Your cart is currently empty!
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የተለያዩ ንብረቶች በዝግ ጨረታ እና ድርድር ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Reporter(Oct 26, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ በአዋጅ ቁጥር 97/90፣ 216/92 እና 1147/2011 መሰረት በብድር ዕዳ ምክንያት የተረከባቸውን ከዚህ በታች በሰንጠረዡ የተዘረዘሩትን ንብረቶች በዝግ ጨረታ እና ድርድር ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
|
ተ.ቁ |
የተበዳሪው የመያዣ ሰጪው ስም |
የንብረት/ፕሮጀክት አድራሻ |
የንብረት/ፕሮጀክት ዝርዝር |
የቦታ ስፋት (በሄክታር) |
የጨረታ መነሻ ዋጋ (ብር) |
የጨረታ ሁኔታ |
የጨረታ ደረጃ
|
ጨረታው የሚካሄድበት ቀንና ሰዓት |
|
1 |
ኤም ዋይ ሹዝ ኤንድ ሌዘር ማኑፋቸሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማ |
አማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ደብረ ብርሃን ከተማ 09 ቀበሌ |
የጫማ እና የቆዳ ማምረቻ ፋብሪካ በትግበራ ላይ ያለ) የህንፃ ግንባታዎች፣ ማሽነሪዎች እና የኤልክትሪክ ሥራዎች |
6.83. ሄክታር
|
ብር 397,968,817.12 (ሦስት መቶ ዘጠና ሰባት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ስልሳ ስምንት ሺህ ስምንት መቶ አስራ ሰባት ብር ከአስራ ሁለት ሳንቲም) |
ዝግ
|
ሁለተኛ
|
ህዳር 23 ቀን 2018 ዓ.ም ከጥዋቱ 4፡00- 6:00 ሰዓት |
|
2 |
አቶ ግርማ አፈወርቅ መድምም |
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንፋስ ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 08 ቀበሌ 11
|
ጋቴፕሮ ቆርቆሮ ፋብሪካ፣ የህንፃ ግንባታዎች የኤልክትሪክ ስራዎች፣ ማሽነሪዎች፣ ቁሳቁሶች፣ የቢሮ ዕቃዎችና መገልገያዎች፣ የጥሬ ዕቃና የምርት ክምችት |
1,678 ካሬ ሜትር በሊዝ የተገኘ መሬት |
122,600,997.28 (አንድ መቶ ሃያ ሁለት ሚሊዮን ስድስት መቶ ሺሀ ዘጠኝ መቶ ዘጠና ስባት ብር ከሃያ ስምንት ሳንቲም)
|
ድርድር
|
አንደኛ
|
ህዳር 22 ቀን 2018 ዓ.ም ከጥዋቱ 4፡00- 6:00 ሰዓት |
ማሳሰቢያ፤
1. ተጫራቾች የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ በመግዛት ንብረቶቹን የሚገዙበትን ዋጋ፣ ስምና አድራሻቸውን በፎርማቱ ላይ በመጥቀስ በባንኩ ዋና መ/ቤት ሁለተኛ ታወር ምድር ቤት ለዚሁ ጨረታ በተዘጋጀዉ ሣጥን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣ ከሦስተኛው ቀን ጀምሮ ለኤም ዋይ ሹዝ ኤንድ ሌዜር ፋብሪካ እስከ ህዳር 23 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 3፡50 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይችላሉ እና ለቆርቆሮ ፋብሪካ ህዳር 22 ቀን 2018 ዓ.ም ከ4፡00-6፡00 ባለው ጊዜ ውስጥ ቀርበው መደራደር ይችላሉ።
2. ተጫራቾች የጨረታውን መነሻ ዋጋ 10 በመቶ በባንክ ክፍያ ማዘዣ /ሲ.ፒ.ኦ/ ብቻ በማስያዝ መጫረት ይችላሉ።
3. አሸናፊ የሆነው ተጫራች ያሸነፈበትን ቀሪ ገንዘብ በ15 /በአስራ አምስት/ ተከታታይ ቀናት ውስጥ አጠቃሎ ካልከፈለ ያስያዘው ገንዘብ ለባንኩ ገቢ ሆኖ ጨረታው ይሰረዛል።
4. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በሰንጠረዡ በተመለከተው ቀንና ሰዓት በባንኩ ዋናው መ/ቤት ታወር ሁለት 5ኛ ፎቅ በሚገኘው መሰብሰቢያ አዳራሽ ይካሄዳል። ህጋዊ ሰውነት ያላቸው አካላትን ወከሎ በጨረታው ለመሳተፍ የሚቀርብ ሰው የማህበሩ መመስረቻ ጽሁፍ/መተዳደሪያ ደንብ ከእነ ማሻሻያዎቹ(ካለ)፣ የንግድ ምዝገባ፣ የንግድ ፍቃድ፣ ሌሎች አስፈላጊ ማስረጃዎችን እና የተረጋገጠ የውክልና ስልጣን ሰነዶችን ይዞ መቅረብ ይኖርበታል።
5. 15% የተጨማሪ እሴት ታክስና ሌሎች ገዢ እንዲከፍላቸው በሕግ የተወሰኑ ክፍያዎችን፣ የስም ማዛወሪያ ክፍያን ጨምሮ ገዢው ይክፍላል።
6. አንዳንድ የድርጅቶቹ ንብረቶች የጉምሩክ ቀረጥና ታክስ ያልተከፈለባቸው ስለሆኑ ገዢው የቀረጥ ነጻ መብት ሊኖረው አሊያም የሚፈለገውን ቀረጥ/ታክስ ለመንግስት ለመክፈል ይገደዳል።
7. ተጫራቾች ንብረቱን ለመጎብኘት ከፈለጉ አስቀድሞ ከባንኩ ጋር ቀጠሮ በመያዝ ከጨረታው ቀን በፊት መጎብኘት ይችላሉ።
8. የንብረቱ ስሙ–ንብረት ለገዥው እንዲዞር ባንኩ ለሚመለከተው መንግስታዊ አካል ደብዳቤ ይፅፋል። ገዥው ጉዳዩን ተከታትሎ ያስፈፅማል።
9. ባንኩ ንብረቶቹን የሚሸጠው ሙሉ በሙሉ በጥሬ ገንዘብ ይሆናል።
10. በጨረታው ዝርዝር እና ተጨማሪ መረጃን ለማግኘት የኢትዮጵያ ልማት ባንክ ዋና መ/ቤት ታወር ሁለት ሦስተኛ ፎቅ ላይ በሚገኘው የኦንጎይንግ ኮንስርን ፕሮጀክትስ እና አኳየርድ አሴትስ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ ወይም በስልክ ቁጥር 011-524-5373/ 011-524-4269 ደውሎ ማግኘት ይቻላል። የመያዣ ንብረቶቹን መጐብኘት የሚፈልግ ከዳይሬክቶሬቱ ጋር አስቀድሞ ቀጠሮ በመያዝ መጐብኘት ይቻላል።
11. ባንኩ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ