በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ስር የሚገኘው እቴጌ መነን የልጃገረዶች አዳሪ ትምህርት ቤት የተለያዩ ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል


Addis Zemen(Feb 07, 2026)

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 002/18

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ስር የሚገኘው እቴጌ መነን የልጃገረዶች አዳሪ ት/ ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

1. የተለያዩ ቋሚ ዕቃዎች

2. የጽዳት ዕቃዎች

3. የጽህፈት መሳሪያዎች

4. የደንብ ልብስ እና የደንብ ልብስ ስፌት

5. የተለያዩ የስጦታ ዕቃዎች

6. የጥገና ዕቃዎች

7. የፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ ኪራይ መኪና

8. የእንስሳ ህክምና

9. የመኪና ዕቃዎች

10. የማሽነሪ ዕቃ ጥገና እና ሰርቪስ

11. ህትመት

12. አላቂ የህክምና ዕቃዎች

13. በት/ቤት ግቢ ውስጥ ያሉ የተለያዩ የጥገና ሥራዎች

  1.  ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ፡፡
  2. የታደሰ ንግድ ፈቃድ ተጨማሪ እሴት ታክስ(ቫት) ተመዝጋቢ መሆናቸውን ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ የሚችሉ እና ከፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢነት ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ስለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡
  3. ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300.00 (ሶሰት መቶ ብር) በየሎቱ በመክፈል ከት/ቤቱ ቢሮ ቁጥር 103 መግዛት ይችላሉ፡፡ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት 1ኛ ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት የጨረታውን ሰነድ ዋናውንና ኮፒውን ኤንቨሎፕ ለዚህ በተዘጋጀ የጨረታ ሣጥን ውስጥ ቢሮ ቁጥር 111 ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም ጨረታው እስከሚከፈት ድረስ የዕቃ ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  4. አሸናፊው በሚያቀርባቸው ዕቃዎች ላይ 10% የውል ማስከበሪያ ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
  5. ጨረታው 11ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ4፡30 ሰዓት ቢሮ ቁጥር 111 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
  6. ተጫራቾች ት/ቤቱ ባቀረበው የዋጋ መሙያ ብቻ በመሙላት ማቅረብ እና ያሸነፉበትን ዕቃ በራሳቸው ትራንስፖርት ት/ቤቱ ንብረት ክፍል ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  7. ት/ቤቱ የሚገዛውን ዕቃ ብዛት 20% የመጨመርና የመቀነስ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር ለእያንዳንዱ ሎት ብር 20,000.00 ማለትም (ከሎት1-6 እና 9-12 ላሉት ለእያንዳንዳቸው ሃያ ሃያ ሺህ ብር) ለሎት 7 እና 8 ለእያንዳንዱ 3,000.00 ብር ለሎት 13 5,000 ብር በባንክ የተረጋገጠ ከፍያ አቅርቦት (CPO) ብቻ በፖስታው ውስጥ አብረው ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ጥቃቅንና አነስተኛ ተወዳዳሪዎች የሚወዳደሩት በሚያመርቱት ምርት ካልሆነ በስተቀር ዕቃ ገዝተው የሚያቀርቡ ከሆነ እንደማንኛውም ተጫራቾች ሰነድ በመግዛትና ሲፒዮ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  10. ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታው ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
  11.  በጨረታ የሚሳተፉ አካላት ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ (ማብራሪያ) ከፈለጉ በአካል በመምጣት ወይም በስልክ ቁጥር 0111 261 615 /0111 22 49 54/56 በመደወል ማግኘት ይችላሉ፡፡እንዲሁም የሚሰሯቸውን ስራዎች በሙሉ በአካል ት/ቤቱ በመገኘት ሳንፕል መውሰድ ማየት ይችላሉ
  12.  ተጫራቾች በአንድ የዕቃ አይነት በአንድ ብራንድ ብቻ መወዳደር ይኖርባቸዋል፡

አድራሻ፡-እቴጌ መነን የልጃገረዶች አዳሪ ት/ቤት ከ6 ኪሎ ዩንቨርሲቲ በግራ በኩል በሚወስደው መንገድ ወይም ምስካዬ ኅዙናን መድሀኒያለም ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት ገባ ብሎ ይገኛል
እቴጌ መነን የልጃገረዶች አዳሪ ት/ ቤት


Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *