Your cart is currently empty!
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ዋና ኦዲተር መ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚዉሉ የተለያዩ እቃዎች መግዛት ይፈልጋል
Be’kur(Oct 27, 2025)
Please read the detailed instructions below. ከስር የተጠቀመጠውን እያንዳንዱን መረጃ በጥንቃቄ ያንብቡ።
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 02/2018
የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ዋና ኦዲተር መ/ቤት ለ2018 በጀት ዓመት አገልግሎት የሚዉሉ የተለያዩ እቃዎች
- ሎት 1 የጽህፈት መሣሪያዎች፣
- ሎት 2 የጽዳት እቃዎች፣
- ሎት 3 ኤሌክትሮነክስ እቃዎች፣
- ሎት 4 ፈርኒቸር የቢሮ መገልገያ መሳሪያዎች፣
- ሎት 5 የመኪና መለዋወጫና ዲኮር፣
- ሎት 6 የመኪና ጎማ ከነ ከለመዳሪ፣
- ሎት 7 የብስክሌት ጎማ ከነ ካለማደሪያ፣
- ሎት 8 ህትመት (ላይት ቦክስ) ፣
- ሎት 9 ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች አመታዊ ጥገና እንዲሁም
- ሎት 10 የእንጨትና ብረታ ብረት እቃዎች አመታዊ ጥገና የመሳሰሉትን ግዥ ለመፈፀም በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ።
- የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ የሚወዳደርበት ሎት ጠቅላላ ዋጋ ከብር 200,000 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የቫት ተመዝጋቢነት ማስረጃ እና የተጨሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢነት ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- በጨረታው ለመሣተፍ የሚፈልጉ የተጫራቾች መመሪያውንና የእቃዎችን ዝርዝር የሚገልጽ ሰነድ ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሰራ ሰዓት የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከአብክመ ዋና ኦዲተር መ/ቤት ገንዘብ ያዥ ቢሮ ቁጥር 009 ባ/ዳር መውሰድ ይችላሉ።
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ከጠቅላላ ዋጋው አንድ በመቶ ያላነሰ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ (ሲፒኦ) ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ወይም ከጨረታው መዝጊያ ሰዓት በፊት ገቢ መደረግ ይኖርበታል።
- ስለጨረታው ዝርዝር ሁኔታ በተጫራቾች መመሪያ ላይ የሚገለጽ ይሆናል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዳቸው ላይ በእያንዳንዱ ገጽ ማህተማቸውን በማስፈርና በጥንቃቄ በታሸገ ኢንቬሎፕ ዋና እና ቅጅ ሰነዶችን ለየብቻ በማሸግ ለአብክመ ዋና ኦዲተር መ/ቤት ቢሮ ቁጥር 013 ለዚሁ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ሳጥኑ የሚዘጋው የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ በ3፡30 የሚዘጋ ሲሆን በዚሁ እለት ከረፋዱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፤ ሆኖም ግን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ጨረታውን ከመክፈት የሚያግድ ነገር አይኖርም።
- የርክክብ ቦታ ባ/ዳር ከተማ መ/ቤቱ ድረስ በግንባር በመቅረብ ይሆናል።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፈል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሀሳብ ላይ ግዥዉ በቀረበዉ ዝርዝር መሰረት የእቃዉን ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ የአንዱ ዋጋ እና ጠ/ዋጋ መሞላት አለበት።
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 058 220 89 65 ደውሎ መረጃ መጠየቅ እና በተቋሙ ዌዩቭሳይት ANRSOAG.GOV.ET ባ/ዳር ማየት ይችላሉ።
የአብከመ ዋና ኦዲተር መ/ቤት
ባሕር ዳር
cttx Advertising and Promotion cttx, cttx Billboards and Digital Advertising cttx, cttx Cleaning and Janitorial Equipment and Service cttx, cttx Computer and Accessories cttx, cttx Electrical, cttx Equipment and Accessories cttx, cttx Furniture and Furnishing cttx, cttx House Furniture cttx, cttx IT and Telecom cttx, cttx Maintenance and Repair cttx, cttx Metal and Metal Working cttx, cttx Office Furniture cttx, cttx Office Machines and Accessories cttx, cttx Office Machines and Computers cttx, cttx Office Supplies and Services cttx, cttx Other Metals cttx, cttx Others cttx, cttx Printed Advertising Materials cttx, cttx Printing and Publishing cttx, cttx Promotional Items cttx, cttx Spare Parts and Car Decoration Materials cttx, cttx Stationery cttx, cttx Steel, cttx Tri Wheeler, cttx Wood and Wood Working cttx, Electromechanical and Electronics cttx, Metals and Aluminium cttx, Motorcycles and Bicycles Purchase cttx