የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ደሴ ዲስትሪክት የእርሻ ትራክተር ከነተሳቢው በድርድር ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 22, 2025)

ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below. 

የድርድር ጨረታ ማስታወቂያ

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ለራያ ፍሬሽ ፕሮዲዩስ ኃ/የተ/የግ/ማህበር የሰጠውን ብድር ድርጅቱ ተመላሽ ባለማድረጉ ንብረቶቹን ተረክቦ በድርድር ጨረታ ሸጦ ካለባቸው እዳ ላይ እንዲቀናነስ ያደረገ ቢሆንም የመያዥያ ንብረቶቹ ብድሩን መሸፈን ባለመቻላቸው ባንካችን በድርጅቱ ስም ተመዝግቦ የሚገኝ ሀብት ወይም ንብረት በማፈላለግ በድርጅቱ ስም ግዥ የተፈፀመበትን የመከስከሻ ማሽን በአዋጅ ቁጥር 97/90፤98/90 እና 216/92 ለባንኩ በተሰጠው ስልጣን መሰረት በድርድር ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

ከዚህ በተጨማሪ ባንኩ ለሰሜን ወጋገን ህ/ስራ/ማ/ዩኒየን ኃ/የተወሰነ የእርሻ መካናይዜሽን ፕሮጀክት የሰጠውን የካፒታል እቃ የሊዝ እዳ ወቅቱን ጠብቆ መክፈል ባለመቻሉ የካፒታል እቃዎቹን ማለትም አንድ የእርሻ ትራክተር ከነተሳቢው አሁን ባለበት ሁኔታ በሊዝ አዋጅ ቁጥር 103/1998 (እንደተሻሻለው እ.ኤ.አ 807/2013) መልሶ በመረከብ ለባንኩ በተሰጠው ስልጣን መሰረት በድርድር ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።

.

የተበዳሪው/የተከራይ ስም/የመያዣ ሰጭው ስም

የሚሸጠው ንብረት አድራሻ እና አይነት

የጨረታ መነሻ ዋጋ

የድርድር ጨረታ ደረጃ

የድርድር ጨረታው የሚካሄድበት ቀን እና ሰዓት

 

 

1

 

 

ራያ ፍሬሽ ፕሮዲዩስ /የተ/የግ/ማኅበር

 

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን ደሴ ከተማ አስተዳደር የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ደሴ ዲስትሪከት ቅጥር ግቢ ውስጥ የሚገኘውን የመከስከሻ ማሽን (Disc Harrow)

 

 

1,537,500

 

 

 

3

 

 

አርብ ጥቅምት 28 ቀን 2018 . ከቀኑ 800 ሰዓት እስከ 1000 ሰዓት

 

ሞዴል: NVCR DE 32 D/DSC MIS 22*P1

መለያ ቁጥር፡00614943085001

ማሽኑ የተመረተበት ዘመን April,2017

የተመረተበት ሀገር፡ብራዚል

የመከስከሻው ብዛት፡32

ብዛት፡01

 

 

 

 

 

 

 

2

 

 

 

 

 

 

 

ሰሜን ወጋገን /ስራ /ዩኒየን /የተወሰነ

 

በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በደቡብ ወሎ ዞን ደሴ ከተማ አስተዳደር፤ ጢጣ ቀበሌ የሚገኘውን የእርሻ ትራክተር (አሁን ባለበት ሁኔታ)

 

 

 

 

 

 

 

1,874,895.64

 

 

 

 

 

 

 

 

2

 

 

 

 

 

 

 

 

አርብ ጥቅምት 28 ቀን 2018 . ከጧቱ 400 ሰዓት እስከ 600 ሰዓት

 

ሞደል: –MF470-4WDXTRA

የቻንሲ ቁጥር፡-BY42007

የሞተር ቁጥር፡ HMD396050

የተመረተበት ሀገር፡ብራዚል

የፈረስ ጉልበት፡-120HP

የሰሌዳ ቁጥር: አማ/ልዩ/189

ማሽኑ የተመረተበት ዘመን: 2017 G.C

ብዛት፡ 01

የትራክተር ተሳቢ (አሁን ባለበት ሁኔታ)

ሞደል: RH60

Serial No.:- 05120010

የተመረተበት ሀገር፡ቱርከ

የመጫን አቅም፡ 6 ቶን

ማሽኑ የተመረተበት ዘመን: 2017 G.C

ብዛት፡ 01

ማሳሰቢያ

1. ተጫራቾች የድርድር ጨረታውን መነሻ ዋጋ 1/4 (አንድ አራተኛ) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ብቻ በማስያዝ የድርድር ጨረታ መወዳደር የሚችሉ ሲሆን የድርድር ጨረታ ሰነዱን በደሴ ቅርንጫፍ ቀርበው አንድ መቶ ብር (100) ከፍያ በመፈፀም መግዛት ይችላሉ።

2. አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 (በአስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል።

3. የድርድር ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ደሴ ዲስትሪክት ቅጥር ግቢ ሲሆን ንብረቱን በአካል ማየት የሚፈልግ ተጫራች በዲስትሪክቱ ቢሮ በመምጣት ማየት ይችላሉ።

4. አሸናፊው ድርጅት/ግለሰብ ባሸነፈበት ዋጋ ላይ የሚታሰብ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) እና ሌሎች ገዥ እንዲከፍላቸው በህግ የተወሰነ ታክስ እና ግብሮችን፣ የስም ማዞሪያ ከፍያን ጨምሮ ገዥው/የጨረታ አሸናፊው ይከፍላል።

5. ተጫራቾች የእርሻ ትራክተር መከስከሻ፣ የእርሻ ትራከተር እና የትራክተር ተሳቢ ግዥ ለመፈፀም በንብረቱ ላይ የቀረጥ እና ታክስ ነፃ መብት ያለው መሆኑን ከሚመለከተው የመንግስት አካል ማቅረብ የሚገባው ሲሆን ይህ መብት የሌለው ተጫራች በመንግስት የተቀመጠውን ቀረጥና ታክስ ክፍያ መፈፀም ይኖርበታል።

6. በድርድር ጨረታ ላይ መገኘት የሚችሉ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው፣ የታደሰ መታዊቂያ እና 1/4 (አንድ አራተኛ) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) መያዝ ይጠበቅባቸዋል።

7. የድርድር ጨረታ ሳጥኑ ግልፅ ሆኖ ውስጡ ባዶ መሆኑን የድርድር ተጫራቾች ከተመለከቱት በኋላ በስም በታሸገ ፖስታ የተዘጋጀውን ሰነድ የድርድር ጨረታ ሳጥኑ ውስጥ ማስገባት ይችላሉ።

8. ጨረታው የሚካሄድበት ቦታ በኢትዮጵያ ልማት ባንክ ደሴ ዲስትሪክት ቅጥር ግቢ ሲሆን ንብረቱን በአካል ማየት ለምትፈልጉ ተጫራቾች ጥቅምት 17 እና 18 ቀን 2018 ዓ.ም ደሴ ዲስትሪክት ድረስ በአካል በመምጣት ንብረቱ በተቀመጠበት ማቆያ ቦታ ከዲስትሪከቱ ሠራተኞች ጋር በጋራ በመሆን መጎብኘት ይችላሉ።

9. ዝርዝር እና ተጨማሪ መረጃን በተመለከተ የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ደሴ ዲስትሪክት አንደኛ ፎቅ በሚገኘው ሎን ወርከ አውት ቡድን ቢሮ ማግኘት ይቻላሉ ወይም በስልክ 033 312-48- 07/033-312-00-87 ደውሎ ማብራሪያ ማግኘት ይችላል።

10. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ደሴ ዲስትሪክት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *