Your cart is currently empty!
የሰንዳፋ በኬ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅቱ የማይጠቀምበት የሚያገለግሉ እና የማያገለግሉ ጀኔረተሮች አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Addis Zemen(Feb 11, 2026)
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ
የሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የሰንዳፋ በኬ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅቱ የማይጠቀምበት የሚያገለግሉ እና የማያገለግሉ ጀኔረተሮች አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች በማሟላት መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልጸለን።
የመሥሪያ ቤት አድራሻ በሰንደፋ በኬ ከተማ አስተዳደር ዳሽን ባንክ ፊትለፊት በሰንዳፋ በኬ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት በመቅረብ የማይመለስ ብር 500 (አምስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል የጨረታ ሠነዱን መግዛት የሚቻለው ዘወትር ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ አስር የሥራ ቀናት መሆኑን እናሳውቃለን።
1. ተጫራቾች ሕጋዊ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆናቸውን ቲን ቁጥር ያላቸው አንዲሁም የተጨማሪ ዕሴት ታክስ ተመዝጋቢና ምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
2. የጨረታ ሠነዱን መግዛት የሚቻለው ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30-6፡30 እና ከሰዓት 7፡30-11፡00 ሰዓት ብቻ ነው።
3. የንብረቶቹን ሁኔታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአስር (10) ቀን ዘወትር በሥራ ቀናት ከጠዋቱ 2፡30-6፡30 እና ከሰዓት 7፡30-11፡00 ሰዓት ድረስ ጀኔረተሩ በሚገኝበት ቦታ ማየት ይችላሉ።
4. ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ዋጋ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ አንደኛ (11) ቀን እንድታቀርቡ እናሳውቃለን።
5. ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በአስራ አንደኛ ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ተዘግቶ በዕለቱ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
6. ተጫራቾች ለእያንዳንዱ ጨረታ መነሻ ዋጋ 10% የጨረታ ማስከበሪያ CPO በማዘጋጀትና ዋጋ ማቅረቢያው ኤንቨሎፕ ውስጥ በመክተት ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
7. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር 011 686 0068
የሰንዳፋ በኬ ውሃ እና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት