሆናል፡፡
  • ተጫራቾች በራሳቸው ፈቃድ ጨረታው በሚከፈትበት ሰዓት ባይገኙ የጨረታውን መከፈት የማያስተጓግል ከመሆኑም በተጨማሪ በጨረታው ሂደት ለተላለፈ ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡
  • ጨረታውን ያሸነፈ ተጫራች ያሸነፈበትን ዋጋ በ15 ቀን ውስጥ ለፕሮጀክት ጽ/ቤቱ ገቢ ማድረግ ይኖርበታል፡፡ በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ገቢ የማያደርጉ ተጫራቾች ጨረታው ተሰርዞ የጨረታ ማስከበሪያ ተወርሶ ለመንግስት ገቢ ይደረጋል፡፡
  • አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ተወዳድረው ያሸነፉትን ዕቃ በራሳቸው የማጓጓዣ ወጪ አራት ኪሎ በሚገኘው የጠቅላይ ፍርድ ቤት የህንጻ ግንባታ ሳይት ውስጥ ከሚገኙ መጋዘኖች ወጪ በማድረግ በ5 ቀናት ውስጥ መውሰድ ይኖርበታል፡፡
  • ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግ እንዲሁም ከጨረታ ራሳቸውን ማግለል አይችሉም፡፡
  • የፕሮጀክት ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ አድራሻ – ቦሌ መንገድ ሀንሰም ህንጻ ላይ 5ኛ ፎቅ የቢሮ ቁጥር 502

ስልክ ቁጥር፦ 011 5 58 12 28
በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የፌዴራል መንግሥት ሕንፃዎች ግንባታ ፕሮጀክት ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *