Your cart is currently empty!
የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ያገለገሉ ማሽነሪዎችና መለዋወጫዎች ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 07, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ያገለገሉ ማሽነሪዎችና መለዋወጫዎች
የግልፅ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡– DIS 01/2017
ድርጅታችን የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ያገለገሉ የተለያዩ አይነት ፎርክ ሊፍቶችን፣ ኢምፒቲ ኮንቴይነር ማንሻ ማሽኖችን፣ የተርሚናል ትራክተሮችን፣ የውሃ ታንከር ትሬለርን፣ ትራክተርን፣ ሪችስታከርን፣ ትራክተርን፣ ታይር ሪካፕ ማሽነሪን፣ ኮንከሬን ማሽንንና የማሽነሪ መለዋወጫ የሆነ የማሽን ሞተር ጊርቦክስ፣ ሃይድሮሊክ ሲሊንደር ፒስተን፣ ሊፍቲነገ ሲሊንደር፣ ስቲሪንግ ሲሊንደር፣ ትራንስሚሽን ጊር ቦክስ እንዲሁም የማሽነሪ አታችመንት የሆኑ ፔፐር ሮል ክላምፕን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም በግልፅ ጨረታው ለመሳተፍና ለመወዳደር ፈቃደኛ የሆነ ተጫራች ይህ ማስታወቂያ እሁድ ጳጉሜን 2 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታው እስከ ሚታሸግበት አርብ መስከረም 9 ቀን 2018 ዓ.ም ዘወትር በሥራ ሰዓት ከ2፡30 እስከ 6፡00 ሰዓት እና ከሠዓት ከ8፡00 እስከ 11፡00 ሰዓት እና አርብ መስከረም 9 ቀን 2018 ዓ.ም ከ2:30 እስከ 4፡00 ሰዓት ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ የማይመለስ ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ለገሀር ከሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት 3ኛ ፎቅ በመክፈል ሰነዱን ከ6ኛ ፎቅ መውሰድና በጨረታ ሂደቱ መሳተፍ ይቻላል።
ተጫራቾች ንብረቶቹን ለማየት ማስታወቂያው ከወጣበት እሁድ ጳጉሜን 2 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ጨረታው እስከ ሚታሸግበት አርብ መስከረም 9 ቀን 2018 ዓ.ም ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ከ2፡30 እስከ 6፡00 እና ከ8፡00 እስከ 111፡00 ሰዓት እና አርብ መስከረም 9 ቀን 2018 ዓ.ም ከ2፡30 እስከ 4፡00 ሰዓት በአካል በቃሊቲ ወደብና ተርሚናል እና በሞጆ ሎጀስቲክስ ማዕከል የጨረታ ሰነድ የገዙበትን ማስረጃ በማሳየት መመልከት ይችላሉ።
ጨረታው አርብ መስከረም 9 ቀን 2018 ዓ.ም በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ እለት በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ለገሀር በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የሚከፈት ሲሆን ተጫራቾች በክፍል ሁለት ላይ በሚፈልጉት የንብረት አይነት ላይ የመወዳደሪያ ዋጋቸውን ተ.እ.ታ ጨምሮ በመሙላት እና ለሚወዳደሩበት የንብረት አይነት የተቀመጠውን 20% (ሃያ በመቶ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) በተቋሙ ትክክለኛ ስም የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ (Ethiopian Shipping & logistics) በማሠራት ከጨረታ ሰነዱ ጋር በፖስታ በማሸግ ከ8፡ዐዐ ሰዓት በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
በጨረታ መክፈቻው ሰዓት፣ እለትና ቀን ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በራሳቸው ፈቃድ ካልተገኙ ተቋሙ ጨረታውን ከመከፈት አይታገድም።
ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስለጨረታው ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– 011-5-54-93-04/ 0951-41-42-04 ማብራሪያ ማግኘት ይቻላል።
የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ