ሪዬስ ኢንጂነሪንግ አክሲዮን ማህበር የተለያዩ ያገለገሉ ማሽነሪዎች በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

ሪዬስ ኢንጂነሪንግ አክሲዮን ማህበር የተለያዩ ያገለገሉ ማሽነሪዎች በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen (Apr 07, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ

ኩባንያችን ሪዬስ ኢንጂነሪንግ አክሲዮን ማህበር ሳሪስ 106 ቅርንጫፍ የሚገኙ፤ ከዚህ በታች በዝርዝር የተገለጹትን

  • ያገለገሉ ማሽነሪዎች፤
  • ትራክተሮች፤
  • የትራክተር ጎማዎች፤
  • የቀላል መኪና ጎማዎች፤
  • የትራከተር ጎማ ቸርኬዎች፤
  • ያገለገለ ከባድ መኪና፤ ተሳቢ፤
  • ያገለገለ የድንች መሰብሰቢያ ማሽን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ስለዚህ ማንኛውም ግለሰብ ወይም ድርጅት ለዚሁ ጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 1000.00 (አንድ ሺህ ብር) ከፍሎ በመግዛት በጨረታው መሳተፍ ይቻላል።

ተጫራቾች ንብረቶቹን ሣሪስ ዋናው መሥሪያ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለአምስት ተከታታይ የሥራ ቀናት ዘወትር ጠዋት 300 እስከ 600 ሰዓት ድረስ በአካል ተገኝተው መመልከት ይችላሉ። ተጫራቾች የሚፈልጉትን ንብረት ለጨረታው ሲባል በተሰጣቸው ካታጎሪ መሠረት ሊገዙ የሚችሉበትን ዋጋ ከተጨማሪ ዕሴት ታክስ (VAT) ጋር በመጨመር ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ፎርም ላይ ብቻ በመሙላትና ለጨረታ ማስከበሪያም ያቀረቡትን ዋጋ 100 ሺህ ብር CPO በማስያዝ የድርጅቱ ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።

ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የሥራ ቀናት በኋላ በሚኖረው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የስብሰባ አዳራሽ ይከፈታል።

ማሳሰቢያ፡

1. የጨረታ አሸናፊዎች በማስታወቂያ ከተገለጸው ቀን አንስቶ በአንድ ሳምንት ጊዜ ውስጥ ያሸነፈበትን ዋጋ ቫትን ጨምሮ በመክፈል እቃዎችን ማንሳት አለባቸው።

2. በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ ክፍያ ፈጽመው እቃዎቹን የማያነሱ ከሆነ ለጨረታ ማስከበሪያው የተያዘው ገንዘብ ወደ ድርጅቱ ገቢ ይደረጋል።

3. የጨረታ ተሸናፊዎች የአሸናፊዎች ዝርዝር ከተገለጸባቸው ቀን ጀምሮ ለጨረታ ያስያዙት CPO ተመላሽ ይደረግላቸዋል።

4. በአንደኛው ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም።

5. የማንሻ ማሸን፤ መኪና፤ ጉልበት ሠራተኛ አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያቀርባል።

6 ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ስልክ ቁጥር 0114 42133

የውስጥ መስመር 208 ወይም 212 ደብረ ዘይት መንገድ (ሳሪስ አካባቢ)

ሪዬስ ኢንጅነሪንግ / /አዲስ አበባ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *