Your cart is currently empty!
በደጀን ከተማ ዳሽን ሲሚንቶ ፋብሪካ ቅጥር ጊቢ ያገለገሉ ጎማዎችና በርሜሎች እንዲሁም ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶችን በግልጽ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 19, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ያገለገሉ ልዩ ልዩ ዕቃዎች ሽያጭ የጨረታ ሰነድ
በደጀን ከተማ ዳሽን ሲሚንቶ ፋብሪካ ቅጥር ጊቢ ያገለገሉ ጎማዎችና በርሜሎች እንዲሁም ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶችን በግልጽ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
1. በጨረታ የሚሳተፍ ድርጅት የታደሰ ንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር የከፈለ መሆኑን የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል፤
2. ተጫራቾች አዲስ አበባ ስቴዲዮም ናኒ ሕንፃ ዋናው መስሪያ ቤት 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 10 በአካል ቀርበው የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 100.00 (አንድ መቶ) በዳሽን ሲሚንቶ ፋብሪካ ስም በዳሸን ባንክ የሂሳብ ቁጥር 0674409295011 በማስገባት ያስገቡበትን ደረሰኝ በማቅረብ መውሰድ ይችላሉ፡፡
3. ተጫራች በጨረታው ለሚሳተፍባቸው ለእያንዳንዱ ዕቃዎች ለጨረታ ያቀረቡትን 5% የጨረታ ማስከበሪያ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፤
4. ተጫራቾች የሚገዙትን ዕቃዎች ድርጅቱ ባዘጋጀው የዋጋ ማቅረቢያ ቅፅ የሚገዙበትን ዋጋ በመጥቀስ እንዲሁም ከሲ.ፒ.ኦ ጋር በማካተት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት እስከ አስር ቀን ከቀኑ 4፡00 ድረስ አዲስ አበባ ስቴዲዮም ናኒ ሕናፃ ዋናው መስሪያ ቤት 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 10 በሰም በታሸገ ኢንቨሎፕ በማዘጋጀት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ በማስገባት መወዳደር ይችላሉ፤ ጨረታው በዕለቱ 4፡15 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
5. ተጫራቾች በአማራ ክልል ደጀን ከተማ ዳሽን ሲሚንቶ ፋብሪካ ቅጥር ግቢ ውስጥ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት አስር የሥራ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ዕቃዎችን ማየት ይችላሉ፤
6. በጨረታው ላይ የፋብሪካው ሠራተኞች መሳተፍ አይችሉም፡፡
7. በጨረታው አሸናፊ የሆነ ግለሰብ /ድርጅት አሸናፊነቱ በተገለጸለት በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ጊዜ ውስጥ አሸናፊ የሆነባቸውን ዕቃዎች ሙሉ ዋጋ ገቢ በማድረግ ዕቃውን ማንሳት ሲኖርበት ዕቃዎቹን ማንሳት ካልቻለ ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዘው CPO እንዲወረስ ይደረጋል፤
9. በጨረታው የተሸነፈ ተጫራች ያስያዘው የጨረታ ማስከበሪያ ሰነድ CPO ለተጨራች እንዲመለስ ይደረጋል፡፡
ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ ሕጋዊ መብት አለው።
አድራሻ ፡–
- አዲስ አበባ ከተማ
- ስቴዲዮም ናኒ ሕንፃ ዋናው መስሪያ ቤት 7ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 10
ማሳሳቢያ፡
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር +251 99 394 9598 / +251 95 493 7915 ይጠቀሙ።
ተጫራቾች ሙሉ አድራሻ እና አማራጭ ስልኮቻቸውን መጥቀስ ይኖርባቸዋል።
ዕቃዎቹ የሚገኙት በአማራ ክልል በደጀን ከተማ ዳሽን ሲሚንቶ ፋብሪካ ቅጥር ጊቢ
ዳሽን ሲሚንቶ ፋብሪካ ኃ/የተ/የግ/ማኅበር