የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት: የቁም ደን ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ – test3.diretenders.com

የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት: የቁም ደን ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ


Addis Zemen (May 12, 2026)

የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት

የቁም ደን ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር OFWE/BA-05/2018

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ

ፊንፊኔ ደንና ዱር እንስሳት ቅ/ጽ/ቤት ስር ሱባ ሰበታ፤ በረክ፤ ጂባት ገዶ፤ በምሥራቅ ሸዋ ድስትሪከት እና እንጦጦ ጫንጮ ድስትሪክቶች የሚያስተዳድሩት የቁም ባህርዛፍ ደን እንዲሁም በምሥራቅ ሸዋ በማህበራት የሚተዳደር ደን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል። 

ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ

ፊንፊኔ ደንና ዱር እንስሳት ቅ/ጽ/ቤት ስር ሱባ ሰበታ፤ በረክ፤ ምሥራቅ ሸዋ ድስትሪክት እና እንጦጦ ጫንጮ ድስትሪክቶች የሚያስተዳድሩት የቁም ባህርዛፍ ደን እንዲሁም በምሥራቅ ሸዋ ማህበራት የሚተዳደር ደን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም፡-

1. የጊንድላ፣ የአጣና፣ የእንጨት መሰንጠቂያ እና ተዛማጅ ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው ድርጅቶች እና ግለሰቦች እንዲሁም የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ ስለ ጨረታው ዝርዝር ሁኔታ የሚገልፅ የጨረታ ሰነድ ለእያንዳንዳቸው 200/ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ቀበና ሼል /ኦይል ሊቢያ አጠገብ በሚገኘዉ የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት ዋና መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 201 ወይም ጨረታው የወጣበት ፊንፊኔ ደንና ዱር እንስሳት ቅ/ጽ/ቤት በጨረታው መሣተፍ ይችላሉ።

2. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ /የወጣበትን ቀን ጨምሮ/ ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣው ለ15 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆያል።

3. ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ /የወጣበትን ቀን ጨምሮ ለ10 ተከታታይ ቀናት ክፍት ሆኖ ይቆያል።

4. ጨረታው የሚዘጋበት እና የሚከፈትበት ቀንና ሰዓት በጨረታው ሰነድ ውስጥ ይገለጻል።

5. ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid bond) የሚሆን ያቀረቡትን ጠቅላላ ዋጋ 5% በማስላት አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ከሚገኙ ባንኮች በባንክ በተረጋገጠ ደረሰኝ (CPO) ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።

6. ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለተጨማሪ መረጃ፡- WWW.oromiaforest.et  ማግኘት ይችላሉ

በስልክ ቁጥር፡- 011 124 0249 መደወል ይችላሉ

የኦሮሚያ ደንና ዱር እንስሳት ድርጅት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *