Your cart is currently empty!
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ት/ፅ/ቤት የኢትዮ ኮርያ ሞዴል የመ/ደ/ት/ቤት የተለያዩ ዕቃዎችን እና አገልግሎቶችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 20, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልፅ የጨረታ መስታወቂያ
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ት/ፅ/ቤት የኢትዮ ኮርያ ሞዴል የመ/ደ/ት/ቤት በ2018 በጀት ዓመት ግልፅ ጨረታ ቁጥር 001/2018 ከዚህ በታች
የተዘረዘሩት ዕቃዎች ማለትም፡-
- የደንብ ልብስ
- አላቂ የቢሮ እቃዎች
- አላቂ የትምህርት እቃዎች
- ህትመት
- የህክምና ዕቃዎች
- የፅዳት እቃዎች
- ልዩ ልዩ ዕቃዎች
- ለህንፃ፣ የቤት ዕቃ፣ የቤት ውስጥ ተገጣጣሚዎች ግዢ
- ልዮ ልዮ/ ጥቃቅን ከፍያዎች
- የምርምር ዕቃዎች
- የጭነት አገልግሎት
- ቋሚ ዕቃዎች፡- በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት እና ማሰራት ይፈልጋል።
ስለሆነም በዚህ ጨረታ ላይ መሳተፍ የሚፈልግ ድርጅት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት ይኖርበታል።-
- ተጫራቾች ህጋዊ የንግድ ፍቃድ ያወጡና የተሰጣቸው ንግድ ፈቃድ 1 (አንድ) ዓመት የሞላው ከሆነ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን አለባቸው።
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN No) ያላቸው መሆኑን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- በዕቃ አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተዛቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ።
- ተጫራቾች ከአሁን በፊት በመንግስት ግዢዎች ላይ ተሳትፈው አሸናፊ መሆናቸውን ተገልጾላቸው ግዴታቸውን የተወጡና መልካም አፈጸጻም ያላቸው እና ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችሉ የገዢ መመሪያን በአግባብ የሚከተሉ እና የሚፈጽሙ እንዲሁም የሀገር ውስጥ አምራቾች የሀገር ውስጥ አምራች ለመሆናቸው የሚያረጋግጥ ደጋፊ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
- በወጣው ጨረታ ላይ መሳተፍ የሚፈልግ ተጫራች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ 400 ብር (አራት መቶ ብር) በፋይናንስ በመክፈል መውሰድ ይችላሉ። የጨረታ ማስከበሪያ በየሎቱ (ሎት 1) 40576 ብር ( ሎት 2) 20000 ብር( ሎት 3) 20000 ብር (ሎት 4) 1200 ብር (ሎት 5) 400 ብር (ሎት 6) 28000 ብር (ሎት 7) 6000 ብር (ሎት 8) 600 ብር (ሎት 9) 1866 ብር (ሎት 10) 200 ብር (ሎት 1) 5000 ብር (ሎት 12) 2000 ብር ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ከላይ በተገለፀው መሰረት በሲፒዩ ማስያዝ ይኖርበታል። ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 10 (አስር) የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 6፡30 እና ከሰዓት ከ7፡30 እስከ 11፡30 ቢሮ ቁጥር ስራ ከፍል በአካል በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
 
- መ/ቤቱ የሚገዛቸው ዕቃዎች ማለትም በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን የዕቃዎችና ተያያዥ አገልግሎቶች ዝርዝር መግለጫ ላይ ናሙና ሳምፕል እንድታቀርቡ እና ተከፍተው መታየት ያለባቸው ሳንፕሎች ተከፍተው ይታያሉ። ት/ቤቱ የራሱን ኮድ የሚሰጥ በመሆኑ በምታቀርቡት ናሙና ሳምፕል ላይ የድርጅታችሁን ስም መጻፍ ወይም መለጠፍ በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን በጥብቅ ያሳውቃል።
- ተጫራቾች በተሰጣቸው የዋጋ መሙያ ሠነድ ላይ ምንም ዓይነት ስፔሲፊኬሽን መጨመርም ሆነ መቀነስ አይችሉም።
- ተጫራቾች የወሰዳችሁትን የጨረታ ሰነድ ሙሉ በሙሉ ሳይገነጣጠል ተመላሽ የምታደርጉ ሲሆን በጨረታ ሰነዱ ላይ ምንም አይነት ስርዝ ድልዝ ሰነድ ት/ቤቱ የማይቀበልና ከውድድር ውጭ የሚያደርግ መሆኑን ይገልጻል።
- የጨረታ መዝጊያ ጊዜ ከተጠናቀቀ በኋላ ተጫራቾች ባቀረቡት የመወዳደሪያ ሃሳብ ላይ ለውጥ ወይም ማሻሻያ ማድረግና ከጨረታው ራሳቸውን ማግለል አይችሉም። በተጨማሪም ጨረታውን ለማዛባት የሚሞከሩ ተጫራቶች ከጨረታው ውጭ ሆነው ለወደፊቱም በመንግስት ግዥ እንዳይሳተፉ ይደረጋሉ።እንዲሁም ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ይወረስባቸዋል።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዕቃ በመለየትና በፖስታው ላይ በመግለጽ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ በት/ቤቱ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት ውስጥ ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት የምትችሉ መሆን እያሳወቅን የጨረታ ሳጥኑ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይታሸግና 4:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል። ሆኖም ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ጨረታው በሚከፈትበት ቦታ፣ቀንና ሰዓት / በራሳቸው ምክንያት ባይገኙ የጨረታ ሳጥኑ እንዲከፈት በማድረግ ውድድሩ ይካሄዳል።
- በጨረታው ላይ ሁለት እና ከሁለት በላይ የሆኑ እጩ ተወዳዳሪዎች በግምማው እኩል ውጤት ካቀረቡ ቅድሚያ ለአገር ውስጥ አምራች ለሆኑ ዕድሉን የምንሰጥ ሲሆን አምራች ተወዳዳሪ ከሌለ አሸናፈውን ለመለየት አብላጫ እቃዎችን ላሸነፈው እድሉን እንሰጣለን።
- አሸናፊ ተጫራች የግዢ ውል እንዲፈጽም ከመ/ቤቱ ደብዳቤ ከደረሰው ከ5ቀናት በኋላ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የአቅርቦት ውል ከግዢ ፈጻሚ መ/ቤቱ ጋር መፈራረም አለበት። ውል ተቀባይ ፈቃደኛ ካልሆነ በቀጣይ ከመንግስት ግዢ እንዲታገድ ይደረጋል።
- የጨረታ ውጤቱ ይፋ ሆኖ አሸናፊና ተሸናፊ ተጫራቾች እንደተለዩ በማስታወቂያ ላይ ከተገለጸ በኋላ ተሸናፊ ተጫራቾች ያስያዙትን 2% የጨረታ ማስከበሪያ ይመለስልኝ ደብዳቤ በመጻፍ ተመላሽ ይደረግላቸዋል። አሸናፊ ተጫራች ግን የውል ስምምነት እንዲፈጽም በተገለጸው ጊዜ ውስጥ ከአሸነፈበት ዕቃ አገልግሎት ጠቅላላ ዋጋ 10% የግዢ የውል ማስከበሪያ ሲያሲዙ ቀደም ብለው ያስያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ 2% ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
- ገዢው መ/ቤት በጨረታ ማስታወቂያ የተጠየቀውን ዕቃ ካቀረበው መጠን /ብዛት ላይ 20% ከውል በፊት የመጨመርና የመቀነስ መብት አለው።
- አቅራቢው በገባው የውል ስምምነት መሰረት የዕቃውን ዓይነት፣ መጠን እናጥራት ጠብቆ በውሉ ላይ በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ ካላቀረበ የግዢ ፈጻሚ መ/ቤቱ በጨረታ ሰነዱ በተገለጸው መሠረት አሸናፊ ተጫራች ካሸነፈውጠቅላላ ዋጋ ላይ 0.01% በየቀኑ ዕቃውን እስከሚያስረክብበት ቀን ድረስ ተቀናሽ ሆኖ ለመስሪያ ቤቱ የጉዳት ካሳ ገቢ ይሆናል። በተጨማሪም አቅራቢው ያሸነፈበትን ዕቃ ፈጽሞ ካላቀረበ ያስያዘው የውል ማስከበሪያ መ/ቤቱ ይወርሳል።
- በግዢ ፈጻሚ መ/ቤት እና በአቅራቢው መካከል የተለየ ስምምነት ከሌለ በስተቀር የተያዘው የውል ማስከበሪያ ዋስትና አቅራቢው ግዴታውን ሙሉ በሙሉ እንደተወጣ ሲረጋገጥ ወዲያውኑ ተመላሽ ይደረግለታል።
- በጨረታ ሂደቱ ላይ ጉዳት ደርሶብኛል ወይም በጨረታ ግምገማ ውጤት ላይ ቅር የተሰኘ ማንኛውም ተጫራች ጨረታው በድጋሜ እንዲታይለት የጨረታ ውጤት ይፋ ሆኖ በማስታወቂያ ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ቅሬታውን በግዢ ፈጻሚ መ/ቤት የበላይ ኃላፊ በጽሁ ፍቅሬታውን ማቅረብ ይኖርበታል። ሆኖም በተሰጠው ቀናት ውስጥ ቅሬታውን ሳያቀርብ ቀርቶ ቀነ ገደቡ ካለፈ በኋላ የሚመጣ ቅሬታ ተቀባይነት አይኖረውም። በጨረታ ሂደቱ ላይ ጉዳት ደርሶብኛል ወይም በጨረታ ግምገማ ውጤት ላይ ቅር የተሰኘ ማንኛውም ተጫራች ጨረታው በድጋሜ እንዲታይለት የጨረታ ውጤት ይፋ ሆኖ በማስታወቂያ ከተለጠፈበት ቀን ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ ቅሬታውን በግዢ ፈጻሚ መ/ቤት የበላይ ኃላፊ በጽሁፍ ቅሬታውን ማቅረብ ይኖርበታል። ሆኖም በተሰጠው ቀናት ውስጥ ቅሬታውን ሳያቀርብ ቀርቶ ቀነ ገደቡ ካለፈ በኋላ የሚመጣ ቅሬታ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
- በውድድር ወቅት በአንዱ ዋጋና ጠቅላላ ዋጋ መካከል ልዩነት ቢኖር በአንዱ ዋጋ መሰረት እና በአሃዝና በፊደል በሚገለጽበት ወቅት ልዩነት ቢኖር በፊደል በተገለጸው መሰረት በማስተካከል ይገመግማል።
- ያቀረቡት ናሙና የጨረታ ውጤት ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ ባሉት 60/ስልሳ ተከታታይ ቀናት ውስጥ እንዲወስዱ ተገልጾላቸው ጠይቀው ካልወሰዱ ለመንግስት በውርስ ገቢ ይደረጋል።
- ተጫራቾች የሚያቀርቧቸውን ዕቃዎች እስከ መ/ቤቱ መጋዘን ድረስ በራሳቸው ትራንስፖርት /ወጪ/ በማጓጓዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል። በተጨማሪም የሚያቀርቡት የዕቃ አይነት ተገጣጣሚ ከሆነ በራሳቸው ወጪ ገጣጥመው ማስረከብ ይኖርባቸዋል።
- በጨረታው ሠነድ ላይ ግልጽ ያልሆኑ ጉዳዩች አስመልክቶ ማብራሪያ ቢያስፈልጋችሁ በጽሁፍ ኢትዮ ኮርያ የመ/ደ/ት/ቤት በአካል በመምጣት ማቅረብ /መጠየቅ ትችላላችሁ።
- ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ፡- አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ስሙ ቃሊቲ ገብርኤል
ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት 40/60 ኮንዶሚኒየም ገባ ብሎ የመከላከያ የጋራ
መኖሪያ ቤት (ፋውንዴሽን) አጠገብ ኢትዮ ኮርያ ሞዴል የመ/ደ/ት/ቤት ስልክ ቁጥር 09 61 12 24 41/ 09 13 08 84 66
በአቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ት/ጽ/ቤት የኢትዮ ኮርያ ሞዴል ት/ቤት
cttx Advertising and Promotion cttx, cttx Building and Finishing Materials cttx, cttx Cleaning and Janitorial Equipment and Service cttx, cttx Computer and Accessories cttx, cttx Construction and Water Works cttx, cttx Education and Training cttx, cttx Electrical, cttx Equipment and Accessories cttx, cttx Freight Transport cttx, cttx Furniture and Furnishing cttx, cttx General Service Provision cttx, cttx Hand Tools and Workshop Equipment cttx, cttx Health Care, cttx Health Related Services and Materials cttx, cttx Home Appliance and Supplies cttx, cttx House Furniture cttx, cttx IT and Telecom cttx, cttx Laboratory Equipment and Chemicals cttx, cttx Materials cttx, cttx Medical Equipment and Supplies cttx, cttx Office Furniture cttx, cttx Office Machines and Accessories cttx, cttx Office Supplies and Services cttx, cttx Printed Advertising Materials cttx, cttx Printing and Publishing cttx, cttx Promotional Items cttx, cttx Rent cttx, cttx Shoes and Other Leather Products cttx, cttx Stationery cttx, cttx Test & Measurement Tools cttx, cttx Textile, cttx Vehicle cttx, cttx Warehousing, Electromechanical and Electronics cttx, Garment and Leather cttx, Garments and Uniforms cttx, Medical Industry cttx, Transit and Transport Service cttx