Your cart is currently empty!
የኦሮሚያ ስቲል ፓይፕ ሚል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ የተለያየ የስፋት መጠን ያላቸው የብረት ቧንቧዎች (ከ3 ኢንች እስከ 24 ኢንች ወይም ከ 88.3- 609 ሚሊ ሜትር) የብረት ቧንቧዎች በግምት 750 ቶን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 26, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ለኮንስትራክሽን፣ ለመስኖ ውሃ ማስተላለፊያ፣ ለተለያዩ አይነት ፍሳሽ ማስወገጃና ለሌሎች
አገልግሎቶች የሚውሉ የብረት ቧንቧዎች ሽያጭ ጨረታ ማስታወቂያ
ፋብሪካችን የተለያየ የስፋት መጠን ያላቸው የብረት ቧንቧዎች (ከ3 ኢንች እስከ 24 ኢንች ወይም ከ 88.3- 609 ሚሊ ሜትር) የብረት ቧንቧዎች በግምት 750 ቶን በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ሕጋዊ የታደሰ የንግድ ፍቃድ ያለውና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ ድርጅቶች/ግለሰቦች ማስረጃቸውን በመያዝ 100 ብር በመክፈል የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ከኩባንያው ፋይናንስ ዳይሬክቶሬት 3ኛ ፎቅ ቁጥር 301 በመውሰድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ ጥቅምት 28 ቀን 2018 ዓ.ም. ከቀኑ 5፡00 ሰዓት ለጨረታው በተዘጋጀ ሣጥን ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 5፡30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጨረታ ሰነዱ ውስጥ በተጠቀሰው አድራሻ ይከፈታል።
ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የምትሹ ተወዳዳሪዎች አንዱን ኪሎ ግራም ወይም አንድ የምትገዙበትን ዋጋ በመግለጽ ከጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ብር 300,000.00 (ሶስት መቶ ሺህ) በሲፒኦ ወይም በባንክ ዋስትና ጋር በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማሸግ ቦሌ መንገድ የኦሮሚያ ፕሬዚዳንት ጽ/ቤት ፊት ለፊት በሚገኘው ብትወደድ ባህሩ አብርሃም ህንጻ 3ኛ ወለል በሚገኘው የኩባንያው ጽ/ቤት ማቅረብ አለባቸው።
የጨረታው አሸናፊ ድርጅት/ግለሰብ አሸናፊ መሆናቸው ከተገለጸላቸው ቀን አንስቶ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የራሳቸው ትራንስፖርት በማቅረብ የብረት ቧንቧዎችን ማንሳት ይጠበቅባቸዋል።
በተጠቀሰው ጊዜ ውስጥ የገዙትን የብረት ቧንቧዎች የማያነሱ ከሆነ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለኩባንያው ገቢ ሆኖ ኩባንያው ሌላ ጨረታ በማውጣት የሚሸጥ መሆኑን ያስታውቃል።
ኩባንያው ሌላ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስልክ ቁጥር፣ 251-552 2681 / 251-552 2731
የኦሮሚያ ስቲል ፓይፕ ሚል ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ኩባንያ