የሲዳማ ከልል የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት በአበራ ገለዴ ቀበሌ ሊያሰራ ላቀደው የበጎች በረት፣ የላሞች በረት እድሳት እና የውኃ ገንዳ ሥራ እንዲሁም እና በሎቄ ንዑስ የምርምር ጣቢያ እና የአጥር ሥራ፣ የአሳ ገንዳ እድሳት እና የጥበቃ ቤት ለማሠራት ህጋዊ ተጫራቾችን በአከባቢ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል


Addis Zemen(Aug 18, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ

የሲዳማ ከልል የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት 2017 በጀት ዓመት በዓለም ባንክ ድጋፍ በኤፍ. ኤስ.አር. ፕሮግራም በሁለት ሎት ማለትም

  •  1) በአበራ ገለዴ ቀበሌ ሊያሰራ ላቀደው የበጎች በረት፣ የላሞች በረት እድሳት እና የውኃ ገንዳ ሥራ እንዲሁም፣
  •  2. በሎቄ ንዑስ የምርምር ጣቢያ እና የአጥር ሥራ፣ የአሳ ገንዳ እድሳት እና የጥበቃ ቤት ለማሠራት ህጋዊ ተጫራቾችን በአከባቢ ጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሠረት፡

  1. ደረጃቸውGC-6/BC-6 እና ከዚያ በላይ የሆኑ የሥራ ተቋራጮች 2017 . ፈቃዳቸውን ያሳደሱና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN NO.) ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ ከኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ባለሥልጣን ወይም ከሲዳማ ክልል ኮንስትራክሽን ባለስልጣን የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ እና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ፡፡
  2. አስፈላጊውን የግንባታ ማቴሪያሎች፣ የሥራ መሣሪያዎች እና ሌሎች ሀብቶችን በግላቸው አቅርበው ግንባታውን መሥራትና ማጠናቀቅ አለባቸው፡፡
  3. በሲዳማ ክልል ውስጥ ሶስት (3) እና ከዚያ በላይ ፕሮጀክቶችን ውል ገብተው ግንባታ እያከናወኑ ያሉ እና ያላስረከቡ ስራ ተቋራጮች ይህን የጨረታ ሰነድ መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችሉም፡፡
  4. በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ውስጥ ፕሮጀክቶችን ሠርቶ ለማስረከብ ከአሠሪ እና ከሚመለከታቸው መሥሪያ ቤቶች ጋር ህጋዊ ውል ገብተው በስራ ወቅት ከአሠሪ መስሪያ ቤት ወይም ከአማካሪ መስሪያ ቤት ማንኛውም ዓይነት የሥራ አፈፃፀም ማስጠንቀቂያ የተሰጣቸው ሥራ ተቋራጮች የጨረታ ሰነድ መግዛትም ሆነ መወዳደር አይችሉም፡፡
  5. የሥራ ተቋራጮች ለውድድር ያቀረቡትን ብቃት (ቴክኒክ) መወዳደሪያ ሰነዶች ዋና (ኦሪጅናል) ሲጠየቁ አቅርበው ማመሳከር አለባቸው፤ ይህ ተጣርቶ ኮፒው ከዋናው ጋር ተመሳክሮ ትክክለኛ ካልሆነ ተቋራጩ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
  6. ማንኛውም ተጫራች ከአንድ ሎት በላይ መግዛት እና መወዳደር አይችልም፡፡
  7. የጨረታ ማስከበሪያ(Bid Security) ለሎት 1. 15,000.00 (አሥራ አምስት ሺህ ብር) ለሎት 2. 60,000.00 (ስልሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ዋስትና /BANK GAURANTEE/ ወይም የክፍያ ማዘዣ (CPO) ከመጫረቻ ሰነድ ጋር ማቅረብ የሚችሉ፡፡
  8. የሥራ ተቋራጮች በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ሕጋዊ ፈቃዳቸውን እና .. (VAT) የተመዘገቡበትን ሰርተፊኬትና ታክስ ክሊራንስ በማቅረብ የጨረታ ዶክመንቱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ 15 (አሥራ አምስት) ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 500 /አምስት መቶ ብር/ በሲዳማ ክልል የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ግዥ ፋይናንስ ንብ/አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በመክፈል ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
  9. የሥራ ተቋራጮች ከጨረታው መዝጊያ ቀን በፊት የግንባታውን ሳይት በራሳቸው ወጪ አይተው ማረጋገጥ አለባቸው፡፡
  10.  የጨረታው ሰነድ በተጫራቾች መመሪያ መሠረት ተሞልቶ ጨረታ ማስከበሪያ (bid bond/ security) ፋይናንሻል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ቅጂ(ኮፒ) እንዲሁም ቴክኒካል አንድ ዋና (ኦርጅናል) እና ሁለት ቅጂ(ኮፒ) ሰነዶችን በተለያየ ኤንቨሎፕ በሰም በማሸግ ለየብቻቸው ታሽጎ በአንድ ትልቅ ፓስታ ውስጥ በማድረግ በሁሉም ዶክመንት ላይ ስምና አድራሻ በመጻፍ ሕጋዊ የሆነ ማህተም በመምታት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 400 ሰዓት እስከ 600 ሰዓት በሲዳማ ክልል ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት ግዥ/ፋይናንስ ንብ/አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ለዚሁ አገልግሎት የተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ የጨረታ ማስከበሪያው ከቴክኒካል ሰነድ ጋር አብሮ መታሸግ አለበት፡፡
  11. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከላይ በተጠቀሰው ቦታ ከቀኑ 600 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ከቀኑ 8:00 ሰዓት ላይ ይከፈታል፣ የተጫራቾች አለመገኘት የጨረታውን ከመከፈት አያግደውም፡፡
  12.  አሠሪው መሥሪያ ቤት የተሻለ አማራጭ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብት አለው፡፡
  13. አሸናፊው ተጫራች በጨረታ ሰነዱ ላይ በተጠቀሰው መሠረት ለቅድመ ክፍያ በሁኔታ ላይ ያልተመሠረተ የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  14.  የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ላይ ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ቦታና ሰዓት ይሆናል፡፡

በሲዳማ ክልል የግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት