Your cart is currently empty!
ዘ ሀንገር ፕሮጀክት ኢትዮጵያ የተለያዩ ለዉሃ ኮንስትራክሽን ግብዓቶችን በብዛት የሚያቀርቡ አቅራቢዎችን አወዳድሮ መግዛት ስለፈለገ በዝርዝሩ መሰረት ማቅረብ የምትችሉ አቅራቢዎችን ማወዳደር ይፈልጋል
Reporter(Sep 03, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ ለዉሃ ኮንስትራክሽን ግብዓቶች ግዥ
ዘ ሀንገር ፕሮጀክት ኢትዮጵያ
ዘ ሀንገር ፕሮጀክት ኢትዮጵያ ትርፋማ ያልሆነ በሲቪል ማህበር ድርጅት ኤጀንሲ እ.ኤ.አ. 2004 ተመዝግቦ በኢትዮጵያ ገጠራማ አካባቢዎች ፕሮጀክቶችን ተግባራዊ እያደረገ ያለ የውጭ ድርጅት ነው:: በአሁኑ ጊዜ ድርጅቱ ለሚሰራዉ የህብረተሰብ አቀፍ ፕሮጀክቶች ግብዓት የሚሆን የተለያዩ ለዉሃ ኮንስትራክሽን ግብዓቶችን በብዛት የሚያቀርቡ አቅራቢዎችን አወዳድሮ መግዛት ስለፈለገ በዝርዝሩ መሰረት ማቅረብ የምትችሉ አቅራቢዎችን ማወዳደር ይፈልጋል:: የዉሃ ኮንስትራክሽን ግብዓት እቃዎች ዓይነትና ዝርዝር ከዚህ በታች በሠንጠረዡ ዉስጥ ተዘርዝረዋል።
ተ.ቁ |
የእቃዎች ዓይነትና ዝርዝር Item Description |
መለኪያ Unit |
ብዛት Qty |
ያንዱ ዋጋ Unity price |
1 |
Afridev pump with accessories indian mark ajay (15m) |
pcs |
1 |
|
2 |
Cylinder |
pcs |
1 |
|
3 |
Foot valve with Finger |
pcs |
1 |
|
4 |
Fulcrum Pin |
pcs |
1 |
|
5 |
Hanger Pin |
pcs |
1 |
|
6 |
Bush Bearing |
pcs |
1 |
|
7 |
Rod |
pcs |
1 |
|
8 |
PVC |
pcs |
1 |
|
ከዚህ በታች የተመለከቱትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ማንኛዉም ፍላጎት ያለው ተጫራቾች በጨረታው መወዳደር የሚችሉ ሲሆን ከዋጋ ማቅረቢያው ጋር የሚከተሉትን ሰነዶች ማቅረብ ይጠበቅበታል።
- የታደሰ ንግድ ፍቃድ
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸዉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች የሚያቀርቡትን ጠቅላላ ዋጋ 2% የጨረታ ማስክበሪያ ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል።
ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከዚህ በታች በተገለጸው አድራሻ በአካል በመቅረብ የዋጋ ዝርዝር በመሙላት የጨረታ ሰነዱን ማስገባት ይችላሉ።
ጨረታዉ በመስከረም 8, 2018 ዓ/ም ከጥዋቱ 4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቻዉ በተገኙበት በድርጅቱ ቢሮ ይከፈታል።
ድርጅቱ ጨረታዉን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነዉ።
አድራሻ፡ ዘ ሀንገር ፕሮጀክት ኢትዮጵያ ጽ/ቤት በየካ ክ/ከተማ ወረዳ 08 ቤት ቁጥር 765/04 አዲስ አበባ፤ ምስራቅ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከፍ ብሎ የሚገኝ ሲሆን ተጫራቾች
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0111 267 151 /267950. +251913258163 መደወል ይችላሉ።