Your cart is currently empty!
መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር ፓኔል /panel/ እና ስካፎልድንግ /scaffolding with all accessories/ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Oct 28, 2025)
ከስር የተቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ። Please read the detailed instructions below.
የጨረታ ማስታወቂያ
የሰነድ ቁጥር ጥቅ07/2018
ድርጅታችን መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር አያት በሚገኘው ሳይቱ ላይ እጅግ ዘመናዊ የሆነ ለአረጋውያኑ – ለአዕምሮ ህሙማኑ መኖሪያ የሚሆን ፎቅ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ ስለሆነም ለዚህ ግንባታ የሚውል ፓኔል/panel እና ስካፎልድንግ /scaffolding with all accessories በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱ ጋር አካተው ማቅረብ ያለባቸው ሰነዶች፣
በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድና ዋና ምዝገባ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (Tin Number) ያላቸው የጨረታ ማስረከቢያ ብር 100,000.00 (አንድ መቶ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማሲያዝ ይኖርባቸዋል፤ አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፉበትን የጠቅላላ ዋጋውን 10% የስራ አፈፃፀም ዋስትና በቅድሚያ ማሲያዝ ይኖርባቸዋል፤ ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ማቅረብ የሚችሉ የሚያቀርቡትን ዋጋ የጨረታ ሰነዱን ከማዕከላችን ቢሮ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በመግዛት ወስደው ሞልተው በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማቅረብ አለባቸው፤ ይህ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 14 ቀናት አየር ላይ ቆይቶ በ15ኛው ቀን ከቀኑ 8፡30 ተዘግቶ በእለቱ በ9፡00 ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን 15ኛው ቀን እሁድ ወይም በዓል ከሆነ በሚቀጥለው ቀን ይሆናል፡፡ ድርጅቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡– 8131 ይደውሉ፡፡
መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር