የኢትዮጵያ ፖስታ የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ እና ሽያጭ ለመፈፀም ይፈልጋል


Reporter(Oct 22, 2025)
Addis Zemen(Oct 22, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የጨረታ ማስታወቂያ 

የጨረታ ቁጥር ግጨ 06/2018 ዓ.ም

የኢትዮጵያ ፖስታ ከዚህ በታች ከሎት እስከ ሎት 4 የተጠቀሱትን የጨረታ አይነቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ግዥ እና ሽያጭ ለመፈፀም ይፈልጋል።

ሠንጠረዥ 1. ገዥ እና ሽያጭ የሚፈፀምባቸው የጨረታ አይነቶች/

ተራ.ቁ

ሎት

የጨረታ አይነት

ብዛት

ሰነድ የሚመለስበት

የመክፈቻ ቀን

1

ሎት 1

የፖስታ መገልገያ እቃዎች ግዥ

 

ሰነድ የሚመለስበት ቀን ህዳር 03 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:30 እስከ ከቀኑ 6፡00 ሰዓት

የመክፈቻ ቀን በዕለቱ ህዳር 03 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ይከፈታል

ነጭ ታግ

220,000

ቀይ ታግ

110,000

ፍላየር ኢንቨሎፕ ትልቁ

45,000

ፕላስቲክ ፓሌት (pallet)

60

የፖስታ ማመላለሻ (ጋሪ) ዋግነር

17

የፖስታ ማመላለሻ ትንሹ (ጋሪ)

12

ፕላስቲክ ሲል ነጭ ኢኤም ኤስ

190,000

ፕላስቲክ ሲል ቀይ

100,000

ፕላስቲክ ሲል ኢትዮ ፖስት ነጭ

10,800

ካኪ ፕላስተር በሎጎ

18,0000

አድሬስ ሌብል

75,000

2

ሎት 2

የህትመት ወረቀት ግዥ

 

6ዐ ግራም ወረቀት

በሪም 500

የህትመት ወረቀት ግዥ 80 ግራም ወረቀት

በደስጣ 800

4

ሎት 3

ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ሽያጭ

 

አቶቡስ

3

አውቶሞቢል

1

ያገለገሉ ሞተር ሳይክሎች

12

ሊፋን ቫን

1

5

ሎት 4

የተለያዩ የመኪና መለዋወጫ አዲስ እቃዎች (spare part) ሽያጭ

 

ስለሆነም፡-

በዚህ ጨረታ ለመካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች በዘርፉ ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ ተጫራቾች አወዳድሮ መግዛትና መሸጥ ይፈልጋል። በመሆኑም በድርጅቱ ገንዘብ ቤት የማይመለስ ብር 300.00 (ሶስት መቶ ብር) በመክፈል ዋናው መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ግዥ ከፍል እየቀረቡ የጨረታ ሠነድ በመውሰድ ቴክኒካልና ፋይናንሻል ሰነድ ለየብቻ (በተናጠል) በማድረግ በጨረታ ሠነዱ ላይ በተገለጸው የሥራ ዝርዝር መሠረት ዋጋ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎኘ በማድረግ እስከ ህዳር 03 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 6፡30 ሰዓት ድረስ ሠነዱን ከገዙበት ቢሮ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል።

ሎት 1 እና ሎት 2 ላይ ለቀረቡት የፖስታ መገልገያ እቃዎች ናሙና/Sample/ ተጫራች በአካል በመገኘት ማየት የሚችል ሆኖ የእቃዎቹን ዝርዝር መግለጫ በመውሠድ ጭምር መወዳደር የሚችል መሆኑን እናሳውቃለን።

  • ተጫራቾች በቅድሚያ በየሎቱ ከሎት 1 ፣2 እና 4 ለተገለፁት የጨረታ አይነቶች ተመላሽ የሚሆን በሁኔታዎች ላይ ያልተመሠረተ የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ (CPO) 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር)፤ ለሎት 3 ማለትም ለአውቶቡስ እና አውቶሞቢል 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ) ብር ሲሆን ላገለገሉ ለሞተር ሳይክሎች 5,000.00 (አምስት ሺህ) ሎት በማሠራት ከቴክኒካል ኦርጅናል ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  • የጨረታው ኤንቨሎኘ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ህዳር 03 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡30 ሰዓት በድርጅቱ የሠራተኞች ክበብ ይከፈታል።
  • CPO (ሲፒኦ) ሲያሠሩ ፡- “የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት” ወይም ETHIOPIAN POSTAL SERVIC ENTERPRISE በማለት ያሠሩ

ድርጅቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 09 91 18 75 13 / 09 18 42 75 68 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።

የኢትዮጵያ ፖስታ