Your cart is currently empty!
የጎንደር ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ለስራ የሚፈልጋቸውን ፕላስቲክ ነክ የውሃ እቃዎች፣ ብረት ነክ የውሃ እቃዎች፣ ዲ-ሲ-አይ ውሃ እቃዎች፣ ፓምፕ፣ ኬብል፣ ቦርድና ፓምፕ መለዋወጫ እቃዎች በግልፅ ጨረታ በማወዳደር ግዥ መፈፀም ይፈልጋል
Addis Zemen(Feb 05, 2026)
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር GTWSSS/0008/2018 ዓ/ም
የጎንደር ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ለስራ የሚፈልጋቸውን
- ሎት 1. ፕላስቲክ ነክ የውሃ እቃዎች (HDPE & PPR Fittings)፣ እና
- ሎት 2. ብረት ነክ የውሃ እቃዎች (GS Fitting)፣
- ሎት 3. ዲ–ሲ–አይ ውሃ እቃዎች (DC Fitting) እና
- ሎት 4 ፓምፕ፣ ኬብል፣ ቦርድና ፓምፕ መለዋወጫ እቃዎች በግልፅ ጨረታ በማወዳደር ግዥ መፈፀም ይፈልጋል።
በመሆኑም በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሱትን መረጃዎች በማቅረብ መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡–
- በዘርፉ ህጋዊ ንግድ ስራ ፈቃድ ያላቸው፣
- የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣
- የግብር ከፋይነት ሰርተፍኬት (TTN No) ያላቸው፣
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ NAT Register/ የሆኑና
- የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዱ ሎት የጠቅላላ ዋጋውን 1% በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ (CPO) ብቻ ማስያዝ የሚችሉ መሆን ይጠበቅባቸዋል።
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 500.00 /አምስት መቶ ብር/ በመክፈል ጎንደር ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት ቢሮ ቁጥር 27 ከቀን 28/05/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ 12/06/2018 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ድረስ መግዛት ይችላሉ፣
- በጨረታ ዝርዝሩ መሰረት ዋጋቸውን በመሙላትና በፖስታ በማሸግ የካቲት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 4፡00 ድረስ ግዥና ንብረት አስተዳደር ንዑስ የስራ ሂደት ቢሮ (ቢሮ ቁጥር 14) ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት ይችላሉ። ተጫራቾች የተወዳደሩበትን የጨረታ ሰነድ ተለያይቶ በታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦርጅናል (ቴክኒካልና ፋይናንሻል) እና አንድ ኮፒ (ቴክኒካልና ፋይናንሻል) የያዙ ሰነዶችን ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- ጨረታው የካቲት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ታሽጎ ከጠዋቱ 4፡30 ለመገኘት ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። ተጫራቾች ባይገኙም ይከፈታል።
- የጨረታው መክፈቻ ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል። በሀገር አቀፍ በዓላት ካልተዘጋ በስተቀር ዘወትር ቅዳሜ እስከ 6፡00 ሰዓት የስራ ቀን ሲሆን ይህም እንደ አንድ የስራ ቀን ይቆጠራል።
- ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 058 211 3316/058 112 0697 በመደወል ማነጋገር ይችላሉ።
ጎንደር ከተማ የመጠጥ ውሃና ፍሳሽ አገልግሎት ድርጅት
cttx Building and Finishing Materials cttx, cttx Construction and Water Works cttx, cttx Electrical, cttx Equipment and Accessories cttx, cttx Mechanical cttx, cttx Metal and Metal Working cttx, cttx Other Metals cttx, cttx Plastic Products cttx, cttx Plastic Raw Materials and Products cttx, cttx Pumps, cttx Steel, cttx Steel Raw Materials and Products cttx, cttx Water Engineering Machinery and Equipment cttx, cttx Water Pipes and Fittings cttx, Electromechanical and Electronics cttx, Metals and Aluminium cttx, Motors and Compressors cttx