ደቡብ ወሎ ዞን የወረኢሉ ወረዳ አካባቢና ደን ጥበቃ ጽ/ቤት የባሕርዛፍ ደን አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen(Feb 11, 2026)

የባሕርዛፍ ደ ሽያጭ ማስታወቂያ

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት በደቡብ ወሎ ዞን የወረኢሉ ወረዳ አካባቢና ደን ጥበቃ ጽ/ቤት በወረዳው ስር በሚገኙ ሁለት ቀበሌዎች ሦስት የማኅበረሰብ ደን በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ በሎት አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፤ ለዚህም ሎት1. 013 ቀበሌ ልዩ ስሙ ቱሉደጀላ ሎት2. 014 ቀበሌ ልዩ ስሙ አማኑኤል ሎት 3. 014 ቀበሌ ልዩ ስሙ ጅቡ ማሪያ ሲሆኑ ከላይ በሎት የዘረዘርናቸውን የማኅበረሰብ ደን ለመግዛት የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የዘረዘርናቸውን መስፈርቶች አሟልታችሁ መሳተፍ ትችላላችሁ።

ለዚህም

  1. በአጣና ወይም በጣውላና ግንድላ ንግድ ሥራ የተሰማሩ ተጫራቾች ከሆኑ በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና የግብር ከፋይ ምዝገባ ቲን/ TIN number/ ሰርቲፊኬት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል።
  2. ደኑን ለግል ፍጆታ ጥቅም ላይ ማዋል የሚፈልጉ መንግሥታዊ መ/ቤቶች፤ ከፊል መንግሥታዊ ድርጅቶች፤መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ማህበራትና ግለሰቦች በጨረታው መሳተፍ ይችላሉ
  3. የተዘጋጀውን የመጫረቻ ሰነድ ከወረኢሉ ወረዳ አካባቢና ደን ጥበቃ ጽ/ቤት በነፃ መውሰድ ይችላሉ
  4. በጨረታ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ የበዛበት ከሆነና ፓራፍ ካላደረጉ ከጨረታው ውድቅ ይሆናሉ።
  5. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን የደን አይነት የሞሉትን የጠቅላላ ዋጋ 10% የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ cpo በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና/bank bid bond እንዲሁም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይጠበቅባችኋል።
  6. ተጫራቾች በጨረታው መክፈቻ ቀን በአካል የማይገኙ ከሆነ በራሳቸው ፍቃድ የጨረታ አከፋፈት ሥነ- ሥርዓቱ ላይ እንዳልተገኙ ተቆጥሮ ጨረታው የሚከፈትበትን ሰዓት የማያስተጓጉል ከመሆኑ በተጨማሪ በጨረታው ሂደት በተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ።
  7. የጨረታው አሸናፊ የሆኑት አካል ለደኑ ከሞሉት ጠቅላላ ዋጋ 13% ለወረዳው ገቢዎች ጽ/ቤት የሮያሊቲ ክፍያ መፈጸም አለባቸው።
  8. ለጨረታ የቀረበውን ደንማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች ለዚሁ ሲባል በተዘጋጀው የመጫረቻ ሰነድ ላይበተገለጸው ቦታ በአካል በመገኘት ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 20 ቀናት ማየት ይችላሉ
  9. ተጫራቾች የጨረታ ሃሳባቸውን/ደኑን የሚገዙበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ በመሙላት ሙሉ ስማቸውን እና አድራሻቸውን በመጻፍ በጥንቃቄ በፖስታ በማሸግ በወረኢሉ ወረዳ አካባቢና ደን ጥበቃ ጽ/ቤት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት እስከ 20ኛው ቀን ድረስ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  10. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ20 ተከታታይ ቀናት በአየር ላይቆይቶ ተጫራቾች እንዲሁም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ21 ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ታሸጎ በዚያው ቀን 4፡30 ይከፈታል።

ማሳሰቢያ ፡-

  • መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይንም በሕዝብ በዓላት ቀን ከሆነ ወደፊት ባለ የስራ ቀን ይከፈታል
  • ለበለጠ መረጃ በአካል በመቅረብ ወይንም በ 033 116 0621 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ

ዞን የወረኢሉ ወረዳ አካባቢና ደን ጥበቃ ጽ/ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *