Your cart is currently empty!
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት ለመምሪያው የስራ ክፍሎች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ጨረታዎችን በሀገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 14, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር A.K.K.K.P.D./NCB 001/2018 ዓ/ም
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ በ2018 በጀት ዓመት ለመምሪያው የስራ ክፍሎች አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ ጨረታዎችን በሀገር ውስጥ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት የሚፈልግ ሲሆን፦
|
ሎት |
የጨረታ ዓይነት |
የናሙና መለያ |
የጨረታ ማስከበሪያ ብር |
|
|
1 |
የጽህፈት መሳሪያዎች፤ |
ናሙና የሚቀርብባቸው |
60,400 |
00 |
|
2 |
የአይ ሲ ቲ (ICD) መለዋወጫ ዕቃዎች፤ |
ናሙና የሚቀርብባቸው |
40,900 |
00 |
|
3 |
የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ጥገናና ዕድሳት፤ |
ናሙና የሚቀርብባቸው |
6,000 |
00 |
|
4 |
የጽዳትና ሌሎች አላቂ ዕቃዎች፤ |
ናሙና የሚቀርብባቸው |
15,200 |
00 |
|
5 |
የህትመት ውጤቶች፣ |
ናሙና የሚቀርብባቸው |
25,500 |
00 |
|
6 |
የተሽከርካሪዎች ጎማ፤ ወንበር ልብስ፤ የዝናብና ፀሐይ መከላከያ ሸራ ከነመወጠሪያው ብረት እና የመኪና ሰርቪስ ዕቃዎች፣ |
ናሙና የሚቀርብባቸው |
71,000
|
00 |
|
7 |
ለስልጠና የታሸገ ውሃ ፤ |
ናሙና የሚቀርብባቸው |
11,100 |
00 |
|
8 |
የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ፤ |
ናሙና የሚቀርብባቸው |
47,500 |
00 |
|
9 |
የኤሌክትሪክ ፤ የቧንቧና የህንፃ መሳሪያዎች ፤ |
ናሙና የሚቀርብባቸው |
27,000 |
00 |
|
10 |
የተለያዩ ደንብ አልባሳቶች ግዥ እና ልብስ ስፌት አገልግሎት |
ናሙና የሚቀርብባቸው |
68,800 |
00 |
|
11 |
የተጠርጣሪዎች ቀለብ አቅርቦት ግዥ ፤ |
ናሙና የሚቀርብባቸው |
20,000 |
00 |
|
12 |
የመጸዳጃ ቤት ፈሳሽ ማስመጠጥ አገልግሎት ፤ |
ደጋፊ ሰነድና ሊብሬ |
8,000 |
00 |
|
13 |
የተሽከርካሪዎች ጎማዎች ጥገናና ዕድሳት (ጎሚስታ) |
|
2,000 |
00 |
|
14 |
የክበብ ጨረታ ለመምሪያውና 9ኙ ፖሊስ ጣቢያ ፤ |
|
67,000 |
00 |
|
15 |
የቋሚ ዕቃዎች |
ናሙና የሚቀርብባቸው |
69,000 |
00 |
|
ድምር ብር |
539,400 |
|
||
ስለዚህ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት አለባቸው።
- የታደሰ ምዝገባ ፈቃድና ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸው መሆን እና በዘርፉ የተሰማሩ ለመሆናቸው በጀርባው ይመልከቱ የሚል ፅሁፍ በግልፅ ማቅረብ አለባቸው።
- የግብር ከፋይ መለያ የያዘ (Tin) ሠርተፍኬት ፤
- ተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው።
- የመንግስት መ/ቤቶች ለሚያወጡት ጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የአቅራቢዎች የዌብ ሣይት የሚረጋገጥ ይሆናል።
- ጥቃቅንና አነስተኛ በሚያመርቱት ምርት ብቻ ልዩ አስተያየት ይደረጋል።
- አማራጭ ዋጋ እና አማራጭ ዕቃ በዚህ ጨረታ ማቅረብ አይቻልም።
- በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ የጨረታ ውጤቱ እንደታወቀ ተመላሽ የሚሆን በሎቱ ፊት ለፊት የተቀመጠውን የገንዘብ መጠን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ተብሎ በተዘጋጀው ከባንክ በተመሰከረለት ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- በጨረታ ውጤቱ አሸናፊ መሆኑን ከታወቀ ከ8ኛ ቀን ጀምሮ 10% የውል ማስከበሪያ ዋስትና ለአዲስ ከተማ ከፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ተብሎ በተዘጋጀው ከባንክ በተመሰከረለት ሲ.ፒ.ኦ ማስያዝና ውል መዋዋል ይኖርባቸዋል።
- ማንኛውንም ተጫራቾች ቴክኒካል ሰነዶችንና የዋጋ ማቅረቢያዎችን /ፋይናሻል ሰነዶች በተለያየ ፖስታ ታሽጎ ለየብቻ እና የሚያስገባው ሰነድ ፋይናሻል የጨረታ ሰነድ አንድ ኦሪጅናልና አንድ ኮፒ በተለያየ ፖስታ በማሸግ በፖስታው ላይ የጨረታ ሰነዱን ቁጥር የሚጫረትበትን ዕቃ አይነት በትክክል መፃፍ እንዲሁም በፖስታውና በገዙት ሙሉ የጨረታ ሰነድ ላይ ፈርመውና ማህተም በመምታት ማስገባት ያለበት ሲሆን፣ ስርዝ ድልዝ በፍሉድ የጠፋ ሰነድ ዋጋ ያልተሞላበት ዝርዝር ተቀባይነት የሌለው መሆኑን እናሳውቃለን።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚያሲዙት ሲ.ፒ.ኢ. ከቴክኒክ ሰነዶችጋር በአንድ ላይ ታሽገው መቅረብ አለባቸው።
- በጨረታ አሸናፊ የሆኑ ድርጅቶች ዕቃውን ወይም አገልግሎቱን በራሳቸው ትራንስፖርት አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ሚገኘው የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ግምጃ ቤት ወይም በክፍል 6 በፍላጎት መግለጫው በተጠቀሰው የማስረከቢያ ቦታ ድረስ በማምጣት ማስረከብ አለባቸው።
- በጨረታ ሰነድ በክፍል 6 ውስጥ በሚገኘው የፍላጎት መግለጫ ላይ በሚገለፀው መሰረት ጨረታ ሰነዱ ላይ በቀረበው መሰረት ናሙና ማቅረብ አለበት።
- ተጫራቾች ያቀረቡት ናሙናም ሆነ አሸናፊ መሆናቸው ሲረጋገጥ የሚያቀርቡአቸው ዕቃዎች ፖሊስ መምሪያው ባወጣው ፍላጎት መግለጫ /specification/ መሰረት መሆኑን በመምሪያው የጥራት ኮሚቴ ወይም በኢትዮጵያ ተስማሚነት ምዘና ኤጀንሲ አማካኝነት የሚረጋገጥ ይሆናል።
- ናሙናው ግቢ መሆን ያለበት ጨረታው ከሚከፈትበት ከአንድ ቀን በፊት መሆን አለበት።
- ተጫራቾች ጎጃም በረንዳ አስፋው ወሰን ሆቴል ጎን በሚገኘው መ/ቤት 5ኛ ፎቅ ግዢ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 ቀርበው በእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 11፡30 ሰዓት ድረስ እንዲሁም በማግስቱ በ11ኛው ቀን እስከ ጠዋቱ 4፡00 ሠዓት ድረስ ጨረታው ክፍት ሆኖ ቆይቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሠዓት ታሽጎ በዛው ዕለት 04፡30 ሰዓት ተጫራቾችና የሚመለከታቸው አካላት ባሉበት በመ/ቤቱ 5ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 10 ይከፈታል።
- ዘግይተው የሚመጡ የጨረታ ሰነዶች ተቀባይነት የላቸውም።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለበለጠ መረጃ በስ/ቁጥር 011 273 3735 ወይም 011 273-3404
የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ