Your cart is currently empty!
በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ፋይናንስ ጽ/ቤት የጽህፈት መሳሪያ፣ የደንብ ልብስ፣ የጽዳት እቃዎችን፣ ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣ የትራንስፖርት አገልግሎት፣ የኤሌክትሮኒክስ እና ሌሎች የቢሮ መገልገያ ጥገና አገልግሎቶች፣ የመስተንግዶ አገልግሎት፣ የደንብ ልብስ ስፌት አገልግሎት እና የሞንታርቦ፣ ድንኳን፣ ጀኔሬተር እና ሌሎች ኪራይ አገልግሎት በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Sep 24, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የ1ኛ ዙር ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ ጨረታ መለያ ቁጥር ጉ/ክ/ከ/ወ/001/2018
በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 8 ፋይናንስ ጽ/ቤት የጽህፈት መሳሪያ፣ የደንብ ልብስ፣ የጽዳት እቃዎችን፣ ቋሚ የቢሮ እቃዎች፣ የትራንስፖርት አገልግሎት፣ የኤሌክትሮኒክስ እና ሌሎች የቢሮ መገልገያ ጥገና አገልግሎቶች፣ የመስተንግዶ አገልግሎት፣ የደንብ ልብስ ስፌት አገልግሎት እና የሞንታርቦ፣ ድንኳን፣ ጀኔሬተር እና ሌሎች ኪራይ አገልግሎት በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
በዚህ መሰረት ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሕጋዊ ተጫራቾች የሚከተለውን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው፡፡
1. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እና ቲን ነምበር ያላቸው መሆን አለባቸው።
2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትር ወይም በአዲስ አበባ ፋይናንስ ቢሮ የአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡበትን የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
3. ለሚጫረቱባቸው እቃዎች እንደአስፈላጊነቱ ናሙና ማቅረብ አለባቸው።
4. የታደሰ ንግድ ፈቃድ እና የንግድ ፍቃድ የምስክር ወረቀት ያላቸው በተሰጠበት የንግድ ዘርፍ ብቻ መሳተፍ ይችላሉ።
5. ተጫራቾች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በጽ/ቤቱ ስም የተዘጋጀ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብቻ ማቅረብ አለባቸው።
6. ተጫራቾች ከአንድ ሎት በላይ የሚወዳደሩ ከሆነ የጨረታ ማስከበሪያውን በተናጠል ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
ሎት ቁጥር |
አላቂ የጽህፈት መሳሪያ
|
የተጠየቀው የጨረታ ማስከበሪያ (በኢትዮጵያ ብር) |
1 |
አላቂ የጽህፈት መሳሪያ |
84,000 |
2 |
የፅዳት ዕቃዎች |
83,631 |
3 |
የደንብ ልብስ |
80,000 |
4 |
ቋሚ የቢሮ እቃዎች |
20,000 |
5 |
ህትመት |
18,174 |
6 |
የትራንስፖርት አገልግሎት |
25,000 |
7 |
የኤሌክትሮኒክስ እና ሌሎች የቢሮ መገልገያ እቃዎች ጥገና አገልግሎት |
9,000 |
8 |
የመስተንግዶ አገልግሎት |
73,245 |
9 |
የደንብ ልብስ ስፌት አገልግሎት |
25,000 |
10 |
የሞንታርቦ፤ ድንኳን፤ጀኔሬተር አና ሌሎች ኪራይ አገልግሎት |
17,950 |
7. በጨረታው ያላሸነፉ ድርጅቶች ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ይመለስላቸዋል፡፡
8. ተጫራቾች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የሥራ ቀናት የሚውል ሲሆን ብር 500 (አምስት መቶ ብር) የኢትዮጵያ ብር በመክፍል የጨረታ ሰነዱ ጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ-8 ፋ/ኢ/ል ጽ/ቤት ቢሮቁጥር 2 መውሰድ ትችላላችሁ፡፡
9. ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ ዋናውን እና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በማሽግ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
10. በአምራች ዘርፍ የተሰማሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ብቻ የተደራጁ አካላት መወዳደር ከፈለጉ በጽ/ቤት ኃላፊ የተፈረመ የዋስትና ደብዳቤ ማስረጃ ሲያቀርቡ የጨረታ ሰነድ ወስደው መወዳደር ይችላሉ፡፡
11. በአምራች ዘርፍ የተሰማሩ ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞች ተደራጅተው ማስረጃ በማቅረብ የሚወዳደሩ ድርጅቶች ለውል ማስከበሪያ የሚሆን በጽ/ቤት ኃላፊ የተፈረመ የዋስትና ደብዳቤ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
12. ጨረታው ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት ተከታታይ 1o የሥራ ቀናት ውስጥ ጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ-8 ፋ/ኢ/ል ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡
13. ጨረታው በ10ኛው ቀን በ10፡30 ታሽጎ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
14. አንዱ በአንዱ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይችልም፡፡
15. ተጫራቾች የአንዱ ነጠላ ዋጋ ቫትን ያካተተ መሆኑን ወይም አለመሆኑን መጠቀስ አለበት ያልተጠቀሰ ከሆነ ቫት እንዳካተተ) ተደርጎ ይወስዳል፡፡
16. አሸናፊው ያሸነፈባቸውን ንብረቶች የወረዳው ንብረት ክፍል ድረስ ገቢ ማድረግ አለበት (የሰራተኛ እና የትራንስፖርት ወጪ አቅራቢ ድርጅቱ የሚችል ይሆናል)፡
17. አድራሻችን ጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ-8 አስተዳደር አዲሱ ገበያ ጤና ጣቢያ በስተጀርባ ነው፡፡
18. ፖስታዎቹ መታሸግና በላያቸው ላይ ማህተም መደረግ ይኖርባቸዋል፡፡
19. ለሰራተኞች የካፌ አገልግሎት ለመስጠት የሚጫረቱ ድርጅቶች የሻይ ማሽን፤ ፍሪጅ፤ ቴሌቪዥን፤ ወንበር፤ ጠረጴዛ እንዲሁም አስፈላጊ የሆኑ ምግብ ማብሰያ እና ማቅረቢያ በራሱ ማቅረብ ይኖርበታል
20. ቲ.ኦ.ቲ ተመዝጋቢዎች በመስተንግዶ የሞንታርቦ፤ ድንኳን፤ጀኔሬተር እና ሌሎች የኪራይ አገልግሎቶች እና የትራንስፖርት አገልግሎት ላይ መወዳደር ይችላሉ፡፡
21, መስሪያ ቤቱ በጨረታ በተገለፀው የዕቃ መጠን ላይ 20% የመጨመር ወይንም የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው
22. መ/ቤቱ ጨረታውን የተሻለ አማራጭ ካገኘ ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
23. ተጫራቾች ሳምፕል ለማይቀርብላቸው አቃዎች የእቃውን ፎቶ ኮፒ ከሰነዱ ጋር አያይዘው ማስገባት ይኖርባቸዋል
አድራሻ፡– ጉለሌ/ክ/ከተማ ወረዳ 8 ፋ/ኢ/ልማት ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2
ለበለጠ መረጃ ፡ በስልክ ቁጥር 0111547450 መደወል ይችላሉ፡፡
በጉለሌ ክ/ከተማ የወረዳ-8 ፋይናንስ ጽ/ቤት