Your cart is currently empty!
በቂርቆስ ክ/ከተማ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ዕቃ ወይም አገልግሎቱን መግዛት ወይም ማግኘት ይፈልጋል
Addis Zemen(Aug 27, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ጨረታ ቁጥር 01/2017 ዓ.ም
በቂርቆስ ክ/ከተማ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የመንግስት ግዥ ቡድን ከዚህ በታች በተዘረዘሩት ላይ ተጫራቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ዕቃ ወይም አገልግሎቱን መግዛት ወይም ማግኘት ይፈልጋል፡፡
ሎት
|
|
የጨረታ ማስከበሪያ በሲኦፕ
|
ሎት 1 |
የፅሕፈት መሳሪያዎች |
20000
|
ሎት2 |
የቢሮ ምንጣፍና መጋረጃ |
4000
|
ሎት3 |
የድንኳን እና ፕላስቲክ ወንበሮች እና ጠረጴዛዎች ኪራይ |
2000
|
ሎት4 |
የተሽከርካሪ ግብዓቶች |
5000
|
ሎት5 |
የሰራተኞች ካፍቴሪያ አገልግሎት |
20000
|
ሎት6 |
ጫኝና አውራጅ የጉልበት |
5000
|
ሎት7 |
የሊፍት ጥገናና ሰርቪስ አገልግሎት |
10000
|
ሎት8 |
የጄኔሬተር ጥገናና ሰርቪስ አገልግሎት |
4000
|
ሎት9 |
የኤሌክትሪክ መለዋወጫ ዕቃዎች |
5000
|
ሎት10 |
የህክምና መሳሪዎች ዕቃዎች |
10000
|
ሎት11 |
ቋሚ የፈርኒቸር ዕቃዎች |
10000
|
ሎት12 |
ቋሚ ዕቃዎች |
5000
|
ሎት13 |
የከባድ መኪና ጋራዥ ጥገናና ሰርቪስ |
20000
|
ሎት14 |
የመኪና መቆጣጠሪያ ጂፒኤስና የነዳጅ ሴንሰር |
10000
|
በዚህም መሰረት ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ድርጅቶች ወይም ግለሰቦች በጨረታ እንዲሳተፉ እንጋብዛለን፡፡
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት፣ በአቅራቢነት የተመዘገቡና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN NO/ እንዲሁም የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት ያላቸው::
- የጨረታ ሰነድ አቀራረብ ቴክኒካል ሰነድ ኦርጅናል፣ ቴክኒካል ሰነድ ኮፒ፣ ፋይናንሻል ሰነድ ኦርጅናል፣ ፋይናንሻል ሰነድ ኮፒ ለየብቻው እንዲሁም ሲፒኦ/CPO/ በባንክ የተረጋገጠ ለብቻ በታሸገ ኢንቨሎፕ ማቅረብ አለበት፡፡
- በጨረታው ላይ ጥቃቅንና አነስተኛ አቅራቢዎች ይበረታታሉ ሆኖም ግን የጨረታ ሰነዱን በነጻ ለማግኘት የሚችሉት ከተቋማት የበላይ ሀላፊዎች ተገቢና የተሞላ ማስረጃ ሲያቀርቡ ብቻ ነው፡፡
- ናሙና ለሚያስፈልጋቸው ማቴሪያሎች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ በገዙበት ሰነድ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ ቫትን ጨምሮ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን እስጢፋኖስ ቤ/ክርስቲያን አካባቢ በሚገኘው የቂርቆስ ክ/ከተማ አስተዳደር ህንጻ 6ኛ ፎቅ የፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ልማት ጽ/ቤት የፋይናንስና አስተዳደር የግዥ ቡድን በመቅረብ 400 ብር በመክፈል መውሰድ የሚችሉ ሲሆን ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን የሚከፈተው ደሞ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋ ሲሆን በተመሳሳይ ቀን ከጠዋቱ 4፡30 ላይ ጨረታው ይከፈታል፡፡
- አሸናፊ ድርጅት አሸነፊነቱ ከተገለጸለት ከ7 ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ በግንባር ቀርቦ አሸናፊ የሆነበት ጠቅላላ ዋጋ 10 በመቶ የውል ማስከበሪያ በማስያዝ በ8 የስራ ቀናት ውስጥ ውል መያዝ አለበት፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፣ እስጢፋኖስ ከሚገኘው ከማዎት ሆቴል ፊትለፊት የቂርቆስ ክ/ከተማ
አስተዳደር 6ኛ ፎቅ ስልክ 011 558 2871
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሃብት ልማት ጽ/ቤት