በአቃ/ቃ/ክ/ከተማ ሳሪስ ጤና ጣቢያ ያገለገሉ የቢሮ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል – test3.diretenders.com

በአቃ/ቃ/ክ/ከተማ ሳሪስ ጤና ጣቢያ ያገለገሉ የቢሮ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen (May 02, 2026)

ያገለገሉ እቃዎች ሽያጭ ጨረታ ቁጥር 03/2018

በአቃ/ቃ/ክ/ከተማ ሳሪስ ጤና ጣቢያ ያገለገሉ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በአቃ/ቃ/ክ/ከ/ወረዳ 6 ልዩ ቦታ ሳሪስ ጤና ጣቢያ አደይ አበባ ሙኒክ ሆቴል ፊት ለፊት የሚገኝ ሲሆን የተለያዩ ያገለገሉ ከ31 አይነት በላይ እቃዎች አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል። እቃዎቹ የሚገኝበት ሳሪስ ጤና ጣቢያ ግቢ ውስጥ ሆኖ የዋጋ መሙያ ሰነድ እና የጨረታ ሳጥን ቢሮ ቁጥር 35 ይገኛል። ማንኛውም ተጫራች ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 ቀናት የጨረታ ሰነዱን ከሳሪስ ጤና ጣቢያ ከፋ ቡድን ቢሮ ቁጥር 35 የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋጋ ማለትም ያገለገሉ የቢሮ እቃዎች ሽያጭ 3000.00 (ሶስት ሺህ ብር) በሲፒኦ (CPO) በአድራሻችን ከጨረታ ሰነድ ጋር በፖስታ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው። የጨረታ ሰነድ ጨረታ ሳጥን ውስጥ ከገባ በኋላ እና አሸናፊው ድርጅት አሸናፊ መሆኑን በደብዳቤ ከተገለፀለት ቀን ጀምሮ ከውድድሩ ቢወጡ የጨረታ ማስከበሪያ ለመንግስት ገቢ ይሆናል። ጨረታው ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን አየር ላይ ውሎ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዛኑ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸቸው ባሉበት ሳሪስ ጤና ጣቢያ ካርድ ክፍል ፊት ለፊት ባለው አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም የጨረታ መክፈት ሂደት በተቀመጠው መሰረት ይካሄዳል። የጨረታ መዝጊያ እና መክፈቻ ቀን ዝግ ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል። ተጫራቾች ከመስሪያ ቤቱ በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ ብቻ የዋጋ ዝርዝር ሞልተው ማቅረብ አለበቸው። አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት ወይም ግለሰብ በጠቅላላ ዋጋ ብልጫ ያለው ብቻ ነው። አሸናፊው ተጫራች ማሸነፉን በደብዳቤ ከተገለፀለት ቀን ጅምሮ በ3 ቀናት ውስጥ ያሸነፈበትን ገንዘብ መስሪያ ቤቱ በሚያዘው የክፍያ አማራጭ ገቢ በማድረግ እቃውን ከቦታው ማንሳት ያለበት ሲሆን ይህ የማይሆን ከሆነ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው ዋስትና የሚወረስ ይሆናል። ይህ ጨረታ የታካሚዎች ካርድ ማስወገድን ስለሚያካትት ማንኛውም አሸናፊው ድርጅትም ሆነ ግለሰብ የታካሚዎችን ካርድሙሉ በሙሉ ሪሳይክል ወይም የሚወገድበት ዘዴ በፋብሪካ ተፍጭቶ ወደ ሌላ አገልግሎትየሚውልመደረጉን ተቋሙ ያዋቀረው ኮሚቴ በቦታው ላይ ሄዶ ሪሳይክል መደረጉን ለማሳየትፈቃደኛ መሆን ግዴታ አለበት። አሸናፊ የሚሆነው ድርጅት/ግለሰብ ጠቅላላ ድምር ብልጫያለው ስለሆነ እቃውን በሙሉ ማንሳት አለበት። መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

አድራሻ፡- አቃ/ቃ/ክ/ከ/ወረዳ 06 ሳሪስ ጤና ጣቢያ 3 ፊት

ለፊት ከሙኒከ ሆቴል አጠገብ ስልክ፡- 0114-70-98-59/0114-70–79–77

በአዲስ አበባ ከተማ ጤና ቢሮ የአቃቂ ቃሊቲ

ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት የሳሪስ ጤና ጣቢያ


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *