Your cart is currently empty!
በአዲስ አበባ ከተማ አስ/ትምህርት ቢሮ በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 የለም 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሠራት ይፈልጋል
Addis Zemen(Feb 06, 2026)
ግልጽ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ ጨረታ መለያ ቁጥር ለም/002/2018
በአዲስ አበባ ከተማ አስ/ትምህርት ቢሮ በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 14 የለም 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች ለተዘረዘሩት
- ሎት 1 የደንብ ልብስና የስፖርት ትጥቅ፣
- ሎት2 የደንብ ልብስ ስፌት፣
- ሎት3 አላቂ የሕትመት ሥራዎች፣
- ሎት5 አላቂ የትምሀርት እቃዎች እና አጋዥ መጽሐፍት ፣
- ሎት6 አላቂ የፅዳት እቃዎች፣
- ሎት7 ልዩ ልዩ መሣሪያዎች፣
- ሎት 8 የቤተ ሙከራ ኬሚካሎችና እቃዎች፣
- ሎት9 የኤሌክትሮኒክስ ማሽነሪ እድሳትና ጥገና፣
- ሎት 10 የኤሌከትሪክ፣ የቁሳቁስና ተገጣጣሚዎች፣ የበር፣ የቧንቧ ውሃ መስመር ዝርጋታ እድሳትና ጥገና፣
- ሎት11 የኤሌክትሮኒክስ ቋሚ እቃዎች፣
- ሎት 12 ተገጣጣሚ የፈርኒቸር እቃዎች፣
- ሎት 14 የመኪና አጠቃላይ ጥገና እና የመኪና ትራንስፖርት ኪራይ
- ሎት 15.የመፀዳጃ ቤት ፍሳሽ የማስነሳት አገልግሎት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛትና ማሠራት ይፈልጋል።
በዚህ መሠረት ጨረታውን ለማሳተፍ የሚፈልጉ ሕጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው።
1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን ሕጋዊ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ለመከፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
2. በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢነት የተመዘገበና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
3. የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው፣
4. ተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ
5. ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ አለባቸው።
|
ሎት ቁጥር |
የሎት ዝርዝር |
የተጠየቀው የጨረታ ማስከበሪያ በኢትዮ ብር |
|
ሎት 1 |
የደንብ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ |
25000(ሀያ አምስት ሽህ ብር) |
|
ሎት 2 |
የደንብ ልብስ ስፌት |
5000 (አምስት ሽህ ብር) |
|
ሎት 3 |
አላቂ የህትመት ሥራዎች |
5000 (አምስት ሽህ ብር) |
|
ሎት 5 |
አላቂ የትምህርት እቃዎች እና አጋዥ መጽሐፍት… |
20000 (ሀያ ሽህ ብር) |
|
ሎት 6 |
አላቂ የጽዳት እቃዎች |
7000(አስራ ሰባት ሽህ ብር) |
|
ሎት 7 |
ልዩ ልዩ መሣሪያዎች |
10000 (አስር ሽህ ብር) |
|
ሎት 8 |
የቤት ሙከራ ኬሚካሎችና እቃዎች |
5000.00 (አምስት ሽህ ብር) |
|
ሎት 9 |
የኤሌከትሮኒክስ ማሽነሪ እድሳትና ጥገና. |
5000.00 (አምስት ሽህ ብር) |
|
ሎት 10 |
ኤሌክትሪክ፣ የቁሳቁስና ተገጣጣሚዎች፣ የበር፣ የቧንቧ ውሀ መስመር ዝርጋታ እድሳትና ጥገና |
4000 (አራት ሸህ ብር) |
|
ሎት 11 |
የኤሌከትሮኒክስ ቋሚ እቃዎች |
45000 (አርባ አምስት ሽህ ብር) |
|
ሎት 12 |
ተገጣጣሚ የፈርኒቸር እቃዎች |
20000 (ሀያ ሺህ ብር) |
|
ሎት 14 |
መኪና ትራንስፖርት ኪራይ እና የመኪና አጠቃላይ ጥገና ሥራ |
5000 (አምስት ሽህ ብር) |
|
ሎት 15 |
የመፀዳጃ ቤት ፍሳሽ የማስነሳት አገልግሎት ሥራ |
5000 (አምስት ሽህ ብር ) |
6. የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ በየሎቱ የማይመለስ ብር 100(መቶ ብር) በመከፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከፋይናንስ ቢሮ እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ።
7. ተጫራቾች በሥራና ከሎት የተደራጁ ከሆነ በራሳቸው ምርት ብቻ ካደራጃቸው ጽ/ቤት የጨረታ ማስረከቢያ ዋስትና ደብዳቤ በማፃፍ መወዳደር ይችላሉ። የራሳቸው ምርት ካልሆነና ገዝተው ለሚያቀርቡት እቃ የጨረታ በነድ መግዥያና የጨረታ ማስረከቢያ ሲፒኦ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
8. ተጫራቾች ጨረታ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የሥራ ቀናት ፋይናንስ ቢሮ በመምጣት ዋጋው የተሞላበትን የጨረታ ሰነዱን ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ለየብቻው በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው
9. ጨረታው በአስረኛው ቀን 10፡00 ሰዓት ታሽጎ በአስራ አንደኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል። የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተሰኙበት ይከፈታል።
10. ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋና የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ አለባቸው።
11. ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ናሙና ለሚቀርብባቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው ናሙና የማይቀርብባቸው ቋሚ እቃዎች መሥሪያ ቤቱ ባቀረበው ስፔስፊኬሽን መሠረት ማቅረብ አለባቸው።
12. የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፉበትን እቃ በራሳቸው ትራንስፖርት ት/ቤት ድረስ ማቅረብ አለባቸው ::
13. መ/ቤቱ ለጨረታ ከቀረበው እቃ አስከ 20% የመቀነስም ሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።
14. የኤሌክትሮኒክስ ጥገና ፣የውሃ ቧንቧ ጥገና፣ የበር ጥገና፣ የጄነሬተር ጥገና፣ የመኪና ትራንስፖርት ኪራይእናየመኪናአጠቃላይ ጥገና ሥራ፤ የመፀዳጃ ቤት ፍሳሽየማስነሳት አገልግሎት ሥራ አሸናፈው ለአንድ ዓመት ውል ይዞ መሥራት ይጠበቅበታል።
15. የመምህራን የደንብ ልብስ ለመስፋት ት/ቤቱ ድረስ ለስፌት የሚያገለግሉ እቃዎች አምጥተው መስፋት ይጠበቅበታል።
16. የጨረታ ሰነዱን በትከክል በማንበብና በመሙላት ማሕተምና ፊርማ በእያንዳንዱ ገፅ ላይ በማድረግ ዋጋ መሙያ ሎቱን ብቻ ቀዶ በማውጣት መሙላት ከጨረታው ውድቅ ያደርጋል ስለዚህ የጨረታ ሰነዱ ሁሉም በሥርዓት በመሞላት ገቢ መሆን አለበት።
17. ዋጋው ከነቫቱ መሞላት ይኖርበታል።
18. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
አድራሻ ፡- ከኢምፔርያል ሆቴል ወደ ገርጂ በሚወስደው መንገድ ከኮሪያ ሆስፒታል ጎን
ስ/ቁ-0116394668/0116295040
በአዲስ አበባ ከተማ አስ/ትምህርት ቢሮ የቦሌ ክ/ከተማ ት/ጽ/ቤት የለም 2ኛ ደረጃ ት/ቤት