Your cart is currently empty!
በ/ማ/ኢ/ክ/መ/በጉራጌ ዞን ቸሀ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለሴክተር መ/ቤት አገልግሎት የሚውል ሞተር ሳይክል፣ የተለያዩ ወንበሮች፣ ኤሌክትሮኒክ፣ የውሀ እቃዎች መለዋወጫ እና ቆርቆሮ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
Addis Zemen(Feb 04, 2026)
የጨረታ ማስታወቂያ 002/18
በ/ማ/ኢ/ክ/መ/በጉራጌ ዞን ቸሀ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለሴክተር መ/ቤት አገልግሎት የሚውል
- lote one ሞተር ሳይክል፣
- lote two የተለያዩ ወንበሮች
- lote three ኤሌክትሮኒክ
- lote four የውሀ እቃዎች መለዋወጫ
- lote five ቆርቆሮ በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
ስለሆነም፤
1. በየንግድ ዘርፉ የተሰማራችሁ ተወዳዳሪዎች የዘመኑ ግብር የከፈላችሁ የታደሰ ንግድ ፈቃድና የምዝገባ ምስክር ወረቀት የቫት ተመዝጋቢ እንዲሁም የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት ማስረጃ ማቅረብ የምትችሉና ከዚህ በፊት በጨረታ ያልታገዳችሁ፤
2. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት የጨረታውን ሰነድ ቸሀ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 7 በመቅረብ የማይመለስ ለእያንዳንዱ ብር 200 ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት የምትችሉ መሆኑ፤
3. ተጫራቾች የጨረታ ዶክመንታችሁ ላይ በእያንዳንዱ ገጽ ላይ የድርጅቱ ማህተምና ፊርማ በማድረግ ከላይ በተራ ቁጥር 1 ላይ የተዘረዘሩ ማስረጃዎች ኦርጅናል ሰነድና ኮፒ በተለያዩ በታሸጉ ፖስታዎች በማድረግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ማስገባት አላባችሁ።
4. ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ /21/ሃያ አንድ ቀናት አየር ላይ ይውላል እስከዚያ ድረስ የጨረታ ዶክመንታችሁን ማስገባት ይኖርባችኋል፤ ጨረታው የሚያበቃው የመጨረሻው ቀን ከቀኑ 8:00 /ስምንት ሰዓት ሲሆን የሚከፈተው በዚሁ ቀን ከቀኑ 8፡30 ስምንት ተኩል ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሲሆን ባይገኙም ጨረታው ለመክፈት የሚያግድ የሌለ መሆኑን እየገለጽን በዓል ቅዳሜና እሁድ ከሆነ የሚቀጥለው የሥራ ቀን ይተላለፋል።
5. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ገንዘብ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ሞተር ሳይክል /30,000/ ሰላሣ ሺህ ብር ፤ የተለያዩ ወንበሮች 20,000 /ሃያ ሺህ/ ኤሌክትሮኒክስ 30,000 /ሰላሣ ሺህ ብር፤ የውሀ እቃዎች 20,000 /ሃያ ሺህ ብር/ የቆርቆሮ 20,000/ሃያ ሺህ ብር/ ብቻ ማስያዝ ይኖርባችኋል።
6. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ማሳሰቢያ ፡ የአቅራቢነት የምስክር ወረቀት በኦላይን የተመዘገባችሁ ብቻ በጨረታው የምትሳትፉ ሲሆን ከዚህ ውጭ የሚመጣ ተጫራች ከጨረታ ውጭ ይሆናል።
ለበለጠ መረጃ 011 331 0812/011 331 0254 በ / ማ /ኢ/ክ/መ/በጉራጌ ዞን ቸሀ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ ቤት