Your cart is currently empty!
በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽህፈት ቤት የቁም ደን ባለበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 24, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
የቁም ደን ምርት ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት በደቡብ ጎንደር ዞን ደራ ወረዳ ሁለቱ ወገዳሜ ቀበሌ ገልዳ ማዶ የመንግስት ደን ውስጥ ያለውን የፈ/ጽድ 889.41 ሜ/ኩብ እና ቀይ ባህርዛፍ 351.84 ሜ/ኩብ በድምሩ 1,241.25 ሜ/ኩብ ቁም ደን እና በደቡብ ወሎ ዞን ተሁለደሬና ደሴ ዙሪያ ወረዳዎች ባሉ የተለያዩ ቀበሌዎች የሚገኝ የመንግስት ደን ውስጥ ያለውን የፈ/ጽድ 3,209.30 ሜ/ኩብ፣ የነጭ ባህርዛፍ 17,422.43 ሜ/ ኩብ፣ የፈ/ግራር 16.25 ሜ/ኩብ እና የወደቀና የደረቀ 6.82 ሜ/ኩብ በድምሩ 20,654.80 ሜ/ኩብ ቁም ደን ባለበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል።
ስለሆነም ተጫራቾች:
1. ተጫራቾች በዘርፉ የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድና የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፍኬት ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል።
2. የሽያጩ መጠን 200,000.00/ሁለት መቶ ሺህ ብር በላይ ከሆነ የተእታ VAT ምዝገባ የምስክር ወረቀት ከጨረታ ሰነዱ ጋር ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
3. ለጨረታ የቀረቡትን ቁም ደን ምርቶች ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች ዘወትር በሥራ ሰዓት በቦታው ተገኝተው ማየት ይችላሉ።
4. የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 10 የስራ ቀናት ውስጥ/ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ/ በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት ባሕርዳር ቀበሌ 14 አዲሱ መናኸሪያ ጀርባ እንስሳት ማዳቀያ ግቢ ውስጥ ከኢንተርፕራይዙ ቢሮ ቁጥር 06 እና በሁሉም ቅ/ጽ/ቤቶች የማይመለስ 200 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መግዛት ይችላሉ።
5. ተጫራቾች ለመግዛት የሚፈልጉትን ምርት ጠቅላላ ዋጋ 2% የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond በባንክ የተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ/CPO/ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
6. ተጫራቾች መግዛት የሚፈልጉትን ቁም ደን በኦርጅናል ዋጋ መሙያ ቅጽ የሚገዙበትን ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ ፧ስምና አድራሻቸውን በመፃፍ ፈርመው በመሙያው ሰነዱ ላይ ማህተም በማስቀመጥ የታሸገውን የጨረታ ፖስታ በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 06፣ደ/ብርሃንና ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ‹‹የቁም ደን የጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ›› ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 10 የሥራ ቀናት (ቅዳሜ ግማሽ ቀን ጨምሮ) እስከ መጨረሻው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዚሁ ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ ሳጥኑ ታሽጎ በ4፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ይሁን እንጅ ተጫራቾች ባይገኙም ይከፈታል።
7. ተጫራቾች የሚሞሉት ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ 15% ተእታን አይጨምርም፡፡ ሆኖም አሸናፊው ባሸነፈበት ዋጋ ላይ 15% ተእታን ጨምሮ ይከፍላል።
8. ተጫራቾች ቁም ደኑን በተመለከተ ቅልቅል ደን ተብሎ የቀረበውን ሁሉንም ክፍልፋይ መሙላት ይጠበቅባቸዋል።
9. በሌላ ተጫራች ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም።
10. ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን በሙሉ ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
11. ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር ባ/ዳር 058 226 3095፣ ደ/ታቦር 058 44 10306፣ ደ/ብርሃን 011 637 5017፣ እንጅባራ 058 227 0485፣ ደ/ማርቆስ 058 871 9004፣ ኮ/ቻ 0914 716 636 ደውሎ መጠየቅ ይችላል።
የአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ዋና ጽ/ቤት