Your cart is currently empty!
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 አስተዳደር የፋይናንስ ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት በአስተዳደር ለሚያሠራው የግንባታ ሥራ የተለያዩ የግንባታ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 25, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁፕር 1212/2018
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 አስተዳደር የፋይናንስ ጽ/ቤት የ2018 በጀት ዓመት በአስተዳደር ለሚያሠራው የግንባታ ሥራ የተለያዩ የግንባታ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
- በተለያዩ የሕንፃ ግንባታ የሚውል የብረት ዓይነቶችን፣
- የተለያዩ ዓይነት የመሬትና የግርግዳ ሴራሚክ እቃዎች፣
- የተለያዩ የመብራት እቃዎች ግዢዎች፣
ማሳሰቢያ፡-
1. ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥርና የቫት ሰርተፊኬት የዘመኑን ግብር የተከፈሉበት ሕጋዊ ማስረጃ ያላቸው ሊሆኑ ይገባል፡፡
2. ተጫራቾች ከላይ ከተዘረዘሩት ለሁለት ወይም ከዚያ በላይ ለሆኑ ዕቃዎችና ቁሳቁሶች የሚወዳደሩ ከሆነ ለእያንዳንዱ ዘርፍ ያወጡት ህጋዊ የንግድ ሥራ ፈቃድ በአቅራቢነት ዝርዝር የተመዘገቡትን ሰርተፊኬት ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
3. ተጫራቾች በገንዘብ እና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በአቅራቢነት ሊስት ውስጥ የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል፣ ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
4. ተጫራቾች የጥቃቅንና አነስተኛ አንቀሳቃሾች ከሆኑበት ጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁበትን እና ሕጋዊ ሰርተፊኬት ከአደራጁ መሥሪያ ቤት የተሰጣቸውን ወቅታዊ የድጋፍ ደብዳቤ ከሌሎች ዶክመንቶች ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ዕለት ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የሥራ ቀናት በመደበኛ የሥራ ሰዓት ከጽ/ቤቱ 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በጥንቃቄ በመሥሪያ ቤቱ ፍላጎት መሰረት ብቻ በመሙላት የተሟላ የመወዳደሪያ ሰነድ ኦሪጅናልና ኮፒ በሁለት የተለያየ ፖስታ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ማስገባት ይኖርባቸዋል፣ የሚያስገቡት ዋጋ በነጠላ ቫትን ያካተተ መሆን ይኖርበታል፡፡
7. የጨረታ ሳጥኑ በአስረኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ሰዓት ተዘግቶ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው ባሉበት በወረዳው ፋይናንስ ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡
8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና አጠቃላይ እቃዎች የዋስትና ማስያዣ ዋጋ 50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
9. ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለጹትን ማንኛውም ሁኔታ መለወጥ ወይም ማሻሻል ወይንም ከጨረታ ራሱን ማግለል አይችልም፡፡
10. ተጫራቾች አሸናፊ የሆኑባቸውን እቃዎች እስከመሥሪያ ቤቱ የንብረት ክፍል ድረስ በራሳቸው ማጓጓዣና የጉልበት ወጪ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
11. መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው፡፡
መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 011 557 4183 በመደወል ወይንም ኦሎምፒያ አካባቢ ከጌቱ ኮሜርሻል ሴንተር በጀርባ በኩል ከሚገኘው ወረዳው አስተዳደር ጽ/ቤት ህንጻ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 1 በመምጣት መጠየቅ ይቻላል።
የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ወረዳ 01 አስተዳደር የፋይናንስ ጽ/ቤት