ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ: የጊዜ ገደብ ማራዘሚያ ማስታወቂያ። ለሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዋና መሥሪያ ቤት የህንፃ ኪራይ አገልግሎት የፍላጎት መግለጫ! – test3.diretenders.com

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ: የጊዜ ገደብ ማራዘሚያ ማስታወቂያ። ለሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዋና መሥሪያ ቤት የህንፃ ኪራይ አገልግሎት የፍላጎት መግለጫ!


2merkato.com (Apr 08, 2026)

የጊዜ ገደብ ማራዘሚያ ማስታወቂያ

ለሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዋና መሥሪያ ቤት የህንፃ ኪራይ አገልግሎት የፍላጎት መግለጫ!

ለሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዋና መሥሪያ ቤት የህንፃ ኪራይ አገልግሎት የፍላጎት መግለጫ! ሰነዱ የወጣበት ቀን: ረቡዕ፣ መጋቢት 9 ቀን 2018

ሰነድ ማስገቢያ የመጨረሻ ቀን: ረቡዕ፣ መጋቢት 30 ቀን 2018

መግቢያ

ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ረቡዕ መጋቢት 9 ቀን 2018 ዓ.ም በወጣው የመጀመሪያው የፍላጎት መግለጫ ማስታወቂያ 

መሠረት ሰነዶቻቸውን ላስገቡ የህንፃ ባለቤቶች እና አልሚዎች በሙሉ ላሳዩት ጥረት እና ፍላጎት ምስጋናውን ያቀርባል! 

ተጫራቾች የተሟላ ሰነድ እንዲያቀርቡ ተጨማሪ ጊዜ ለመስጠት እንዲቻል ድርጅቱ የሰነድ ማስገቢያ ጊዜውን ለማራዘም ወስኗል። አዲሱ የሰነድ ማስገቢያ የመጨረሻ ቀን ረቡዕ መጋቢት 30 ቀን 2018 ዓ.ም ሲሆን ቀደም ብለው ሰነዶቻቸውን ያስገቡ ተጫራቾች አስፈላጊ ሆኖ ካገኙት ያቀረቡትን ሰነድ ከልሰው በድጋሚ ማቅረብ የሚችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

መሠረታዊ መስፈርቶች

  • 8,000 – 10,000 ካሬ ሜትር የሚሆን ጠቅላላ የቢሮ ቦታ
  • ለብቻው የሚገኝ ወይም ራሱን የቻለ ለንግድ ተግባር የሚውል ሕንፃ ቢሆን ይመረጣል
  • ደህንነቱ የተጠበቀ እና ለትራንስፖርት አመቺ የሆነ ቦታ ላይ የሚገኝ 

ህንጻው ማሟላት ያለበት ዝርዝር መለኪያዎች

  • በሳፋሪኮም ፍላጎት እና ስታንዳርድ መሰረት የውስጥ ፓርቲሽን መስራት የሚያስችል
  • የማይቆራረጥ የኤሌክትሪክ አቅርቦት ከዝግጁ (Standby) ጀነሬተር ጋር ያሟላ
  • ኬብሊንግ (Structured Cabling) የተዘረጋለት
  • የደህንነት መቆጣጠሪያ ስርዓት እና CCTV ካሜራዎች የተገጠሙለት
  • የእሳት መቆጣጠሪያ ስርዓቶች እና ተገቢ የአደጋ መውጫዎች ያሟላ
  • ብዛት ላለው ሰራተኛ የሚመች የህንጻ ሙቀት መቆጣጠሪያ ስርዓት (HVAC)
  • በቂ የመኪና ማቆሚያ ቦታ ያለው(ለእንግዶች ማቆሚያን ጨምሮ)
  • የዕቃ ማስቀመጫ (store) እና ተያያዝ የአገልግሎት ክፍሎች በበቂ ሁኔታ ያሟላ
  • ተወዳዳሪ ዋጋ ማቅረብ የሚችል
  • የድርጅቱን ብራንድ ለማሳየት ተስማሚ የሆነ የሕንፃ እይታ ያለው
  • የራሱ የሆነ የከርሰ ምድር ውሃ አቅርቦት ያለው ቢሆን ይበልጥ ተመራጭ ይሆናል

ባለንብረቶች ሕንፃውን በሳፋሪኮም የኮርፖሬት፣ የኦፕሬሽን እና ቴክኒክ መስፈርቶች መሰረት ለማስረከብ ፍላጎት እንዳላቸው ማሳየት ይኖርባቸዋል።

መሟላት ያለበት የፍላጎት መግለጫ ሰነዶች

  • የኩባንያ ሰነዶች (ሕጋዊ ከሆነ አካል የተሰጠ የንግድ ፍቃድ፣ የኩባንያ ምዝገባ፣ TIN ሰርተፍኬት፣ የመመስረቻ ሰነድ፣ የሕንፃ ኪራይ ፈቃድ)
  • የንብረቱ ዝርዝር መረጃ እና ቴክኒካዊ መግለጫ
  • የመኪና ማቆሚያ ቦታ አቅም መረጃ
  • የኪራይ ውል ሁኔታዎች እና ለአገልግሎት ዝግጁ የሚሆንበት ጊዜ
  • ለብቻው በሰም የታሸገ የዋጋ ሰነድ (financial proposal) ኤንቨሎፕ

ሰነዱ የሚቀርብበት መንገድ

አገልግሎቱን ለመስጠት ፍላጎት ያላቸው ኩባንያዎች የፍላጎት መግለጫ ሰነዳቸውን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ በሁለት የተለያዩ በሰም በታሸጉ ኤንቨሎፖች በአካል ማቅረብ ይኖርባቸዋል። እነርሱም፤

  • ፖስታ 1 (Envelope 1) – ቴክኒካል ፕሮፖዛል “Technical Proposal – Office Space for Safaricom Ethiopia HQ” ተብሎ መጻፍ ይኖርበታል።
  • ፖስታ 2 (Envelope 2) – የዋጋ (financial) ፕሮፖዛል- “Commercial Proposal – Office Space for Safaricom Ethiopia HQ” ተብሎ መጻፍ  ይኖርበታል።
  • ማስታወሻ፡ የቴክኒካል ፕሮፖዛል (Technical Proposal) በሚከተለው ኢሜይል አድራሻ መላክ ይቻላል፡ Bids@safaricom.et

የፋይናንስ ፕሮፖዛል (Commercial/Financial Proposal) ግን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ (hard copy) ብቻ መቅረብ አለበት። በኢሜይል ወይም በሌላ ማንኛውም መንገድ የሚላክ የዋጋ ፕሮፖዛል ተቀባይነት  የለውም።

የማቅረቢያ አድራሻ

ለሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ዋና መስሪያ ቤት

ስልክ ቁ +251 725 584877

ወሎ ሰፈር፣  አዲስ አበባ

የማቅረቢያ ቀን እና ሰአት 

ከ መጋቢት 9 ቀን 2018 እስከ መጋቢት 30 ቀን 2018፣ 11:00 ሰዓት ድረስ

የስራ ሰዐት ከሰኞ – ቅዳሜ ከ 2:30 ጠዋት – 11:00 ከሰዓት

በቀጣይ የሚከናወኑ ተግባራት

ፍላጎት መግለጫዎች ለሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከደረሱ በኋላ ኩባንያው የሚከተሉትን ተግባራት ያከናውናል፡

  • የተላከውን የፍላጎት መግለጫ ይገመግማል 
  • ከተላኩት የፍላጎት መግለጫዎች ውስጥ ቅድመ መሥፈርቶችን የሚያሟሉትን ይለያል
  • ቅድመ መሥፈርቱን የሚያሟሉ ሕንፃዎች ቴክኒካዊ ግምገማ ያካሂዳል
  • ቴክኒካል መሥፈርቱን የሚያሟሉ ሕንፃ ባለንብረቶች ጋር የዋጋ (financial) ድርድር ይደረጋል
  • ለውል የተመረጠውን ሕንፃ የማሳወቅ ሂደት ይካሄዳል

ማስታወሻ

  • ለቀጣይ ውይይት የሚጋበዙት አቅራቢዎች ዝቅተኛውን መሥፈርት ያሟሉ ብቻ ይሆናሉ 
  • የዋጋ መረጃ በ“Financial Proposal” ኤንቨሎፕ ውስጥ ብቻ መካተት ይኖርብታል። ከዚህ መንገድ 
  • ውጪ የሚቀርቡ ማመልከቻዎች ተቀባይነት አይኖራቸውም።
  • ጨረታውን ለማስገባት የሚደረግ ዝግጅት እንዲሁም ሰነዱን ለማቅረብ የሚወጡ ወጪዎች በሙሉ በተሳታፊዎች የሚሸፈኑ ይሆናል
  • ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ጨረታውንም ሆነ የተጫራቾችን የፍላጎት መግለጫ ወይም የአገልግሎት መነሻ ሐሳብ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው:: ድርጅቱ የሚያሳልፈው ውሳኔ የሚፀና ሲሆን፣ ለተጫራቾች የጨረታውን ውጤት ከማሳወቅ ውጪ ሌሎች ተጨማሪ ዝርዝር ማብራሪያዎች በመስጠት እንዲሳተፍ አይገደድም::
  • ይህ የፍላጎት መግለጫ በቀጥታ ከባለንብረቶች ጋር ለመስራት ብቻ የተዘጋጀ ሲሆን፤ ከኮሚሽን ወኪሎች ወይም አገናኝ አካላት ጋር ውይይትም ሆነ ድርድር ድርጅቱ አያደርግም።
  • ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ለጨረታው የፍላጎት መግለጫ ካቀረቡና በቅድመ መስፈርት ከተመረጡ ተጫራቾች ጋር ምንም ዓይነት ውል አይዋዋልም:: ድርጅቱ ሕጋዊ ስምምነት ውስጥ የሚገባው የቴክኒክና የዋጋ ግምገማ ከተጠናቀቀ እና አሸናፊው ተጫራች ከተለየ እንዲሁም ውል ከታሰረ በኋላ ይሆናል::

Please use the following link for the previous tender  

https://tender.2merkato.com/tenders/69bbb2870a538a2f7b000001 


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *