በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የወረዳ 13 ጀ/አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት የተለያዩ እቃዎችን መግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Feb 07, 2026)

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዢው መለያ ቁጥር ግልጽ ጨረታ 02/18

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የወረዳ 13 ጀ/አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት ስር ላሉት ጽ/ቤቶች 02/18 ዓ.ም በጀት ዓመት የሚያስፈልጋቸውን፡

  • ሎት -1  የፅሕፈት እቃዎች
  • ሎት -2 የፅዳት እቃዎች
  • ሎት – 3 ፈርኒቸር ጥገና
  • ሎት – 4 ኤሌክትሮኒክስ ጥገና
  • ሎት 5 ቋሚ እቃ ግዢ
  • ሎት – 6 ደንብ ልብስ አገልግሎት
  • ሎት – 7 ቋሚ አላቂ እቃዎች
  • ሎት – 8 የሸልማትና ስጦታ እቃዎች
  • ሎት – 9 የጉልበት አገልግሎት
  • ሎት -10 የጭነት መኪና አገልግሎት
  • ሎት -11 የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት

ብቃት ያላቸውና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዢ መፈጸም ይፈልጋል በዚህም መሠረት

12) በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፤ የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑ እና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ

13) ተጫራቾች የጨረታው ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብር ለሎት 1 ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር ብቻ) ለሎት 2 ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር ብቻ) ለሎት 3 ብር 9,000.00 (ዘጠኝ ሺህ ብር ብቻ) ለሎት 4 ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር ብቻ) ለሎት 5 ብር 15,000.00 (አስራ አምስት ሺህ ብር ብቻ) ለሎት 6 ብር 15000 (አስራ አምስት ሺህ ብር ብቻ) ለሎት 7 ብር 12,000.00 አስራ ሁለት ሺህ ብር ብቻ) ለሎት 8 ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር ብቻ) ለሎት 9 ብር 10000 (አስር ሺህ ብር ብቻ) ለሎት 10 ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር ብቻ) ሎት 11 ብር 10,000 (አስር ሺህ ብር ብቻ) በን/ስ/ላ/ክ/ከ ወረዳ 13 ጀ/አ ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም ተዘጋጅቶ ከጨረታ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው;;

14) ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ በተከታታይ 10 የሥራ ቀናት የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወ/3/ጀ ፋይናንስ ጽ/ቤት ጀሞ አንደኛ በር በሚገኘው ሳባ ሕንጻ 6ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 606 ላይ በመምጣት የጨረታውን ሰነድ መግዛት ይችላሉ፡፡

15) ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኢንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የሥራ ቀናት በፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 606 በመምጣት ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡

16) ጨረታው ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ በአስረኛው ቀን በ11፡30 ሰዓት ታሽጎ በ11ኛው ቀን በ3፡00 ሰዓት በወረዳው ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 606 ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓትና ቦታ ታሽጎ ይከፈታል፡፡

17) ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸው ሎት1፣ ሎት2፣ ሎት5፤ ሎት6 እና ሎት7 ሎት 8 ናሙና ማቅረብ የሚኖርባቸው ሲሆን በቀረበው የፍላጎት መግለጫ መሠረት የተሟላ ፍላጎት መግለጫ ማዘጋጀትና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል

18) ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ለእያንዳንዱ ከቫት በፊት እና ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል፡፡

19) የዘገየ ጨረታ እና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም

20) አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት የግዢ ፈጻሚው መሥሪያ ቤት ግምጃ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል

21) መሥሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ለተጨማሪ ማብራሪያ ጥያቄ አድራሻ ጀሞ አንደኛ በር ሳባ ህንጻ 6ተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 606

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የወረዳ 13 ጀ/አስተዳደር
ፋ / ጽ / ቤት