Your cart is currently empty!
የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ የጨረታ ማራዘሚያ ማስታወቂያ አውጥቷል
Addis Zemen(Sep 18, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልፅ የጨረታ ሽያጭ ማራዘሚያ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- DIS 01/2017
ድርጅታችን የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ ያገለገሉ የተለያዩ አይነት ፎርክ ሊፍቶችን፣ ኢምፒቲ ኮንቴይነር ማንሻ ማሽኖችን፣ የተርሚናል ትራክተሮችን፣ የውሃ ታንከር ትሬለርን፣ ትራክተርን፣ ሪችስታከርን፣ትራክተርን፣ ታይር ሪካፕ ማሽነሪን፣ ኮንክሬን ማሽንንና የማሽነሪ መለዋወጫ የሆኑ የማሽን ሞተር፣ ጊርቦክስ፣ ሃይድሮሊክ ሲሊንደር ፒስተን፣ ለፍቲነገ ሲሊንደር፣ ስቲሪንግ ሲሊንደር፣ ትራንስሚሽን ጊር ቦክስ እንዲሁም የማሽነሪ አታችመንት የሆኑ ፔፐር ሮል ክላምፕን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ቅዳሜ ጳጉሜን 1 ቀን 2017 ዓ.ም በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወቃል፡፡ በወጣው ማስታወቂያ መሰረት ጨረታው አርብ መስከረም 9 ቀን 2018 ዓ.ም ከሰዓት 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ እለት ከሰዓት 8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ለገሀር በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያቤት እንደሚከፈት የተመላከተ ቢሆንም ከህዝባዊ በአላት ጋር ተያይዞ ለተጫራቾች በቂ ጊዜ ለመስጠት እንዲቻል የጨረታ መክፈቻ ቀኑን ማራዘም አስፈልጓል፡፡
በመሆኑም በዚህ የግልፅ ጨረታ ሽያጭ ማራዘሚያ ማስታወቂያ መሰረት የማራዘሚያ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ጨረታው እስከ ሚታሸግበት ሐሙስ መስከረም 15 ቀን 2018 ዓ.ም ዘወትር በሥራ ሰዓት ከ2፡30 እስከ 6፡00 ሰዓት እና ከሠዓት ከ8፡00 እስከ 11፡ 00 ሰዓት እና ሐሙስ መስከረም 15 ቀን 2018 ዓ.ም ከ2፡30 እስከ 4፡00 ሰዓት ዘወትር በሥራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ የማይመለስ ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ለገሀር ከሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት 3ኛ ፎቅ በመክፈል ሰነዱን ከ6ኛ ፎቅ መውሰድና በጨረታ ሂደቱ መሳተፍ ይቻላል፡፡
የግልፅ ጨረታው ሐሙስ መስከረም 15 ቀን 2018 ዓ.ም በ8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ እለት በ8፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ለገሀር በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት 6ኛ ፎቅ የሚከፈት ይሆናል፡፡
በጨረታ መክፈቻው ሰዓት፣ እለትና ቀን ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በራሳቸው ፈቃድ ካልተገኙ ተቋሙ ጨረታውን ከመከፈት አይታገድም፡፡
ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስለ ጨረታው ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011-554-9304 ማብራሪያ ማግኘት ይቻላል።
የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ
ከዚህ በፊት የወጣውን ጨረታ ለመመልከት እባክዎን ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ
https://tender.2merkato.com/tenders/68bbfe340a538a0b3f000001