Addis Zemen (May 11, 2026)
የድርድር ጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሻሸመኔ ዲስትሪከት በሊዝ ፋይናንሲንግ አገልግሎት የማሽነሪ ዕቃዎችን በኪራይ ወስደው የነበሩ እና ከዚህ በታች በሰንጠረዥ ውስጥ ስማቸው የተጠቀሰው ተከራይ በሊዝ ውሉ መሰረት የሊዝ ክራይ ክፍያውን ባለመከፈላቸው ምክንያት ባንኩ በአዋጅ ቁጥር 103/1990 እና 807/2005 በተሠጠው ስልጣን መሰረት ከተከራይ መልሶ የተረከበውን የካፒታል ዕቃዎችን በድርድር አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
|
የካፒታል ዕቃ ተከራይ ስም |
የሚሸጠው ንብረት |
ብዛት |
የድርድሩ መነሻ ዋጋ (ብር) |
የሚሸጠው ንብረትና የሚገኝበት ቦታ |
የሚካሄድበት ቦታ ቀን እና ሰዓት |
|
ወ/ሮ አብዲቱ መንግስቱ አግሪካልቸራል መካናይዜሽን አገልግሎት መስጫ |
ትራከተር ብዛት 2 ብራንድ case 1H፣ ሞዴል Max125 አቅም 127HP የስሪት ዘመን 2021 እና 2022 የተመረተበት ሀገር UK ባለ 24 ምጣድ Trailed Offset መከስከሻ/ DiscHarrow/ ብዛት 2 ብራንድ ለ ARZIA የስሪት ዘመን 2022 የተመረተበት ሀገር ጣሊያን ባለ5 ምጣድ ማረሻ Disc Plough; ብዛት 2 ብራንድ OTMA: የስሪት ዘመን 2021 የተመረተበት ሀገር ጣሊያን |
2 |
17,337,150.00
|
በኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት ምዕራብ አርሲ ዞን ሻሸመኔ ከተማ 06 ቀበሌ ጃሎ ሆቴል ፊት ለፊት በሚገኘው የባንኩ ዲስትሪከት ጽ/ቤት |
በዲስትሪክቱ በቅጥር ግቢ ውስጥ ግንቦት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ከ4:00-6:00
|
ማሳሰቢያ
1. ተደራዳሪዎች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 20% (ሃያ በመቶ) የባንክ ክፍያ ማዘዣ (ሲፒኦ) ብቻ በማስያዝ መደራደር ይችላሉ።
2. ተደራዳሪዎች የድርድር ጨረታ ሰነዱን ከኢትዮጰያ ልማት ባንክ ሻሽመኔ ዲስትሪክት በመውሰድ የሚገዙትን የካፒታል ዕቃ እና የሚገዙበትን ዋጋ በመጥቀስ ሌሎች አስፈላጊ የሆኑ መረጃዎችን ጋር በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ግንቦት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ ማስገባት አለባቸው።
3. በጥሬ ገንዘብ አሸናፊ የሆነው ተደራዳሪ ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ጨምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ የድርድር ጨረታው ውጤቱ ይሰረዛል።
4. ሕጋዊ ሰውነት ያላቸው ድርጀቶች በመወከል በድርድር ጨረታ የሚሳተፍ ግለሰብ የተረጋገጠውን የውክልና ስልጣን ይዞ መቅረብ ይኖርበታል
5. ካፒታል ዕቃውን መልሶ መከራየት የሚፈልግ ተደራዳሪ የባንኩን የሊዝ ፋይናንሲንግ መስፈርት ማሟላት እና ንብረቱን የሚከራይበትን ዋጋ፣ ስለቀሪው ኪራይ አከፋፈል ሁኔታ በመጥቀስ በታ ኤንቨሎፕ ማሰገባት ይኖርበታል።
6. አሸናፊው ያስያዘውን ገንዘብ ከግዢው ዋጋ ሲታሰብለት ለተሸነፉ ተደራዳሪዎች ያስያዙት ሲፒኦ ተመላሽ ይደረጋል።
7. የድርድሩ አሸናፊ የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ነጻ መብት ሊኖረው አሊያም በመንግስት የሚፈለገውን ቀረጥ ለመክፈል ይገደዳል።
8. የድርድር ጨረታው አሸናፊ 15% የተጨማሪ እሴት ታክስን ጨምሮ ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎችን እንዲሁም የስም ማዛወሪ ክፍያ ጨምሮ ገዢው ይከፍላል።
9. ዝርዝርና ተጨማሪ መረጃ በተመለከተ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሻሸመኔ ዲስትሪክት መስሪያ ቤት በአካል በመቅረብ ማነጋገር ወይም በስልክ ቁጥር፡- 0911-04-84-79 ላይ መደወል ንብረቱን መጎብኘት የሚፈልግ ተጫራች ከዲስትሪክቱ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በማስያዝ መጎብኘት ይችላሉ።
10. ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሐራጁን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ሻሸመኔ ዲስትሪክት