Your cart is currently empty!
በአራዳ ክፍለ ከተማ የወረዳ 6 አስተዳደር ጽህፈት ቤት አላቂ የፅዳት እቃዎች፣ የመኪና ኪራይ፣ የጉልበት/የጭነት አገልግሎት በ2ኛው ዙር ግልፅ ጨረታ አወዳድረን መግዛትና ማሠራት እንፈልጋለን
Addis Zemen(Feb 07, 2026)
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር፡-02/2018
በአራዳ ክፍለ ከተማ የወረዳ 6 አስተዳደር ጽ/ቤት በ2018 በጀት ዓመት በ2ኛ ዙር ጨረታ አገልግሎት የሚውሉ አላቂ የፅዳት እቃዎች፣ የመኪና ኪራይ፣ የጉልበት/የጭነት አገልግሎት በ2ኛው ዙር ግልፅ ጨረታ አወዳድረን መግዛትና ማሠራት እንፈልጋለን፡፡
በዚህ መሠረት በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች፡-
1. በዘርፉ አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉና የከፋይነት መለያ ቁጥር ቲን ነበር፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያላቸው፡
2. የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆነና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል፣
3. ተጫራቾች ለጨረታው የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ፋይናንስ ጽ/ቤት መውሰድ ይችላሉ፡፡
4. በተጨማሪ ተጫራቾች በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ባዘጋጀው የእቃና አገልግሎት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ መካተታቸውን መመዝገባቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
5, በጨረታው ላይ ያወጣናቸውን እቃዎች በሙሉ ኦርጅናል እና ጥራቱን የጠበቁ ሆነው ማቅረብ የሚችሉ
6. ተጫራቾች የጨረታ ፖስታ በሚያስገቡበት ጊዜ ለተወዳደሩበት እቃ ሳንኘል የሚያቀርቡ መሆን ይኖርባቸዋል፡
7. ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎችን በራሳቸው ትራንስፖርት መ/ቤቱ ድረስ ማምጣት የሚችሉ።
8. ተጫራቾች በገዙት ሰነድ ብቻ የሚወዳደሩበትን ቫት በመጨመርና በእያንዳንዱ ገጽ ፊርማና የድርጅቱ ማህተም በማኖር በታሸገ ኢንቨሎፕ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣ ቀን ጀምሮ ባሉት 10 /አስር/ ተከታታይ የሥራ ቀናት በተጠቀሰው ቢሮ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርበታል።
9. የጨረታው ማስከበሪያ በእያንዳንዱ ሎት 10000 /አስር ሺብር/ በባንክ በተረጋገጠ CPU ብቻ ማቅረብ አለባቸው።
10. ተጫራቾች የጨረታ አሸናፊ ሆነው የተገኙባቸው እቃዎች አጠቃላይ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ ከጽ/ቤቱ ጋር የግዢ ውል ስምምነት መፈፀም ይኖርበታል።
11. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ11ኛው የሥራ ቀናት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ የጨረታው አከፋፈት ላይ ለመገኘት ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተመሳሳይ ቀን /በ11ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት በወረዳው አስተዳደር አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል።
12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ተጫራቾች ለሳንኘል ለናሙና ማቅረቢያ የሚያገለግላቸውን በተጫራቹ ድርጅት ቅጽ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
አድራሻ፡- የካቲት 12 ሆስፒታል ጀርባ በሚገኘው ፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት መንገድ ይዞ ከኢትዮጵያ ዓይነ ስውራን ማኅበር ፊት ለፊት በሚገኘው በአራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 06 አስተዳደር
ስልክ ቁጥር፡- 0111 262 899/0111 580 697
በአራዳ ክፍለ ከተማ የወረዳ 06 አስተዳደር ፋይናንስ ጽ/ቤት