የሐዋሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት የተለያዩ ዕቃዎችን በግልፅ እና በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል


Addis Zemen(Oct 24, 2025)

Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።

የተተውና የተወረሱ ዕቃዎች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 13/2018

የሐዋሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን የሚገኙ በተለያዬ መንገድ በህገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀሱ ተይዘው የተወረሱ ንብረቶች ስለሚወገዱበት ሥርዓት በወጣው የዕቃ አወጋገድ መመሪያ ቁጥር 167/2012 አንቀጽ 4(1) መሠረት

  • የመገናኛ መሳሪያ ዕቃዎች
  • አልባሳትና ጨርቃጨርቅ፤ 
  • የኤሌክትሮኒክስ እና የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣
  • የንፅህና መጠበቂያና የመዋቢያ ዕቃዎች 
  • የቤትና ቢሮ ዕቃዎች የመኪና እና የሞተር ሳይክል አካላትና መለዋወጫ ዕቃዎች፣
  • ፍሩሽካ የከብት መኖ በግልፅ እና በሀራጅ ጨረታ ባሉበት ሁኔታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።

በመሆኑም በጨረታው መወዳደር የሚፈልጉ ተጫራቾች ስጨረታ የቀረቡትን የዕቃዎች ዝርዝር ከጨረታ ሰነዱ በማየት እና በማረጋገጥ የሚከተሉትን ዝርዝር መስፈርቶች ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

  1. ለጨረታ በቀረቡት ዕቃዎች ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጨራቾች በጨረታ ከሚሸጡት ዕቃዎች ጋር በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው/ያላት፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN) እና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ስለመሆኑ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል ሲሆን ከፍተኛ የመሸጫ ዋጋው ከብር 500 መቶ ሺህ በታች የሆነውን ማንኛውንም ዕቃ ለመግዛት የተጨማሪ እሴት ታክስ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ አይገደድም፡፡
  2. ማንኛውም ተጫራች የጨረታውን ሰነድ በጨረታ ማስታወቂያው ላይ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት ከሰኞ እስከ አርብ ጠዋት ከ2፡00 እስከ 6፡00 ፣ ከሰዓት ከ7፡00 እስከ 1100 ሰዓት፣ ቅዳሜ ከ2፡00 እስከ 6፡00 ሰዓት ድረስ በቅ/ጽ/ቤቱ ገቢ ሂሳብና ዋስትና አስተዳደር ቡድን በአካል በመገኘት መግዛት ወይም በሐዋሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ስም በተከፈተው ቀጥታ አካውንት (1000174515488) የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በማስገባት በስልክ ደውለው በማሳወቅና ስሊፕ በመላክ የጨረታ ሰነድ ባሉበት በቴሌግራም እንዲላክሎት ማድረግ ይቻላል፡፡
  3. ተጫራቾች ለጨረታው ማስከበሪያ የሚሆን በሐዋሳ ጉምሩክ ቅ/ጽ/ቤት ሥም የተዘጋጀ የሚጫረቱበትን ጠቅላላ ዋጋ 5% (አምስት በመቶ) በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የተመሰከረለትን CPO በማሰራት የጨረታ ሰነድ እና አጠቃላይ መረጃዎችን ጨረታው ከመከፈቱ በፊት በጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ በተጨማሪ ለሀራጅ ጨረታ ለመዋቢያና የንፅህና መጠበቂያ ዕቃዎች ብር 100,000( አንድ መቶ ሺህ)፣ የከብት መኖ ብር 30,000 (ሰላሳ ሺህ) እና ለቤትና የቢሮ ዕቃዎች ብር 30,000( ሰላሳ ሺህ) ( CPO) ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  4. ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጨረታ ሰነዱን በመግዛት እስከ 5ኛው (አምስተኛው) ቀን ድረስ የዕቃዎችን ናሙና ወይም ንብረቶችን በሀዋሳ ማዕከላዊ መጋዘን ላይ ማየት የሚችሉ ሲሆን ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ6ኛው (በስድስተኛው) ቀን ጠዋት 4፡00 ሰዓት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ 4፡05 በሐዋሳ ጉ/ቅ/ጽ/ቤት ነባሩ መጋዘን ቅጥር ግቢ ውስጥ በተዘጋጀው ቦታ ተከፍቶ ሂደቱ ካለቀ ከ10 ደቂቃ በኋላ የሀራጅ ጨረታው የሚጀምር ይሆናል፡፡ ነገር ግን ጨረታው በበዓል/እሁድ/ቀን የሚውል ከሆነ ጨረታው የሚካሄደው በተመሳሳይ ሰዓት የሚቀጥለው የስራ ቀናት ከላይ በተገለፀው ቦታ ይሆናል፡፡
  5. ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ በቀረበው ቅጽ ላይ ተጫራቹ ያቀረበው ዋጋ በሚለው ርዕስ ስር በተሰጠው ክፍት ቦታ ከነቫቱ በጨረታ ሰነዱ ግልፅ በሆነ መልክ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ ወይም ፖስታ መቅረብ አለባቸው፡፡ ከዚህ ሰነድ ውጭ በሌላ ሰነድ ተሞልቶ የሚቀርብን ዋጋ ቅ/ጽ/ ቤቱ ለመቀበል አይገደድም፡፡
  6. ማንኛውም የጨረታ ሽያጭ የዕቃው አስመጪ ወይም ባለቤት እና ቤተሰብ የነበሩ ሰዎች በጨረታው መሳተፍ አይችሉም፡፡ በተጨማሪ ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነድ ላይ የሰጠውን ዋጋ እና መግለጫ መለወጥ ወይም ማሻሻል አይችልም፡፡
  7. ማንኛውም ተጫራች የሰጠው የመወዳደሪያ ዋጋ የጨረታው ሂደት ተጠናቆ ቅ/ጽ/ቤቱ የጨረታውን ውጤት እስከሚያሳውቅ ድረስ ፀንቶ ይቆያል፡፡
  8. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ራሱን ከጨረታ ውድድር ማግለል አይችልም፡፡
  9. በጨረታው ለተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት CPO በዕለቱ የሚመለስላቸው ሲሆን አሸናፊው ያስያዘው ዋስትና ግን ከሽያጭ ጋር የሚታሰብለት ይሆናል፡፡
  10. ተጫራቾች የዕቃውን ናሙና ሳያዩ ለሚሰጡት ዋጋ ምክንያት ለሚፈጠር ቅሬታ በቅ/ጽ/ቤቱ ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
  11. ለጨረታ የቀረበው ዕቃ ሽያጭ የሚፈፀመው ባለበት ሁኔታ እና በተለየው ኮድ ነው፡፡
  12. አሸናፊው ተጫራቾች ማሸነፋቸውን በውስጥ ማስታወቂያ ከተገለፀበት ቀን ጀምሮ በ5 (አምስት) የስራ ቀናት ውስጥ የአሸነፉበትን ገንዘብ ገቢ በማድረግ ዕቃዎችን ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡ይህንን ባያደርጉ ጨረታው ተሠርዞ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለቅ/ጽ/ቤቱ ገቢ በማድረግ ዕቃው ድጋሚ ጨረታ ላይ የሚወጣ ይሆናል፡፡
  13.  ቅ/ጽ/ቤቱ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

በለጠ መረጃ የስልክ ቁጥር፡-046-212-5396/046-212-6505

በጉምሩክ ኮሚሽን የሀዋሳ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት