Reporter (May 10, 2026)
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
ፀደይ ባንክ አ.ማ. ለጃን ሜዳ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግል ማኅበር ለሰጠዉ ብድር በመያዣ የያዘዉን በደብረ ብርሃን ከተማ የካርታ ቁጥር ደብኢፓ /03/00202014 የቦታዉ ስፋት 20000 ካ.ሜ የሆነ የኢንዱስትሪ ሽድ እና ቦታ ለፕሌይ ዉድና ኤምዲኤፍ ማምረቻ አገልግሎት የሚዉል በአዋጅ ቁጥር 97/90 በተሰጠዉ ስልጣን መሰረት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል:: በመሆኑም ተጫራቾች ለጫረታ ከመቅረባቸው በፊት የሚከተሉትን ደምቦች በመገንዘብና ቅድመ ሁኔታዎችን በማሟላት ተጫራቾች እንዲጫረቱ ይጋብዛል::
- የቤቱ የጨረታ መነሻ ዋጋ ተጨማሪ እሴት ታክስን ሳይጨምር ግምቱ 116,435,02015 (አንድ መቶ አስራ ስድስት ሚሊዮን አራት መቶ ሰላሳ አምስት ሺህ ዜሮ ሃያ ብር ከአስራ አምስት ሳንቲም የሆነ
- ተጫራቾች የቤቱን ጨረታ መነሻ ዋጋ ብር ¼ (በጥሬ ገንዘብ ወይም በሲ.ፒ.ኦ) በጸደይ ባንክ አ.ማ ስም በማሰራት ለጨረታ ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርባቸዋል::
- የጨረታዉ አሽናፊ አሸናፊነቱ የሚረጋገጠዉ የጨረታዉ ዉጤት በሚመለከተዉ አካል ጸድቆ በባንኩ ደብዳቤ ሲሰጠዉ ብቻ ይሆናል::
- በጨረታዉ የሚሳተፈዉ በህግ ሰዉነት ያገኘ ከሆነ የድርጅቱ መመስረቻ ጽሁፍ ወይም መተዳደሪያ ደምብ፣ ህጋዊ ሰዉነት ያገኘበት የምዝገባ የምስክር ወረቀት እንዲሁም ህጋዊ ዉክልና ማቅረብ አለበት::
- የጨረታዉ አሸናፊ አሸናፊነቱ በባንኩ በደብዳቤ ከተገለጸለት ቀን ጀምሮ ያሸነፈበትን ጠቅላላ ዋጋ በ10 ቀናት ዉስጥ አጠቃሎ መክፈልና በጨረታ ያሸነፈዉን ንብረት መረከብ ይኖርበታል:: አሸናፊዉ በ10 ቀናት ዉስጥ ገንዘቡን ካልከፈለ ጨረታዉ ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘዉ ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል::
- በጨረታዉ ለተሸነፉ ተጫራጮች ያስያዙት ጥሬ ገንዘብ ወይም ሲ.ፒ.ኦ ይመለስላቸዋል::
- የጨረታ አሸናፊዉ ከሚገዛዉ ንብረት ዋጋ በተጨማሪ ከቤቱ ጋር የተያያዙ ማናቸዉም ለመንግስት የሚከፈሉ ክፍያዎች፡ ግብር፤ ተጨማሪ እሴት ታክስ 15% እና ከስም ዝዉዉሩ ጋር የሚገናኙ ማንኛዉንም ወጭዎች ገዢ ይሸፍናል/ ይከፍላል:: ዉዝፍ የሊዝ ክፍያ ካለ ባንኩ የሚከፍል ሆኖ ለቀረዉና የክፍያ ጊዜዉ ላልደረሰ የሊዝ ክፍያ ገዢ ከሚመለከተዉ የመንግስት አካል ጋር እንዲዋዋል ይደረጋል::
- ተጫራቾች ቤቱን /ድርጅቱን/ በባንኩ አማካኝነት መጎብኘት ወይም ማየት ይችላሉ::
- ከፍ ሲል የተጠቀሰዉን ንብረት ለሚገዛና የባንኩን የብድር ፖሊሲና መመሪያ መመዘኛዎች ለሚያሟላና ፍላጎት ላለዉ ተጫራች በሚሰጠዉ ከፍተኛ ዋጋ ባንኩ እስከ 30% ( ስላላ በመቶ) ብድር ሊያመቻች ይችላል::
- ጨረታዉ የሚካሄደዉ ሰኔ 2/2018 ከጠዋቱ 3.00 ሰዓት እስከ ቀኑ 6.00 ሰዓት በአዲስ አበባ ከተማ በልደታ ክ/ከተማ ልዩ ቦታዉ ሰንጋ ተራ በባንኩ ዋና መ/ቤት 11ኛ ፎቅ ይሆናል::
- ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጫረታዉን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የጠተበቀ ነዉ::
ለተጨማሪ መረጃ፡– ፀደይ ባንክ ዋና መ/ቤት በስ.ቁ +251918779825 ደዉሎ መጠየቅ ይቻላል::