Addis Zemen (May 06, 2026)
የዝግ ጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በካፒታል ዕቃ ኪራይ ንግድ ሥራ አዋጅ ቁጥር 103/1998 አንቀጽ 6 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ከተካራይ የተረከበውን ንብረት ባለበት በዝግ ጨረታ ለመሸጥ ይፈልጋል።
|
የተከራዩ ስም |
ጨረታ የሚካሄድበት ቦታ |
የንብረት ዝርዝር
|
ንብረቶቹ የሚገኙበት ቦታ |
የጨረታ መነሻ
|
የጨረታ ደረጃ
|
የጨረታ ቀን እና ሰዓት
|
|
የወንድወሰን አላዛር |
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ነቀምቴ ቅርንጫፍ |
Chemical Sprayer
|
ኦሮሚያ ክልል፣ ምሥራቅ ወለጋ ዞን፣ጎቶ ጊዳ ወረዳ፣ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ነቀምቴ ከተማ |
208,372.50 (ሁለት መቶ ስምንት ሺህ ሦስት መቶ ሰባ ሁለት ከ50/100) |
1ኛ |
ሰኔ 03 ቀን 208 ዓ/ም ከቀኑ በ4፡00 ላይ ጨረታው ይከፈታል።
|
የዝግ ጨረታ መመሪያ ፡-
1. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው እና የሚመለከታቸው የመንግሥት አካላት ተወካዮች በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቀን እና ሰዓት በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ነቀምቴ ቅርንጫፍ ቅጥር ግቢ ውስጥ ይካሄዳል።
2. የዝግ ጨረታው ላይ የሚሳተፍ ማንኛውም አካል (ግለሰብ፣ ተቋሟት ወይም አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ) ለዚሁ ጨረታ የተዘጋጀ ሰነድ ከኢትዮጵያ ልማት ባንክ ነቀምቴ ቅርንጫፍ በመግዛት ንብረቱን የሚገዛበትን ዋጋ፣ ንብረቱን ሊገዛበት የሚፈልግበት ሁኔታ (በጥሬ ገንዘብ ለመግዛት)፣ እና ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን በማያያዝ በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ነቀምቴ ቅርንጫፍ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሰኔ 03 ቀን 2018 ዓ.ም ከጧቱ 3፡30 ድረስ ማስገባት አለባቸው።
3. በጨረታው መሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም አካል (ግለሰብ፣ ተቋሟት ወይም አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዝ) ከቀረጥ ነፃ የመጠቀም ተመሳሳይ መብት ያለው ከሆነ ወይም መንግስት በንብረቶቹ ላይ የሚያስከፍለውን የጉምሩክ ቀረጥ ለመክፈል ፍቃደኛ የሆነ ሁሉ በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡
4. ንብረቱን በጥሬ ገንዘብ መግዛት የሚፈልግ የጨረታው መነሻ ዋጋ ሃያ በመቶ(20%) በባንክ በተረጋገጠ የባንክ ክፍያ ማስያዣ/ሲ.ፒ.ኦ/ ማቅረብ ይኖርበታል
5. በጨረታው ለተሸነፉ ተሳታፊዎች ያስያዙት የባንክ ክፍያ ማስያዣ/ሲ.ፒ.ኦ/ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፣
6. ለዝግ ጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ገንዘብ ላሸናፊው ተጫራች ከጠቅላላው ካሸነፈበት ዋጋ ላይ የሚታሰብለት ሲሆን ነገር ግን አሸናፊዎች በራሳቸው ፈቃድ ጨረታውን የተው ከሆነ ያስያዙት ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል፤
7. ንብረቱን ሙሉ በሙሉ በጥሬ ገንዘብ ለመግዛት ተወዳድሮ ያሸነፈ የጨረታው ተሳታፊ ቀሪውን ገንዘብ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ በመክፈል ንብረቱን ማንሳት ይኖርበታል። በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ ውስጥ አጠቃሎ ገንዘቡን ካልከፈለ የጨረታው አሸናፊነቱ ተሰርዞ ያስያዘው ገንዘብ ሙሉ በሙሉ ለባንኩ ገቢ ይሆናል፣
8. የጨረታው አሸናፊ ንብረቱን ለመግዛት የሚፈልግ ከሆነ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ የሚጠበቅበትን ክፍያ አጠቃሎ በመከፍል የማሽነሪ የእጅ በእጅ ሽያጭ ውል መፈረም ይኖርበታል።
9. አስራ አምስት በመቶ/15%/ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ እና ሌሎች በሕግ የተወሰ ክፍያዎችን፣ የስም ማዛወሪያ ክፍያን ጨምሮ ገዢው ይከፍላል፤
10. ስለ ንብረቱ ዝርዝር እና ተጨማሪ መረጃን በተመለከተ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ነቀምቴ ዲስትሪክት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 057-660-0088 ወይም 057-660-0033 ደውሎ ማነጋገር ይቻላል፡፡ ንብረቱን ለመጎበኘት የሚፈልጉም ካሉ ዲስትሪከቱ ጋ አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ መጐብኘት ይቻላል፤
11. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ነቀምቴ ዲስትሪክት