በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጅታል የመንግስት አገልግሎት ግዥ ዳይሬክቶሬት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ዕቃ ወይም አገልግሎቱን መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Feb 07, 2026)

ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ / የጨረታ ቁጥር 001/2018 .

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጅታል የመንግስት አገልግሎት ግዥ ዳይሬክቶሬት ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ላይ ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ዕቃ ወይም አገልግሎቱን መግዛት ይፈልጋል፡፡

ሎት ቁጥር

የሚገዛው ዕቃ አገልግሎት

የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ (CPO)

ሎት 1

አላቂ የጽህፈት መሳሪያ

7,000.00 (ሰባት ሺህ ብር)

ሎት 2

አላቂ የጽዳት እቃዎች

4,000.00 (አራት ሺህ ብር)

ሎት 3

የመኪና እቃዎች

2,000.00 (ሁለት ሺህ ብር)

ሎት 4

የሠራተኞች ደንብ ልብስ

10,000.00 (አስር ሺህ ብር)

ሎት 5

ቋሚ የቢሮ እቃዎች

15,000.00 (አስራ አምስት ሺህ ብር)

ሎት 6

የህትመት እቃዎች

2,000.00 ( ሁለት ሺህ ብር)

ሎት 7

የአገልግሎት ግዥ

10,000.00 (አስር ሺህ ብር)

በጨረታው መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ማሟላት ባቸው፡

1. በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፤

2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ እና ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤

3. የተጨማሪ እሴት ታክስ/የቫት/ ተመዝጋቢ መሆናቸውን ማቅረብ የሚችሉ፤

4. የአቅራቢነት ሰርተፊኬት ያላቸው እና የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር/ Tin No/ ያላቸው፤

5. የጨረታ ሰነዱን ኮፒና ኦርጂናል ብሎ በመለየት በፖስታ አሽገው ሲመጡ (CPO) ውን እና ተያያዥ መረጃዎች ደግሞ የጨረታ ሰነድ ኦርጅናል ባለበት ፖስታ ውስጥ ማስገባትና በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ሎት ለየብቻ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡

6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለመግዛት የሚችሉት ጋዜጣው ከሚወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ይሆናል፡፡

7. ማንኛውም ተጫራች ከተራ ቁጥር 1 እስከ 6 የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ህጋዊ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት አራዳ ክፍለ ከተማ አዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጅታል የመንግስት አገልግሎት ዋና /ቤት የግዥ ዳይሮክቶሬት 6 ፎቅ ቢሮ ቁጥር የማይመለስ 250ብር/ ሁለት መቶ ሃምሳ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡

8. አሸናፊው ድርጅት ጥራቱን የጠበቀ ዕቃ/አገልግሎት ካላቀረበ በራሱ ወጪ የመለወጥ ግዴታ አለበት፡፡

9. /ቤቱ ካቀረበው ሰነድ ውጪ በሌላ ሰነድ በአማራጭነት ማቅረብ አይቻልም፡፡ ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ ቴክኒካል ኦርጅናል እና ኮፒውን እንዲሁም ፋይናንሽያል ኦርጅናል እና ኮፒ ለየብቻ 4 በፖስታ አሽገው የድርጅታቸውን ማህተምና ፊርማ በማድረግ ለጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፤

10. ተጨራቾች ለሚጫረቱባቸው ዕቀዎች ናሙና/ሳምፕል/ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፤

11. ተጫራቾች /ቤቱ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ሳይኖርበት በትክክል መሙላት አለባቸው፡፡

12. ጥቃቅንና አነስተኛ ተጫራቾች ለምትጫረቱባቸዉ ዕቃዎች የጨረታ ሰነዱን በነጻ ለመውሰድ፡

. ከደራጃችሁ /ቤት ደብዳቤ ማምጣት አለበት፤

. ሰነዱን በነጻ ለመውሰድ በመመሪያ መሰረት ለምትወደደሩበት ዕቃ አምራች መሆን አለባቸው፤

13. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ አሸናፊው ድርጅት ያሸነፈበትን ዕቃ ወይም አገልግሎት ዝርዝር ላይ የጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ እንዲሁም አሸናፋው የሆነው ድርጅት አሸናፊነቱ እንደተገለፀለት በመ/ቤታችን ቀርቦ ውል መዋዋል አለበት ይህ ባይሆን ግን ለዋስትና ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ገንዘብ ለመንግሰት ገቢ ይሆናል፡፡

14. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎች በተገኙበት ጋዜጣው ከወጣበት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ 11ኛው ቀን ጠዋት 4:00 ሰዓት ታሽጎ ወዲያውኑ 430 ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 11 ቀን የስራ ቀን ካልሆነ ቀጣይ ባለው የሥራ ቀናት በተጠቀሰው ሰዓት የሚከፈት ይሆናል፡፡ /ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው፡፡

ማሳሰቢያ፡ ተጫራቾች ሰነዱን ሊገዙ ሲመጡ ሶፍት ኮፒ (soft copy) ስለሚወስዱ ፍላሽ ይዛችሁ እንድትመጡ እናሣስባለን፡፡

አድራሻ፡ አዲስ አበባ አራዳ /ከተማ አራት ኪሎ መንገድ አዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጅታል የመንግስት አገልግሎት ዋና /ቤት (የድሮ አራዳ ክፍለ ከተማ ጊቢ) 6 ፎቅ ቢሮ ቁጥር

ለበለ መረጃ ስልክ፡0111 619 8594 / 9838.

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አዲስ መሶብ የአንድ ማዕከል ዲጅታል የመንግስት አገልግሎት