በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ስር የሚገኛው የመሿለኪያ ጤና ጣቢያ የጨረታ ማስተካከያ አውጥቷል


Addis Zemen(Feb 05, 2026)

ማስተካከያ

ጥር 25 ቀን 2018 ዓ.ም በወጣው አዲስ ዘመን ጋዜጣ ገጽ 32 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቂርቆስ ክ/ከተማ ጤና ጽ/ቤት መሿለኪያ ጤና ጣቢያ ያወጣው የጨረታ ቁጥር 02/2018 የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ የመጀመሪያው የጨረታ ማስታወቂያ ሣይካተት የወጣ በመሆኑ በዚህ ማስተካከያ የተስተካከለ መሆኑን እየገለፅን የጨረታው ፈቻ ቀን ይህ ማስታወቂያ ማስተካከያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ 10ተከታታይ የሥራ ቀናት በአየር ላይ የሚቆይ እና በ11ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጐ በዛኑ ቀን 4፡30 የሚከፈት መሆኑን እየገለፅን የተቀረው የጨረታ ማስታወቂያ ጥር 25 ቀን 2018 ዓ.ም በወጣው ማስታወቂያ የሚቀጥል መሆኑን እንገልፃለን።

ግልፅ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር፡- 02/2018

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ስር የሚገኛው የመሿለኪያ ጤና ጣቢያ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ እቃዎች በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

  • ሎት 1 መድኃኒት እና የላብራቶሪ ሪኤጀንት ግዥ
  • ሎት2  የሕክምና መገልገያ ቋሚ እቃ
  • ሎት 3 የሥራ መገልገያ የደንብ ልብስ ግዢ
  • ሎት 4 የፅሕፈት መሣሪያ እና አላቂ የፅዳት እቃዎች ግዥ
  • ሎት 5 የቢሮ መገልገያ ቋሚ እቃ እና ኤሌክትሮኒክስ እቃዎች ግዥ
  • ሎት 6 ልዩ ልዩ መሣሪያዎች ግዥ
  • ሎት 7 የኮምፒውተር፣ የላፐቶፕ፣ የፎቶኮፒ የፕሪንተር ጥገና
  • ሎት 8 የሠራተኛ ካፍቴሪያ አገልግሎት
  • ሎት9 ከ 8 ኩንታል በላይ የሚጭን አገልግሎት የሚሰጥ መኪና
  • ሎት- 10 ለመስተንግዶ አገልግሎት የሚውል ግብዓቶች
  • ሎት- 11 ኅትመት
  • ሎት- 12 ኤሌክትሪሺያን ባለሙያ
  • ሎት- 13 የኤሌክትሪክ መስመር እና ፊቲንግ ጥገና

ለመግዛት ስለሚፈልግ በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች ማሟላት ይጠበቅባቸዋል።

ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን የታደሰ ንግድ ፍቃድ፤ የታክስ ግዴታውን የሚያመላክቱ ሰነዶች፣ የአቅራቢነት ምዝገባና የምስክር ወረቀት፤ የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚገልፅ ማስረጃ እና አነስተኛ እና ጥቃቅን ተቋማት የድጋፍ ደብዳቤ ማስረጃ በግልፅ የሚታይ ፎቶኮፒ ማቅረብ አለባቸው።

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቂርቆስ ክ/ከተማ

ጤና ጽ/ቤት መሿለኪያ ጤና ጣቢያ

ከዚህ በፊት የወጣውን ጨረታ ለመመልከት እባክዎን ከዚህ በታች ያለውን ማስፈንጠሪያ ይጫኑ

https://tender.2merkato.com/tenders/6981b3b90a538a6ec2000001 

, , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , , ,

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *