Your cart is currently empty!
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ከህዳር 01 ቀን 2018 እስከ ህዳር 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የሚያመርተውንና ለሳሙና መስሪያ ግብዓት የሚሆነውን የተነጠረ ሞራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
2merkato.com(Oct 22, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
የተነጠረ ሞራ ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
የአዲስ አበባ ቄራዎች ድርጅት ከህዳር 01 ቀን 2018 እስከ ህዳር 30 ቀን 2018 ዓ.ም ድረስ የሚያመርተውንና ለሳሙና መስሪያ ግብዓት የሚሆነውን የተነጠረ ሞራ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ማንኛውም ተጫራች፡-
- በመስኩ የታደሰ ሕጋዊ የንግድ ፍቃድና የዘመኑን ግብር የከፈለበትን ማስረጃ ኮፒ ማያያዝ ይኖርበታል፡፡
- ለተነጠረ ሞራ የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ለሦስቱ የጨረታ ጊዜ ለእያንዳንዱ ብር 300,000.00 (ሦስት መቶ ሺ ብር) በጥሬ ገንዘብ መሰብሰቢያ ደረሰኝ ወይም በሲ.ፒ.ኦ ብቻ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- ጨረታውን ያሸነፈ ማንኛውም ተጫራች ምርቱ በተመረተበት ቀን ሙሉ በሙሉ የእጅ በእጅ ሽያጭ በማከናወን ማንሳት የሚችል መሆን አለበት፡፡
- አሸናፊው የሚኖረው መብትና ግዴታዎች በውል ውስጥ የሚካተት ይሆናል፡፡
- የተዘጋጀውን የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር) በመክፈል ከድርጅቱ ማርኬቲንግ የሥራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 2 መግዛት ይቻላል፡፡
ጨረታው ጥቅምት 21 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 4:15 ተዘግቶ በዚሁ ዕለት 4:30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በድርጅቱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0114-163978 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ