Your cart is currently empty!
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ. ንብረቶች በግልፅ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Reporter(Oct 26, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
የሐራጅ ማስታወቂያ
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ. በአዋጅ ቁጥር 97/1990 እና 216/1992 እንዲሁም በአዋጅ ቁጥር 1147/2011 በተሰጠው ስልጣን መሰረት በሰንጠረዡ ላይ የተዘረዘሩትን ንብረቶች በግልፅ ሐራጅ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
ሀ. ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ
|
ተ.ቁ |
የተበዳሪው ስም |
የንብረት አስያዥ ስም |
አበዳሪ ቅርንጫፍ |
የንብረቱ አድራሻ |
የቦታው ስፋት |
የባለቤትነት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት |
የንብረቱ ዓይነት |
የጨረታ መነሻ ዋጋ |
ጨረታው የሚከናወንበት ቦታ፣ ቀን እና ሰዓት |
||
|
ከተማ |
ወረዳ |
ቀበሌ |
|||||||||
|
1 |
አቶ ገብረሂወት ከበደ የዕብዮ |
አቶ ገብረሂወት ከበደ የዕብዮ |
የጭላ |
የጭላ |
የጭላ |
– |
250 ካ/ሜ |
8005/004/ መ/ም/ማ/013 |
መኖሪያ |
1,252,650.27 |
ጨረታው የሚከናወነው በባንኩ የጭላ ቅርንጫፍ ታህሳስ 01/2018 ከቀኑ 8፡00-10፡00 ድረስ ይሆናል:: |
ለ. ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ
|
ተ.ቁ |
የተበዳሪው ስም |
የንብረት አስያዥ ስም |
አበዳሪ ቅርንጫፍ |
የንብረቱ አድራሻ |
የቦታው ስፋት |
የባለቤትነት ማረጋገጫ ምስክር ወረቀት |
የንብረቱ ዓይነት |
የጨረታ መነሻ ዋጋ |
ጨረታው የሚከናወንበት ቦታ፣ ቀን እና ሰዓት |
|||
|
ከተማ |
ክ/ከተማ |
ወረዳ |
ቀበሌ |
|||||||||
|
1 |
ዳንኤል ጌታቸው/ራዳር ኮንስትራክሽን/ |
ዳንኤል ጌታቸው/ራዳር ኮንስትራክሽን/ |
የካ |
መቀሌ |
ዓዲሓቂ |
– |
– |
250 ካ/ሜ |
592/32623 |
G+1 መኖሪያ ቤት |
12,325,956.69 |
ጨረታው ሚከናወነው በመቀሌ ከተማ በሚገኘው በባንኩ ሰሜን/ግእዝ ሪጅን መስሪያ ቤት ህዳር 18 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00-6፡00 ድረስ ይሆናል:: |
|
2 |
አቶ ብርሃነ ገ/መድህን |
አቶ ብርሃነ ገ/መድህን እና አቶ ገብረየሱስ ገ/መድህን |
ካዛንቺስ |
መቀሌ |
ሰሜን |
– |
– |
248 ካ/ሜ |
1009/01/3816 |
መኖሪያ ቤት |
12,572,401.60 |
ጨረታው ሚከናወነው በመቀሌ ከተማ በሚገኘው በባንኩ ሰሜን/ግእዝ ሪጅን መስሪያ ቤት ህዳር 18 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00-10፡00 ድረስ ይሆናል:: |
|
3 |
አቶ ሓዱሽ ተወልደብርሃን ገብረመስቀል |
አቶ ሓዱሽ ተወልደብርሃን ገብረመስቀል |
ሰለኽለኻ |
መደባይ ዛና |
– |
መደባይ ዛና |
ዓዲ ቀማልክ |
አንድ ሄክታር |
002434/2011 |
የኢንቨስትመንት ልማት የእንስሳት ማደለቢያ |
2,421,806.72 |
ጨረታው የሚከናወነው በባንኩ ሰለኽለኻ ቅርንጫፍ ታህሳስ 02 ቀን 2018 ከቀኑ 8፡00-10፡00 ድረስ ይሆናል:: |
ሐ. ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የሐራጅ ማስታወቂያ
|
ተ.ቁ |
የተበዳሪው ስም |
የንብረት አስያዥ ስም |
አበዳሪ ቅርንጫፍ |
የመኪናው መግለጫ |
የጨረታ መነሻ ዋጋ |
ጨረታው የሚከናወንበት ቦታ፣ ቀን እና ሰዓት |
||||
|
የመኪናው ዓይነት
|
የሰሌዳ ቁጥር |
የሞተር ቁጥር |
የሻንሲ ቁጥር |
የተሰራበት ዓ.ም |
||||||
|
1 |
ዳንኤል ጌታቸው/ራዳር ኮንስትራክሽን/ |
ዳንኤል ጌታቸው/ራዳር ኮንስትራክሽን/ |
የካ |
ገልባጭ |
ኢ.ት-03-77982 |
F2CE0681 B*B0521 4H00078488* |
LZFF25T44 ED297030 |
እ.ኤ.አ 2015 |
4,750,000 |
ጨረታው ሚከናወነው አዲስ አበባ ከተማ 22 አካባቢ በሚገኘው በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ህዳር 3 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00-10፡00 ድረስ ይሆናል። |
|
2 |
አቶ ሙልጌታ ታደሰ(ማን ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ) |
አቶ ሙልጌታ ታደሰ(ማን ጠቅላላ ስራ ተቋራጭ) |
መሳለሚያ |
ገልባጭ |
ኢ.ት-03-93946 |
WD615.69*17 0617003857* |
LZZ5ELNB 3HD244975 |
እ.ኤ.አ 2017 |
4,000,000 |
ጨረታው ሚከናወነው አዲስ አበባ ከተማ 22 አካባቢ በሚገኘው በባንኩ ዋና መስሪያ ቤት ህዳር 2 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00-6፡00 ድረስ ይሆናል። |
ማሳሰቢያ
1. ተጫራቾች የጨረታ መነሻ ዋጋ አንድ አራተኛ (1/4ኛ) ወይም 25% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ሰነድ (CPO) ብቻ በአንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አ/ማ ስም በማሰራትና ለጨረታ ማስከበሪያነት በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።
2. በፊደል ሐ ላይ እሰከ 07/02/2018 ዓ/ም ድረስ በተ/ቁ 1 ላይ የተመለከተው ተሽከርካሪ ያልተከፈለ የቀረጥ እና ታክስ ብር 200,134.24 በተ/ቁ 2 ላይ የተመለከተው ተሽከርካሪ ብር 396,411.35 አለባቸው።
3. የተጫራቾች ምዝገባ የሚከናወነው በጠዋቱ ክፍለ ጊዜ 4፡00 – 5:30፣ በከሰዓቱ ከ 8፡00-9፡30 ድረስ ይሆናል። ምዝገባው ከተጠናቀቀ በኋላ ለንብረቱ የሚመደበው የጥሪ ስዓት 30 ደቂቃ ብቻ ሲሆን የጨረታው መጠናቀቂያ ሰዓት ድረስ አሸናፊው ካልተለየ አሸናፊ እስኪለይ ድረስ ጨረታው የሚቀጥል ይሆናል።
4. በጨረታው የተሻለ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች ጨረታውን ከሚያካሂደው የባንኩ የህግ አገልግሎት መምሪያ ማሸነፉን የሚገልጽ ደብዳቤ ሲደርሰው ብቻ አሸናፊ ይባላል።
5. የጨረታው አሸናፊ ቀሪውን ገንዘብ አሸናፊነቱ በደብዳቤ ከተገለጸበት ቀን ጀምሮ በአስራ አምስት (15) ቀናት ውስጥ አጠቃሎ መክፈል ይኖርበታል፡፡ በእነዚህ ቀናት ውስጥ ካልከፈለ የሐራጁ ውጤት ተሰርዞ ለጨረታ ማስከበሪያ በሲ.ፒ.ኦ (CPO) ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ይሆናል᎓᎓ በጨረታው የተሸነፉ ተጫራቾች ያስያዙት ገንዘብ ይመለስላቸዋል።
6. የጨረታው አሸናፊ ካሸነፈበት ዋጋ ላይ 15% (አስራ አምስት በመቶ) ተጨማሪ እሴት ታክስ ጨምሮ ይከፍላል።
7. ለጨረታ የቀረቡትን ንብረቶች ለመጎብኘት የሚፈልግ ማንኛውም ተጫራች የጨረታው ቀን ከመድረሱ ከ7 (ሰባት) የስራ ቀናት አስቀድሞ ከባንኩ ጋር ቀጠሮ በማስያዝ መጎብኘት ይችላል።
8. በሐራጅ ጨረታው ላይ መገኘት የሚችሉት ተጫራቾች፣ ተበዳሪዎች እና ንብረት አስያዥ ወይም የነዚህ ሕጋዊ ተወካዮች ብቻ ናቸው:: ተበዳሪዎች እና ንብረት አስያዦች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው የጨረታዉን ሂደት ለመከታተል በተጠቀሰዉ ቦታ እና ሰዓት እንድትገኙ እያሳሰብን ካልተገኛችሁ በሌላችሁበት ጨረታው የሚከናወን መሆኑን እንገልፃለን።
9. ባንካችን ንብረቱ በገዢው ስም እንዲዞር ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይፅፋል።
10. ከሚሸጠው ንብረት ጋር የተያያዙ ከጨረታው በፊት ሆነ በኋላ ያለው ውዝፍ ማንኛውም ለመንግስት ሊከፈሉ የሚገባቸው የሊዝ ክፍያዎች፣ ወጪዎች ወይም ግብር/ቀረጥ እንዲሁም በንብረት ማስተላለፍ ሂደት የሚመጡ ማንኛውም አይነት ክፍያዎች ወይም ግብር ሙሉ በሙሉ የጨረታ አሽናፊው/ገዥው/ የሚሸፍን ይሆናል።
11. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
12. ለበለጠ ማብራርያ ወይም የጉብኝት ቀጠሮ ለማመቻቸት አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ ዋና መ/ቤት ሕግ አገልግሎት መምሪያ በስልክ ቁጥር 011-662-7120፣ በመደባይ ዛና ለሚገኘው ንብረት በባንኩ የሰለኽለኻ ቅርንጫፍ በኩል ወይም በ 0914492789 በመደወል፣ በባንኩ በየጭላ ቅርንጫፍ በኩል ወይም 0933371487 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
አንበሳ ኢንተርናሽናል ባንክ አ.ማ.