Your cart is currently empty!
የጋሞ ልማት ማህበር ጋልማ/ ዋና ጽ/ቤት ያገለገሉ ንብረቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 19, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ያገለገሉ ንብረቶች ለመሸጥ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
ያገለገሉ እስካኒያ መኪናዎች፣ ኖቬዶች፣ የተለያዩ ተሽከርካሪዎች መለዋወጫዎች እና ሌሎች ያገለገሉ ንብረቶች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የጋሞ ልማት ማህበር ጋልማ/ ዋና ጽ/ቤት በጋልማ የአርባ ምንጭ እርሻ ልማት፣ በጋልማ የጋሮ ተሸከርካሪዎች ጥገናና መለዋወጫ እና በጋልማ የአርባ ምንጭ አዞ ራንች ቅጥር ግቢ የሚገኙና ያገለገሉ የተለያዩ ተሽከርካሪዎች፣ መለዋወጫዎች እና ሌሎች ያገለገሉ ንብረቶች ለቢሮና ለመኖሪያ ቤቶች የሚያገለግሉ የተለያዩ እቃዎችን ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ማሳሰቢያ፡–
- ተጫራቾች እንደየንብረቶቹ ዓይነት የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ የማቅረብ በጥሬ ገንዘብ የማስያዝ ግዴታ ያለባቸው ሲሆን በጨረታው ካሸነፉ ከሚገዙት ንብረት ላይ ታሳቢ የሚሆን ሲሆን በጨረታው ካላሸነፉ ያስያዙት ገንዘብ /ሲፒኦ/ ይመለስላቸዋል። የሚያስይዙት /CPO/ /ጥሬ ገንዘብ /በሠነድ ላይ በእቃዎች ፊት ለፊት የተገለፀው ይሆናል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ንብረቶች በጋልማ የአርባ ምንጭ እርሻ ልማት እና በጋልማ የጋሮ ተሽከርካሪዎች ጥገናና መለዋወጫ እና በጋልማ የአርባ ምንጭ አዞ ራንች ቅጥር ግቢ በማንኛውም የሥራ ሰዓት መመልከት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ጨረታውን ማሸነፋቸው ከተረጋገጠበት ቀን ጀምሮ ባሉ 15 የሥራ ቀናት ውስጥ ንብረቱን ማንሳት አለባቸው ካላነሱ ድርጅቱ ንብረቶቹ የቆዩበት 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በየቀኑ ኪራይ ያስከፍላል፣
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 የሥራ ቀናት በግዥ ፋይናንስና ንብረት አስተዳደር ዳይሬክተር ሥራ ክፍል በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ይጨምራሉ፣
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 /ሦስት መቶ ብር/ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን 8፡00 ሰዓት ድረስ በጋሞ ልማት ማህበር ዋና ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ክፍል መግዛት ይችላሉ፣
- ጨረታው በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል። ተጫራቹ ወኪሉ በቦታው ባይገኝም የጨረታው ሂደት አይስተጓጎልም።
- ልማት ማህበሩ በጨረታው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
- ከዚህ ጨረታ ጋር ተያያዥ ለሆኑ ጥያቄዎች በስልክ ቁጥር 0916482815 ደውለው መጠየቅ ይቻላል።
- የድርጅቱ አድራሻ ፡ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት በጋሞ ዞን አርባ ምንጭ ከተማ ነው።
የጋሞ ልማት ማህበር/ጋልማ
አርባ ምንጭ
cttx Computer and Accessories cttx, cttx Electrical, cttx Equipment and Accessories cttx, cttx Furniture and Furnishing cttx, cttx Home Appliance and Supplies cttx, cttx House Furniture cttx, cttx IT and Telecom cttx, cttx Office Furniture cttx, cttx Office Machines and Accessories cttx, cttx Office Supplies and Services cttx, cttx Other Sales cttx, cttx Sales, cttx Spare Parts and Car Decoration Materials cttx, cttx Stationery cttx, cttx Vehicle and Machinery Foreclosure cttx, cttx Vehicle and Machinery Sale cttx, Disposals and Foreclosure cttx, Electromechanical and Electronics cttx