Your cart is currently empty!
የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት የቁም ደንና ጣውላ ምርት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 03, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የቁም ደንና ጣውላ ምርት ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት በደ/ወሎ ዞን በተሁለደሬ ደ/ዙሪያና አልብኮ ወረዳዎች ባሉ ቀበሌዎች የተለያዩ የመንግስት ደን ውስጥ ያለውን የፈ/ጽድ 4,873.77ሜ/ኩብ የነጭ ባህርዛፍ 31,422.97 ሜ/ኩብ የፈ/ግራር 20.26 ሜ/ኩብ እና የወደቀና የደረቀ 23.24 ሜ/ኩብ በድምሩ 36,340.24 ሜ/ኩብ ቁም ደን፣ በደ/ ጎንደር እና ማ/ጎንደር ዞን ደራና ጭልጋ ወረዳ ባሉ ቀበሌዎች የመንግስት ደን ውስጥ ያለውን የፈ/ጽድ 7,494.68 ሜ/ኩብ ቀይ ባህርዛፍ 927.99 እና ነጭ ባህርዛፍ 671.4 ሜ/ኩብ በድምሩ 9,094.08 ሜ/ኩብ ቁም ደን፥ በምስ/ጎጃም ዞን ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ ምጣድ ዱር የመንግስት ደን ውስጥ ያለውን 620.11 ሜ/ኩብ የፈ/ ጽድ ቁም ደን እና በአዊ ዞን ባንጃና ጓንጓ ወረዳዎች ባሉ ቀበሌዎች የመንግስት ደን ውስጥ የሚገኘውን 3,158.20 ሜ/ኩብ የፈ/ጽድ ቁም ደን እንዲሁም በደ/ታቦር እ መሰ/ ማሽን የተመረተ 87.14ሜ/ኩብ የፈ/ጽድ ጣውላ ምርት ባለበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች:
1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድና የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
2. የሽያጩ መጠን 200,000.00/ሁለት መቶ ሺህ /ብር በላይ ከሆነ የተእታ NVAT/ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
3. ለጨረታ የቀረቡትን ቁም ደን ምርቶች ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት በቦታው ተገኝተው ማየት ይችላሉ፡፡
4. የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 10 የስራ ቀናት ውስጥ /ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ/ በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት ባሕር ዳር ቀበሌ 14 አዲሱ መናኸሪያ ጀርባ እንስሳት ማዳቀያ ጊቢ ውስጥ ከኢንተርፕራይዙ ቢሮ ቁጥር 06 እና በሁሉም ቅ/ጽ/ቤቶች የማይመለስ 200.00(ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
5. ተጫራቾች ለመግዛት የሚፈልጉትን ምርት ጠቅላላ ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ/CPO/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
6. ተጫራቾች መግዛት የሚፈልጉትን ቁም ደን በኦሪጅናል ዋጋ መሙያ ቅጽ የሚገዙበትን ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ ፡ስምና አድራሻቸውን በመፃፍ ፈርመው በመሙያው ሰነዱ ላይ ማህተም በማስቀመጥ የታሸገውን የጨረታ ፖስታ በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 06፣ ደ/ብርሃንና ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች የቁም ደንና ጣውላ የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ›› ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 10 የሥራ ቀናት (ቅዳሜን ግማሽ ቀን ጨምሮ) እስከ መጨረሻው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል። ጨረታው በዚሁ ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ ሳጥኑ ታሽጎ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ይሁን እንጂ ተጫራቾች ባይገኙም ይከፈታል።
7. ተጫራቾች የሚሞሉት ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ 15% ተእታን አይጨምርም፡፡ ሆኖም አሸናፊው በአሸነፈበት ዋጋ ላይ 15% ተእታን ጨምሮ ይከፍላል።
8. ተጫራቾች ቁም ደኑን በተመለከተ ቅልቅል ደን ተብሎ የቀረበውን ክፍልፋይ ሁሉንም አይነት ምርት ክፍልፋይ እና የጣውላ ምርትን ሁሉንም ሎት/ምድብ በመሙላት ማንሳት ይጠበቅባቸዋል።
9. በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
10. ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር ባ/ዳር 058 226 3095′ ደ/ታቦር 058 441 0306 ደ/ብርሃን 011 637 5017 እንጅባራ 058 227 0485 ደ/ማርቆስ 058 871 9004 ኮ/ቻ 09 14 71 66 36 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት